Get Mystery Box with random crypto!

ከማዶ ሚመጣው፥ ዘመድ ነው እንግዳ ከላይ የተለጋው፥ ኳስ ነው ወይስ ናዳ ብየ መች ጠየቅሁኝ መጭ | Aki Man Z Menz

ከማዶ ሚመጣው፥ ዘመድ ነው እንግዳ
ከላይ የተለጋው፥ ኳስ ነው ወይስ ናዳ
ብየ መች ጠየቅሁኝ
መጭውን ጠበቅሁት
ድንጋይ ላይ ቁጭ ብየ፤ ጸሀይ እየሞቅሁኝ፥

መከራም አላጣም፥ ተድላም አልጎደለኝ
ደንታ ነው የሌለኝ፥

ባካል በስሜትም፥ ታሞ ላገገመ
ወድቆ ለተነሳ፥ እየደጋገመ
ከገዛ ጉድጓዱ፥ አጽሙን ለሚለቅም
ሞትም ብርቅ አይደለም፥ ትንሳኤም አይደንቅም።