Get Mystery Box with random crypto!

@SHARE!! የወላዲት አምላክ የእምየ ቤተልሄሟ ይህ ነው እዩት ፈርሷልshare በማድረግ በረከት | Aki Man Z Menz

@SHARE!!
የወላዲት አምላክ የእምየ ቤተልሄሟ ይህ ነው እዩት ፈርሷልshare በማድረግ በረከት እናግኞ!
።።።።።።።።።[አይኔ-ማርያም]!
ጥንታዊቷ ስለት ሰሚዋ በይፋት የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የኦሪት መሠዊያ ያለባት {የአይኔ -ማርያም}በዚህ ቦታ ገዳም ብዙ ነገስታት ነገስውባታል፤ብዙ ጳጳሳት ተቀምጠዋባታል።
የአይኔ-ማርያም ያላትም የንጉስ ስብስቲያኖስ(ሰብስቲ) አባት ንጉስ ነጋሴ ክርስቶስ ጊስ ማርያምን የተከለ ነው፤በርቀት ይችንም ጥንታዊ ገዳም አይቷት አይኔ -ማርያም አላት።
ንጉስ ነጋሴ ክርስቶስ 15 ዓመት በዚህ ቦታ መጦ ከተማ መስርቶ ከዚያም ወደ ጎንደር ሄዶ አረፈ በፊት አቦ በሚባል ቦታ ተቀበረ፤ ልጆቹም አክዋ ክርስቶስ እና ስብስቲያኖስ ይባሉ ነበር።እንዳረፈ ልጆቹ እኔ እንግሳለሁ እኔ እነግሳለሁ ተባበሉ ተጣሉ ታላቁን አክዋ ክርስቶስ አሸንፎ ሰበስቲያኖስ በዚህ ገዳም በአይኔ ማርያም ነገሰ።አክዋ ክርስቶስም ወጃ ቅዱስ ሚካኤልን ተከሎ አረፈ። እስካሁንም በይፋት ወጃ ቅዱስ ሚካኤል አካባቢ በቤተክርስቲያኑ አቅራቢያ አክዋ ባዶ የሚባል ቦታ አለ።
ንጉስ ስብስቲያኖስም 5አመት ገዝቶ ከማረፉ በፊት በይፋት ይች ብቻ አይኔ ማርያም ጥንታዊ ገዳም ነበረች፤ ቀጥሎም ይዛባ ማርያምን ገዳም ተተከለች።
ታቦት አልነበረም በየአድባራቱ ፤ከዚያም የንጉስ ስብስቲያኖስ ልጆቹ አብየ እና መርሐዊት የሚባሉ ነበሩት።
ነጋሴ ክርስቶስም የነበረውን መሬት እንደየ ደረጃቸው ለካህናቱ ለዲያቆናቱ ለአይኔ ማርያም ብዙ ጋሻ መሬትም ሰጥቷት ጎንደር አካባቢውን ይገዛ ስለነበረ ሄዶ በድንገት አረፈ።
ከአይኔ ማርያም የነበረውን የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ ገብርኤል ታቦት የንጉስ ስብስቲያኖስ ልጅ አብየ እንደ ስርቆሽ አድርጎ ወስዶ ዶቋቂት በሚባል ቦታ የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ወስዶ ቤተክርስቲያን ስራ ።
ንጉስ ነጋሴ ክርስቶስ የስብስትያኖስ አባት ይዛባ ቅድስት ማርያምን ተከለ።
ንጉስ አብየ የሰብስቲያኖስ ልጁ ታቦታቱን እንደ ስርቆሽ አድርጎ ሲወስድ አባቱም ስብስቲያኖስ እና አይኔ ማርያም ካህናት አያውቁም ነበር። ያለፍቃዳችን እንዴት ይተክላል ገብተን ታቦታቱን እንይ ብለው ገብው ሲያዩት የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ጠፍቷል፤ የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ወስዶ ዶቋቂት ተክሎታል ቤተክርስቲያን ሰርቷል።
አባቱ ስብስቲያኖስ እንዴት ሳያስፈቅድ ታቦታቱን ይወስዳል ብሎ ከልጅ ከአብየ ተጣላ ጦርነት ገጠመ ሾላ ሚዳ በሚባል ቦታ፤የልጁ የአብየ አሽከሮችም ንጉስ ሰብስቲያኖስ ገደሉት።
ልጁ አብየ ማርኩት እንጅ እንዴት አባቴን ትገላላችሁ ብሎ አሽከሮቹን ተጣላቸው አብየ አሽከሮቹንም ገደላቸው ።ንጉስ ሰብስትያኖስም በአይኔ ማርያም ተቀበረ።ልጁም አቡየ ንጉስ ሆነ ስሙም አመሃእየሱስ ወይም አብየ ተብሎ ነገሰ።
የተተከለበት ተራራ ዶቋቂት የሚባለው ቦታው ቤተክርስትያን ከመሰራቱ በፊት አባቱ ስብስቲያኖስ በርቀት ሲያይ በተራራው መብራት አየ ፤በዚያም ግዜ በ16ክፍለ ዘመን በዚህ ቦታ መብራት ያየበት ቦታ ዶቋቂት ተራራ ሲሄድ ከሌላ ሀገር መጥተው የወረሩት እምነት የሌላቸውን ሰዎች አየ አስጠመቃቸው በዶቋቂት በሚባለው ቦታ ክርስትያን አደረጋቸው።
ልጁም ንጉስ አብየ በዶቋቂት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን የተከለበት ቦታ ማለት ነው።ንጉስ አብየ 30ዓመት ገዝቶ በዶቋቂት ቅዱስ ሚካኤል ተቀበረ።ቦታውም የአብየ(አመሀእየሱስ)ተባለ።
እህቱም መንበራዊት የምትባል ነበረች፤ ንብ አንባ በሚባል ቦታ ትኖር ነበር፤አሽከሮቿ ከንብ አንባ እያዘሉ እያመጡ ዶቋቂት ነበር የምታስቀድሰው፤አርግዛም አሽከሮቿ ወደ ዶቋቂት በተልባ ውስጥ ወሰዷት አርግዥ እንዴት በተልባ ምች መቶኞ እንዳሶርድ አሸከሮቼ እንዲህ አደረጉኝ ብላ ለወንድሟ ንጉስ አብየ(አመሀእየሱስ) አዝና ነገረችው።
ወንድሟ ንጉስ አብየ እንደስርቆሽ የወሰደውን ሁለት ታቦታት ማለትም ዶቋቂት በሚባል ቦታ የተከለውን የቅዱስ ሚካኤል የቅዱስ ገብርኤል ነበር። መንበራዊት የነበረችበት ንብ አንባ የሚባለው ቦታ ትንሽ ርቀትም ቆላም ስለነበረ ፤በንብ አንባ ወለደች ለወንድሟ ለንጉስም እባክህ በድንኳን ለአንድ ቀን የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ስጠኞና ክርስትና ላስነሳ ብላ ጠየቀችው ንጉሱም ወንድሟ ፈቅዶላት ክርስትና አስነስታ አንድ ቀን በድንኳን አድሮ ታቦቱን ሊወስዱ ሲል እንቢ አላቸው፤ በዚያሜ ታቦቱ በድንኳን በነበረብት ለአንድ ቀን መጥቶ በአረፈበት ንብ አንባ በሚባል ቦታ ቅዱስ ገብርኤል ተተከለ።
ልጅም ወልዳ በንብ አንባ ቅዱስ ገብርኤል ክርስትና አስነሳች።ቦታውም ንብ አባ የመንበራዊት ተባለ፤ዶቋቂትም የአቡየ(አመሀእየሱስ)ይባላል።
ንግስናውም ዘራቸው ከነጋሴ ክርስቶስ እስከ ሰሐለ ስላሴ ፣ሀይለ መለኮት፣ አፄ እምየ ምንሊክ እና አፄ ሐይለ ስላሴ ድረስ ደረሰ።
ከአይኔ ማርያም ብዙ ታቦታት ወስደው በተለያየ ቦታ ነገስታቶች ታቦታትን ተከሉ ወጃ ቅዱስ ሚካኤል ፣ደብረሲና መድሐኔዓለም ፣ይዛባ ማርያም፣ ዶቋቂት ቅዱስ ሚካኤል፣ ንብ አንባ ቅዱስ ገብርኤል ከአይኔ ማርያም እንደሄዱ ይነገራል።
አይኔ ማርያም እርዳታችሁን ትፈልጋለች
ሀ/ቤተልሄሟ ይህ ነው እዩት ፈርሷል
ሐ/አጥር የላትም
መ/መስቀል ቤትና ደጀ ሰላሙ ፈርሷል የአካባቢው ምዕመንም የመጀመሪያ ሆና ወደ ኋላ ቀረች አሮጊቷን ማርያም አስቧት ቤቷን እንስራ ብለዋል።
ለመርዳት እግዚአብሔር ሲፈቅድ ነው፤ለእርሱ ብድር ነውና መስጠት መርዳት ለእግዚአብሔር ማበደር ነው።
ለመርዳት ለበረከቱ በያላችሁበት ታብቃችሁ፤ ሀገራችን ሰላሙን አንድነትን ፍቅርን እውነትን ትዕግስትን ትስጠን።አሜን!
የገዳሟ የባንክ ቁጥር
Acccount no-74327877
Account name-አይኔ ደብረ ንግስት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን
አቢሲኒያ ባንክ
በሌላ በሁሉም ሐገር ድርቅ ሆኖ በዚህ በይዛባ እና በአይኔ ማርያም አካባቢ በልግ ሆኖ (እህል ሆኖ)____ይህ ተብሎ ነበር...........
<አይኔና ይዛባ አለች ወይ እናትህ፥
ከፈጠርከው ፍጡር ምነው መለየትህ፥
ከፈጠርኩት ፍጡር እኔ መለየቴ፥
አይኔና ይዛባ በትኖር ነው እናቴ።>
በዚያን ግዜ ተባለ ብለው የሐገሩ ሽማግሌዎች ነገሩኝ ተመስገን!
ቦታዋ፦በመንዝናይፋት በይፋት አውራጃ ከደብረሲና ከተማ በእግር የ1ሰዓት መንገድ በመኪና እስከ ቤተክርስቲያን ይገባል 15ደቂቃ መንገድ ነው።