Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Freeseminar
Cloudbridge
Traininginstitute
Cryptocurrency
Аирдроп
Tikvahtechteam
Techdailly
Attention
Cbdc
Cryptocurrencies
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.51K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 255

2022-05-26 21:52:47 #የዛሬ (ግንቦት 18/2017)

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በማዕድን ሥራ እና በሌሎችም ዓለም ዐቀፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመምከር ለመምከር በሚቀጥለው ወር በአዲስ አበባ የሚኒስቴሮች የጋራ ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።

በጭልጋና አካባቢዋ ተፈናቅለው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሠራ እንደሚገኝ ተነግሯል። ከትላንት አንስቶ ከአይከል እና በዙሪያዋ ተፈናቅለው የነበሩ 11 ሺህ 938 የህበረተሰብ ክፍሎች ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ሲሆን ወደ አይከል ከተማ ሲገቡ ማህበረሰቡ በነቂስ ወጥቶ ተቀብሏቸዋል።

የሞጣ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ኮማንድ ፖስት ፤ በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦች በሁለት ቀን ለመንግስት እጅ እንዲሰጡት አሳስቧል።ግለሰቦቹ በተሰጣቸው እድል ባለመጠቀም ለሚወሰደው ርምጃ ሁሉ ሀላፊነት አልወስድምም ነው ያለው። በተጨማሪም ከጠዋቱ 12:30 በፊትና ከምሽቱ 1: 30 በኋላ ስምሪት ከተሰጣቸው የጸጥታ ሀይሎች ውጭ የእንቅስቃሴ ገደብ ተቀምጧል።

የፍትህ መፅሄት ማናጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቢሮው ሲቪል በለበሱ በሁለት መኪና በመጡ የፀጥታ ሀይሎች መወሰዱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ አሳውቋል። በተመሳሳይ ከጥቂት ወራት በፊት ታስሮ የተፈታው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በዛሬው ዕለት መታሰሩ ተሰምቷል። ጋዜጠኛ ያየሰው ዛሬ ሀሙስ በፀጥታ ኃይሎች ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣባያ መወሰዱን ጠበቃው ገልፀዋል። ጠበቃው አቶ ታደለ ገ/መድኅን የካ አባዶ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ መምጣታቸውን በተናገሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።

‘ US Embassy Addis Ababa ’ በሚል ስም ከ127 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የቴሌግራም ቻነል " አሜሪካ ኤምባሲ በጦርነት የተጎዳዉን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመደገፍና ከክፍለዘመን የዘለቀዉን የአሜሪካና የኢትዮጵያን ወዳጅነት ለማጠናከር ለ20 ሺህ ኢትዮጵያዉያን በአሜሪካ የስራ ዕድል ፈጥሯል " በሚል ያጋራው መረጃ ሀሰተኛ እና ሰዎችን ለማጭበርበር እንደሆነ ኢንባሲኸ።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
12.2K viewsedited  18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 21:24:00
የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ሳያሳድሱ የቀሩ 830 ድርጅቶች ፈቃዳቸው ተሰረዘ፡፡

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒሰቴር የጫት ምርትን በተመለከተ የሚደረገውን ህገ-ወጥ ንግድ እና የኮንትሮባንድ ሥራ ለመከላከል ግብረ-ሃይል በማደራጀት ምርቱ በሚወጣባቸው የሃገሪቱ መውጫ በሮች ላይ ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ በህገ-ወጥ ተግባራቱ ላይ ተሳትፎ ነበራቸው ያላቸው ድርጅቶች ላይ እርምጃ ወስዷል።

በዚህም፦

1ኛ. የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ሳያሳድሱ 830 የጫት ምርት ላኪ ድርጅቶች በመገኘታቸዉ የንግድ ስራ ፈቃዳቸው ሰርዟል፡፡

2ኛ. የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ሳያድሱ 14 የጫት ምርት በመላክ ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን የንግድ ስራ ፈቃዳቸው ሰርዟል፡፡

3ኛ. የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ኖሯቸዉ በህግ ወጥ መንገድ የምርት መላኪያ ፍቃድ ለሶሰተኛ ወገን አሳልፈዉ የሰጡ 40 የጫት ምርት ላኪ ድርጅቶች የንግድ ስራ ፈቃዳቸው በጊዜያዊነት እንዲታገድ ተደርጓል፡፡

ህገ-ወጥ ድርጊቱ አስከፊ ገጽታ እየተንስራፋ በመምጣቱ ሀገሪቱ ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሪ ከማሳጣቱም ባሻገር የሀገርን ሀብት ለጎረቤት ሃገራት ሲሳይ በማድረግ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል።

ከሀገር የሚወጡ ማናቸውንም የጫት ምርት አይነት በየጊዜው በመመዝገብ የመላክያ ፍቃድ ለመስጠት የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥ ዝግጅት የጨረሰ በመሆኑንም ጠቁሟል።

''ይህ መግለጫ ከተሰጠበት ዕለት አንስቶ ላኪ ድርጅቶች የሚልኩትን የጫት ምርት የግብይት ውል የባንክ የመላኪያ ፍቃድ ከመውሰዳችሁ በፊት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድረስ በመምጣት እንድታስመዘግቡ እና ህጋዊነቱን እንድታረጋግጡ እናሳውቃለን፡፡'' ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።
15.0K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 10:57:00
ኢትዮጵያና ናይጄሪያ በሚቀጥለው ወር በሚኒስቴር ደረጃ የጋራ ስብሰባ በአዲስ አበባ ያደርጋሉ።

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በማዕድን ሥራ እና በሌሎችም ዓለም ዐቀፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመምከር ለመምከር በሚቀጥለው ወር በአዲስ አበባ የሚኒስቴሮች የጋራ ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንት በናይጄሪያ ያደረጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ተከትሎ ነው መርኃ ግብሩን ለማከናወን ከስምምነት የተደረሰው፡፡

ስለሁለቱ ሀገራት ግኑኝነት አስተያየት የሰጡት በኢትዮጵያ የናይጄሪያ አምባሳደር ቪክቶር አዴሌክ በኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ገልጸው ሁለቱ ሀገራት ወደፊትም ቢሆን የጋራ ጥቅም ላይ በትኩረት ይሰራሉ ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የናይጄሪያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ኢኳቶሪያል ጊኒ ዋና ከተማ ማላቦ በሚደረገው የአፍሪካ ሕብረት ልዩ ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉም ታውቋል፡፡

ስብሰባው በአፍሪካ አኅጉር እያቆጠቆጠ በመጣው ሽብርተኝነት፣ ኢ-ህገመንግሥታዊ የሥርዓት ለውጥ እና ሰብአዊ ድጋፍ ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (Walta TV)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
26.3K viewsedited  07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 10:08:13
በባቡር የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀመው ስርቆት አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል ተባለ።

ለአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

በ2013 በጀት ዓመት ብቻ 1 ሚሊዮን 293 ሺህ 350 ብር የሚገመት ርዝመቱ 1 ሺህ 55 ሜትር የኤሌክትሪክ ኬብል ስርቆት የተፈፀመ ሲሆን በ2014 በጀት ዓመትም 24 ሚሊዮን 800 ሺህ 725 ብር በላይ የሚገመት ርዝመቱ 15 ሺህ 347 ሜትር የኤሌክትሪክ ኬብል ስርቆት ተፈጽሟል።

ተቋሙ ስርቆቱን ለመከላከል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ቢሆንም ድርጊቱን በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ የሚወሰደው እርምጃ አስተማሪ ባለመሆኑ ችግሩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ማስተባበሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቡልቱማ ቂጣታ ገልፀዋል፡፡

በ2014 በጀት ዓመት 11 ወራት በተደረገ ክትትልና የማጣራት ስራ በአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ በቁጥር ከ37 በላይ ‘’የስርቆትና ጉዳት ማድረስ’’ የወንጀል ተግባራት ተፈፅመው ለተለያዩ የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች ክስ ተመስርቶ በምርመራና በፍርድ ሂደት ላይ ናቸው።

በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ስርቆት ሲፈፅም የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ በሃገሪቱ የወንጀል ሕግ ከ15 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ይቀጣል። በሽያጭ፣ በተውሶ፣ በስጦታ፣ በመያዣነት የተቀበለ ወይም በማናቸውም አኳኋን የወሰደ፣ የተገለገለ የደበቀ ወይም ያስቀመጠ፣ ማንኛውም ግለሰብ ደግሞ ከ5 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ ይቀጣል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
25.4K viewsedited  07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 10:07:27
ኢትኤል ዲዛይን ❖ Ethel Design

ለመኖርያ ቤት ለቢሮ ለንግድ ቦታዎ ውብ እና ማራኪ የሆኑ ዲዛይኖችን በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ካለው የፊኒሺንግ ስራ ጋር ሰርተን እናስረክቦታለን። ይደውሉልን።

የምንሰጣቸው አገልግሎት
የዲዛይን እና የፊኒሺንግ ስራ
የእንጨት ፓርቲሽኖችን መስራት
አጠቃላይ የእንጨት ስራ
ብራንዲንግ

Contact us @etheldesign1
0939902740
0919361804

Telegram: t.me/etheldesign
19.3K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 10:07:12
Register at https://www.effsaa.org/short-term-training-program-registration-form/ after the settlement of the training fee.
Venue
At the training hall of Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) which is located at Kazanchis, Nigist Towers Hotel & Apartments 4th Floor (In front of Elilly International Hotel)
For More Information,
Call us at +251 115 589045 / +251 903 182525
OR
Visit our telegram channel
https://t.me/EFFSAAOfficial
20.8K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 23:44:08 #የዛሬ (ግንቦት 17/2014)

በየጊዜው በርካቶች በታጣቁ ሰዎች በሚከፈት ተኩስ የሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ትላንትም እጅግ በጣም ዘግናኝ የሚባል ጥቃት ተፈፅሞ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት ተገድለዋል። በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አንድ የ18 ዓመት ወጣት በከፈተው የተኩስ እሩምታ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት መገደላቸውን ተዘግቧል።

ኮለኔል ገመቹ አያና ዛሬ ከታሰሩበት ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ይስተዋል የነበረውን የተሽከርካሪ ስርቆት ለመከላከል እና ወንጀል ፈፃሚዎችን ህግ ፊት ለማቅረብ የአዲስ አበባ ፖሊስ በጥናት ላይ በመመስረት የምርመራ እና የክትትል ቡድን አቋቁሞ ባካሄደው ኦፕሬሽን በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 22 ተሽከርካሪዎችንና 33 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ከ22 አመታት በፊት አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው ዓለም ዐቀፍ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ማኅበር 22ኛውን ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ከሐምሌ 8 እስከ 18 2014 ዓ.ም “እስላማዊ እሴቶች ለሀገር ሰላም እና እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን ለሁለት ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት የናይጄሪያዋ ዋና ከተማ አቡጃ ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከፊታችን ለሚጠብቀው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ልምምዳቸውን ጀምረዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ባደረገው መረጃ ዋልያዎቹ ከሌሴቶ አቻቸው ጋር ግንቦት 20 እና 22 በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ሜዳ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ እንደሚያደርጉ አሳውቋል።

የውጭ የሞባይል ገንዘብ ኦፕሬተሮች ወይም የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ሰጪዎች የባንክ አዋጁ ማሻሻያ ከመደረጉ በፊትም ቢሆን በኢትዮጵያ እንዲሰሩ ይፈቀድላቸዋል ተብሏል። የዲጂታል ክፍያ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በመዘጋጀት ላይ ሲሆን አዋጁ ሲጠናቀቅ የውጭ ባለሀብቶች የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላቸዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
4.9K viewsedited  20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 18:43:12
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ20 ከተሞችን የውሃ አገልግሎቶች አሠራር ለማዘመን ስምምነት ተፈራረመ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ20 ከተሞችን የውሃ አገልግሎቶች አሠራር የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓትን በማስፈን ለማዘመን ዳፍ ቴክ ሶሻል አይ ሲቲ ሶሉሽን፣ ኢንታፕስ ኮንሰልታንሲ እና ያዮቤ አይሲቲ ሶልሽን ከተባሉ ሦስት ተቋማት ጋር ስምምነት አድርጓል።

የመረጃ አስተዳደር ሥርዓትን ማስፈን የየከተሞቹን ውሃ አገልግለቶች የውሃ ቆጣሪ ንባብ ፣ ገቢ አሰባሰብ ፣ የብድር አስተዳደር፣ የደንበኞች መስተንግዶ፣አጠቃላይ የሂሳብ አያያዝ ሥራንና የሰው ኃይል አጠቃቀምን በዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር ያስችላል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ገልጸዋል።

በሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ከተቃቀፉ 22 ከተሞች በ20ዎቹ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ፕሮጀክቱ በ540 ቀናት ወይም በ18 ወር ጊዜ የሚጠናቀቅ ሲሆን 118.8 ሚሊየን ብር በጀት ተመድቦለታል፡፡

በተመሳሳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ላሊፍቱ አጠቃላይ ልማትና የማማከር አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ጋር የአማካሪ ቅጥር ውል የተፈራረመ ሲሆን አማካሪ ድርጅቱ በደቡብ ክልል ሲራሮ ወረዳ እና በሲዳማ ክልል አዋሳ ዙርያ ባሉ ወረዳዎች ጥናት ያደርጋል ተብሏል።

ጥናቱም፥ በተደጋጋሚ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚጠቁና የውሃ እጥረት ላለባቸው ቀበሌዎች ለትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማት ጨምሮ የውሃ አቅርቦት፣ የአካባቢ ጽደዳትና የግል ንጽህና ደረጃ ግምገማ ጥናት ማካሄድ፣ ሊኖር የሚችል የውሃ አማራጭ የአዋጭነት ጥናት ማከናወን እና አማራጩ የከርሰ ምድር ውሃ ከሆነ የጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ መከታተልን፣ በአዋጭነት ጥናቱ ላይ የተመረኮች ዝርዝር ንድፍ ማዘጋጀትን ያካትታል፡፡

@tikvahethmagazine
19.2K viewsedited  15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 18:29:49
#Ethiopia #Nigeria

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን ለሁለት ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት የናይጄሪያዋ ዋና ከተማ አቡጃ ደርሰዋል። (PMO)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
17.7K viewsedited  15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 18:29:06
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+Zhm6yWqPh7U0N2E0
17.4K views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ