Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (ግንቦት 18/2017) ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በሳይንስና ቴክ | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (ግንቦት 18/2017)

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በማዕድን ሥራ እና በሌሎችም ዓለም ዐቀፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመምከር ለመምከር በሚቀጥለው ወር በአዲስ አበባ የሚኒስቴሮች የጋራ ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።

በጭልጋና አካባቢዋ ተፈናቅለው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሠራ እንደሚገኝ ተነግሯል። ከትላንት አንስቶ ከአይከል እና በዙሪያዋ ተፈናቅለው የነበሩ 11 ሺህ 938 የህበረተሰብ ክፍሎች ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ሲሆን ወደ አይከል ከተማ ሲገቡ ማህበረሰቡ በነቂስ ወጥቶ ተቀብሏቸዋል።

የሞጣ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ኮማንድ ፖስት ፤ በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦች በሁለት ቀን ለመንግስት እጅ እንዲሰጡት አሳስቧል።ግለሰቦቹ በተሰጣቸው እድል ባለመጠቀም ለሚወሰደው ርምጃ ሁሉ ሀላፊነት አልወስድምም ነው ያለው። በተጨማሪም ከጠዋቱ 12:30 በፊትና ከምሽቱ 1: 30 በኋላ ስምሪት ከተሰጣቸው የጸጥታ ሀይሎች ውጭ የእንቅስቃሴ ገደብ ተቀምጧል።

የፍትህ መፅሄት ማናጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቢሮው ሲቪል በለበሱ በሁለት መኪና በመጡ የፀጥታ ሀይሎች መወሰዱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ አሳውቋል። በተመሳሳይ ከጥቂት ወራት በፊት ታስሮ የተፈታው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በዛሬው ዕለት መታሰሩ ተሰምቷል። ጋዜጠኛ ያየሰው ዛሬ ሀሙስ በፀጥታ ኃይሎች ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣባያ መወሰዱን ጠበቃው ገልፀዋል። ጠበቃው አቶ ታደለ ገ/መድኅን የካ አባዶ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ መምጣታቸውን በተናገሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።

‘ US Embassy Addis Ababa ’ በሚል ስም ከ127 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የቴሌግራም ቻነል " አሜሪካ ኤምባሲ በጦርነት የተጎዳዉን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመደገፍና ከክፍለዘመን የዘለቀዉን የአሜሪካና የኢትዮጵያን ወዳጅነት ለማጠናከር ለ20 ሺህ ኢትዮጵያዉያን በአሜሪካ የስራ ዕድል ፈጥሯል " በሚል ያጋራው መረጃ ሀሰተኛ እና ሰዎችን ለማጭበርበር እንደሆነ ኢንባሲኸ።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot