Get Mystery Box with random crypto!

የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ሳያሳድሱ የቀሩ 830 ድርጅቶች ፈቃዳቸው ተሰረዘ፡፡ የንግ | TIKVAH-MAGAZINE

የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ሳያሳድሱ የቀሩ 830 ድርጅቶች ፈቃዳቸው ተሰረዘ፡፡

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒሰቴር የጫት ምርትን በተመለከተ የሚደረገውን ህገ-ወጥ ንግድ እና የኮንትሮባንድ ሥራ ለመከላከል ግብረ-ሃይል በማደራጀት ምርቱ በሚወጣባቸው የሃገሪቱ መውጫ በሮች ላይ ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ በህገ-ወጥ ተግባራቱ ላይ ተሳትፎ ነበራቸው ያላቸው ድርጅቶች ላይ እርምጃ ወስዷል።

በዚህም፦

1ኛ. የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ሳያሳድሱ 830 የጫት ምርት ላኪ ድርጅቶች በመገኘታቸዉ የንግድ ስራ ፈቃዳቸው ሰርዟል፡፡

2ኛ. የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ሳያድሱ 14 የጫት ምርት በመላክ ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን የንግድ ስራ ፈቃዳቸው ሰርዟል፡፡

3ኛ. የጫት ምርት የላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ኖሯቸዉ በህግ ወጥ መንገድ የምርት መላኪያ ፍቃድ ለሶሰተኛ ወገን አሳልፈዉ የሰጡ 40 የጫት ምርት ላኪ ድርጅቶች የንግድ ስራ ፈቃዳቸው በጊዜያዊነት እንዲታገድ ተደርጓል፡፡

ህገ-ወጥ ድርጊቱ አስከፊ ገጽታ እየተንስራፋ በመምጣቱ ሀገሪቱ ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሪ ከማሳጣቱም ባሻገር የሀገርን ሀብት ለጎረቤት ሃገራት ሲሳይ በማድረግ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል።

ከሀገር የሚወጡ ማናቸውንም የጫት ምርት አይነት በየጊዜው በመመዝገብ የመላክያ ፍቃድ ለመስጠት የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥ ዝግጅት የጨረሰ በመሆኑንም ጠቁሟል።

''ይህ መግለጫ ከተሰጠበት ዕለት አንስቶ ላኪ ድርጅቶች የሚልኩትን የጫት ምርት የግብይት ውል የባንክ የመላኪያ ፍቃድ ከመውሰዳችሁ በፊት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድረስ በመምጣት እንድታስመዘግቡ እና ህጋዊነቱን እንድታረጋግጡ እናሳውቃለን፡፡'' ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።