Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያና ናይጄሪያ በሚቀጥለው ወር በሚኒስቴር ደረጃ የጋራ ስብሰባ በአዲስ አበባ ያደርጋሉ። ኢት | TIKVAH-MAGAZINE

ኢትዮጵያና ናይጄሪያ በሚቀጥለው ወር በሚኒስቴር ደረጃ የጋራ ስብሰባ በአዲስ አበባ ያደርጋሉ።

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በማዕድን ሥራ እና በሌሎችም ዓለም ዐቀፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመምከር ለመምከር በሚቀጥለው ወር በአዲስ አበባ የሚኒስቴሮች የጋራ ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንት በናይጄሪያ ያደረጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ተከትሎ ነው መርኃ ግብሩን ለማከናወን ከስምምነት የተደረሰው፡፡

ስለሁለቱ ሀገራት ግኑኝነት አስተያየት የሰጡት በኢትዮጵያ የናይጄሪያ አምባሳደር ቪክቶር አዴሌክ በኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ገልጸው ሁለቱ ሀገራት ወደፊትም ቢሆን የጋራ ጥቅም ላይ በትኩረት ይሰራሉ ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የናይጄሪያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ኢኳቶሪያል ጊኒ ዋና ከተማ ማላቦ በሚደረገው የአፍሪካ ሕብረት ልዩ ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉም ታውቋል፡፡

ስብሰባው በአፍሪካ አኅጉር እያቆጠቆጠ በመጣው ሽብርተኝነት፣ ኢ-ህገመንግሥታዊ የሥርዓት ለውጥ እና ሰብአዊ ድጋፍ ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (Walta TV)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot