Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Freeseminar
Cloudbridge
Traininginstitute
Cryptocurrency
Аирдроп
Tikvahtechteam
Techdailly
Attention
Cbdc
Cryptocurrencies
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.51K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 258

2022-05-23 16:15:36
ARE YOU LOOKING FOR LOGISTICS RELATED SHORT TERM
TRAINING PROGRAMS?

Our Association, Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) has a good news!!!
We arranged continuous short term training programs on various topics of Logistics.

INTERESTED TO KNOW MORE?
Please call us at +251 903 182525 or +251 115 589045
OR
Visit our telegram channel
https://t.me/EFFSAAOfficial
18.1K views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 11:49:09
#ጥቆማ

'አዩቴ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ (AYuTe Ethiopia Challenge)' የተሰኘና በኢትዮጵያ ግብርናን ለማሻሻል የሚረዳ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ዕድሜያቸው ከ18-29 የሆኑ ኢትዮጵያንን የሚያሳትፍ ውድድር ይፋ ሆኗል።

ውድድሩ፥ በኢትዮጵያ ያሉ አነስተኛ አርሶ አደሮችን ተግዳሮቶች መቅረፍ ምርትን ምርታማነትን፣ ገቢን፣ የፋይናንስ አቅርቦትንና የመቋቋም አቅም ያላቸውን የግብርና ቴክኖሎጂ ሀሳቦችን አወዳድሮ ለመሸለም ያለመ ነው።

የማመልከቻ ጊዜው ከግንቦት 13 ቀን 2014 ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ አሸናፊዎች 20 ሺ ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቷል።

ለማመልከት : https://ayute-ethiopia.et/apply-here/

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.4K viewsedited  08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 11:02:11
የአፈር አሲዳመነት አምራች በሚባሉት ክልሎች ላይ በስፋት መከሰቱ ተጠቆመ።

የአፈር አሲዳመነት አምራች በሚባሉት ክልሎች ላይ በስፋት መከሰቱ በምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር ነገር ነው።

የግብርና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው፦

በኦሮሚያ ክልል በ14 ወረዳዎች 1.7 ሚሊዬን ሄ/ር መሬት፤

በአማራ ክልል ለእርሻ አገልግሎት ከሚውለው 4.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 1.2 ሚሊዬን የሚሆነው፤

በደቡብ ክልል ከሚታረሰው የእርሻ መሬት 44 በመቶ የሚሆነው እንዲሁም፤

በሲዳማ ክልል አጠቃላይ ካለው የመሬት ስፋት 95 ሺህ ሄ/ር የሚሆነው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነው ተብሏል፡፡

አሁን ላይ በመንግስት በኩል ያለው የኖራ አቀርቦት በቂ ባለመሆኑ መንግስት ኖራ በብዛት አንዲመረት የግል ባለሀብቶችን ወደ ዘርፉ በሚኒስቴሩ በአማራጭ መፍትሔነት ተይዟል።

በተጠማሪም ኖራ የሚገኝባቸው ቦታዎች ላይ የፀጥታ ችግር እንዳይኖር የማድረግ እንዲሁም አሲዳማነት የሚታይባቸው ቦታዎችን በጥናት በመለየትና ኖራ የሚመረትባቸው ቦታዎች አንዲቃራረቡ በማድረግ ለትራንሰፖርት የሚወጣውን ከፍተኛ ወጭም መቀነስ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
21.9K viewsedited  08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 10:59:25
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በባህላዊ ፍርድ ቤቶች ከሁለት ሺህ በላይ የክስ መዝገቦች እልባት አግኝተዋል።

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ በሶስት ወራት ውስጥ ከሁለት ሺህ በላይ የክስ መዝገቦች በባህላዊ ፍርድ ቤቶች እልባት እንዲያገኙ ተደርጓል ተብሏል። ይህንን የተመለከተ ውይይትም በጭሮ ከተማ ተካሂዷል።

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቡካር ከዲሮ በዞኑ በሶስት ወራት ውስጥ ከቀረቡት 2 ሺህ 954 መዝገቦች 2 ሺህ 230 ጉዳዮች በባህላዊ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በመደበኛ ፍርድ ቤቶች የቀረቡ ጉዳዮች በባለ ጉዳዮቹ ፈቃደኝነት ላይ በመመስረት ጉዳዩ በባህላዊ ፍርድ ቤት የሚታይ ሲሆን በገጠራማ አካባቢ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የስራ ጊዜያቸውንና ለመጓጓዣ የሚያወጡትን ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶላቸዋል ብለዋል።

ጨፌ ኦሮሚያ በሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብስባ በኦሮሚያ ክልል ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች በተጨማሪ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች እንዲቋቋሙ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 240/2013 ማጽደቁ የሚታወስ ነው። (ENA)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
19.6K viewsedited  07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 10:56:47
የት ለመማር ወሰኑ?

በ Software Engineering እና በ Information Technology and Systems በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቶን ለመማር ወደ #ቢትስኮሌጅ ቢመጡ አብዝተው ያተርፋሉ።

በ4 ዓመት ውስጥ በዲግሪ ብቻ ሳይሆን ብቁ ሰራተኛ ሆነው ጭምር ይመረቃሉ።

ጥራታቸውን የጠበቁና የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያግዙ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን፣ በዘመናዊ መልክ የተደራጁ መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተመፃህፍት፣ የኮምፒዩተር ላብራቶሪዎች እና እጅግ ዘመናዊ የአይቲ መሠረተ ልማት #በቢትስኮሌጅ የተሟሉ ናቸው።

ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ፦

ድረ ገጽ www.bitscollege.edu.et

0982 363636 / 0978028655

#BITSCollege
20.5K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 10:56:47
ኢትኤል ዲዛይን ❖ Ethel Design

ለመኖርያ ቤት ለቢሮ ለንግድ ቦታዎ ውብ እና ማራኪ የሆኑ ዲዛይኖችን በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ካለው የፊኒሺንግ ስራ ጋር ሰርተን እናስረክቦታለን። ይደውሉልን።

የምንሰጣቸው አገልግሎት
የዲዛይን እና የፊኒሺንግ ስራ
የእንጨት ፓርቲሽኖችን መስራት
አጠቃላይ የእንጨት ስራ
ብራንዲንግ

Contact us @etheldesign1
0939902740
0919361804

Telegram: t.me/etheldesign
22.3K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 22:16:38 #የዛሬ (ግንቦት 14/2014)

ኢሰመኮ የፌዴራል መንግሥት እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች "በተቀናጀ መንገድ የሕግ በላይነትን ማስከበር" በሚል ባለፉት ጥቂት ቀናት መውሰድ በጀመሩት እርምጃ፣ ጋዜጠኞችና የማኅበረሰብ አንቂዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን ገልጿል።

በርካታ ታሳሪዎች ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ውጭ መታሰራቸውን፣ ፍ/ቤት ያለመቅረባቸውን፣ በቤተሰብ አለመጎብኘታቸውን አመልክቷል። በተለይ በአማራ ክልል በርካታ ታሳሪዎች ከመደበኛ መኖሪያ አካባቢያቸውና ከመደበኛ እስር ቦታዎች ውጭ ጭምር በመታሰራቸው ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን እንኳን ለማወቅ መቸገራቸውን አስረድቷል።

". . . የፌደራል ሆነ የክልል የፀጥታ ኃይሎች ተጠርጣሪዎችን ከወንጀል ምርመራ በፊት ከማሰር፣ ጋዜጠኞችን በስራቸው ምክንያት ከማሰር እና ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ውጭ ሰዎችን ከማሰር ሊታቀቡ ይገባል። በማናቸውም አይነት ሁኔታ የታሰሩ ሰዎች ሁሉ ቤተሰቦቻቸው ወዲያውኑ እንዲያውቁ እንዲደረግና ወደ ፍ/ቤትም ሊቀርቡ ይገባል” ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

ከሰሞኑ በጀርመን፣ በቤልጂየም፣ በጣሊያን፣ በፖርቹጋል፣ በስፔን እና በስዊድን እንዲሁም በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በአውስትራሊያ ባሉ የአውሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) ተከስቷል። በእነዚህ ሀገራት ከ100 በላይ የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ(Monkeypox) መገኘቱ ተገህጿል። እስራኤል እና ስዊዘርላንድም የመጀመሪያዉን የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) በሽታ ሪፖርት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ፤ በኢትዮጵያ ከፍተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የተደራጀ ቡድን ሊቋቋም እንደሆነ አሳውቋል። የሚቋቋመው ግብረ ሃይል ከህክምና፣ ፎረንሲክ፣ መረጃና ሌሎች ተቋማት የሚውጣጡ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሀረር ማኅበረሰቦች የሸዋል ኢድን በመቻሬ ሜዳ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። በዚህ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሀረሪ ባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ማንችስተር ሲቲ የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ ከፍ አድርገው ሲያነሱ ባለፉት አምስት አመታት ለአራተኛ ጊዜ በፔፕ ጋርድዮላ እየተመሩ የሊጉን ዋንጫ ማሸነፍ ችለዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
11.2K viewsedited  19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 21:59:12 #የዛሬ (ግንቦት 13/2014)

ጤና ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር 2,898 አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመቅጠር ማስታወቂያ ቢወጣም አመልካቾች በወጥነት እንዳላመለከቱ በተደረገ ክትትል ታውቋል። በአዲስ አበባ ለ161 ጠቅላላይ ሀኪሞች ቅጥር ወጥቶ ለመቀጠረ ያመለከቱት 2,300 ሲሆኑ በተቃራኒው በሶማሌ እና አፋር ክልል ለጠቅላላ ሀኪሞች የስራ ቅጥር ቢወጣም #ምንም አመልካች ጠቅላላ ሀኪም ለማግኘት አልተቻለም ተብሏል።

የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል። በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር አዲስ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ይህም 130 ቢሊዮን ብር በላይ ከሚፈጀው ከህዳሴው ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ሀገራዊ ፕሮጀክት ይሆናል ተብሏል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ እና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በሙሉ በቀጣይ ዓመት ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል። የዞኑ ትምህርት መምሪያ ተማሪዎቹ በቀጣይ ዓመት ለሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ምክር ቤቱ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በቦርድ እንዲመራም ወስኗል። በዚህም ለባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል። የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
12.8K viewsedited  18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 20:37:05
#SomaliRegion

የሶማሌ ፖሊስ ኮሚሽን በተለያየ ግዜ የመንግስት አገልግሎት በሚሰጡ የኢትዮ ቴሌኮም እና የመብራት መስመሮችን በመቆራረጥ ፣በመሸጥ፣ በመመሸሸግ እና በመግዛት አባሪ ተባባሪ የነበሩ 16 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
18.1K viewsedited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 18:10:56
#ጥቆማ!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA) ጋር በጋራ ተግባራዊ እያደረገው የሚገኝው የኢኖቬሽን ለልማት ፕሮግራም በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ወይም ዲጂታል ዘርፍ ወደ ምርት እና አገልግሎት የሚቀየሩ ኢኖቬቲቭ የቢዝነስ ሀሳቦችን አወዳድሮ ለመሽለም ጥሪ አቅርቧል።

አመልካቾች ከዚህ በታች ያለውን ድህረ ገጽ በመጠቀም ያመልክቱ። http://registration.mint.gov.et/

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.5K viewsedited  15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ