Get Mystery Box with random crypto!

የአፈር አሲዳመነት አምራች በሚባሉት ክልሎች ላይ በስፋት መከሰቱ ተጠቆመ። የአፈር አሲዳመነት አም | TIKVAH-MAGAZINE

የአፈር አሲዳመነት አምራች በሚባሉት ክልሎች ላይ በስፋት መከሰቱ ተጠቆመ።

የአፈር አሲዳመነት አምራች በሚባሉት ክልሎች ላይ በስፋት መከሰቱ በምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር ነገር ነው።

የግብርና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው፦

በኦሮሚያ ክልል በ14 ወረዳዎች 1.7 ሚሊዬን ሄ/ር መሬት፤

በአማራ ክልል ለእርሻ አገልግሎት ከሚውለው 4.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 1.2 ሚሊዬን የሚሆነው፤

በደቡብ ክልል ከሚታረሰው የእርሻ መሬት 44 በመቶ የሚሆነው እንዲሁም፤

በሲዳማ ክልል አጠቃላይ ካለው የመሬት ስፋት 95 ሺህ ሄ/ር የሚሆነው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነው ተብሏል፡፡

አሁን ላይ በመንግስት በኩል ያለው የኖራ አቀርቦት በቂ ባለመሆኑ መንግስት ኖራ በብዛት አንዲመረት የግል ባለሀብቶችን ወደ ዘርፉ በሚኒስቴሩ በአማራጭ መፍትሔነት ተይዟል።

በተጠማሪም ኖራ የሚገኝባቸው ቦታዎች ላይ የፀጥታ ችግር እንዳይኖር የማድረግ እንዲሁም አሲዳማነት የሚታይባቸው ቦታዎችን በጥናት በመለየትና ኖራ የሚመረትባቸው ቦታዎች አንዲቃራረቡ በማድረግ ለትራንሰፖርት የሚወጣውን ከፍተኛ ወጭም መቀነስ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot