Get Mystery Box with random crypto!

በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የሕፃናት የጭንቅላት ቀዶ ሕክምና ማዕከል እየተቋቋም ነው በአዲስ አበ | TIKVAH-MAGAZINE

በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የሕፃናት የጭንቅላት ቀዶ ሕክምና ማዕከል እየተቋቋም ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር በሚገኘው ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የሕፃናት የጭንቅላት ቀዶ ሕክምና " Pediatrics Neurosurgery" ህክምና ማዕከል እየተቋቋመ መሆኑ ተገለፀ።

ማዕከሉ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ከReach Another Foundation ጋር በመተባበር ባለ አራት ፎቅ ህንፃ በዘመናዊ መልኩ በማደስ እየተቋቋመ መሆኑን የፋውንዴሽኑ ዳይሬክተር ዶ/ር ያዕቆብ ሰልማን ገልፀዋል።

የማዕከሉ እድሳት ሲጠናቀቅ በአጠቃላይ 65 አልጋዎች የሚኖሩት ሲሆን ለማዕከሉ የሚያስፈልጉ የህክምና መሳሪያዎች ግዥ የተጠናቀቀ በመሆኑ በሚቀጥሉት አምስት ወራት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን እየተሰራ ነው ተብሏል።

@tikvahethmagazine