Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና መንኮራኩሯ ማንም ሞክሮ በማያውቀው የጨረቃ ክፍል ማረፉን አስታወቀች ቻይና ቻንግ 6 የተበለ | TIKVAH-MAGAZINE

ቻይና መንኮራኩሯ ማንም ሞክሮ በማያውቀው የጨረቃ ክፍል ማረፉን አስታወቀች

ቻይና ቻንግ 6 የተበለው መንኮራኩሯ እሑድ ጥዋት ማንም ሞክሮ በማያውቀው በደቡብ ዋልታ-አይትከን ማረፉን የሀገሪቱ ብሔራዊ የጠፈር አስተዳደር (ሲኤንኤ) አስታውቋል።

የዛሬ ወር ገደማ ጉዞ የጀመረው መንኮራኩር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ውድ ድንጋይ እና አፈርን ለመሰብሰብ ያለመ ሲሆን በደቡብ ዋልታ ላይ ካለው ግዙፍ ጉድጓድ ውስጥ የተወሰኑትን የጨረቃን ጥንታዊ አለቶች ማውጣት እንደሚችል ተነግሯል።

መንኮራኮሩ ምቹ የሆነ ቦታ ለማረፍ በሚያደርገው ጥረት መሰናክሎችን በመለየት መንቀሳቀስ የሚያስችለው ቴክኖሎጂ እና እንደጨለማው ሁኔታ የሚቀያየር ብርሃን የተገጠመለት መሆኑን ተዘግቧል።

Credit: Xinhua, BBC CNN

@TikvahethMagazine