Get Mystery Box with random crypto!

ወላጆች ከጤና ተቋም ውጪ የሚወለዱ ሕፃናትን ለሲቪል ምዝገባ እንዲያሳውቁ ሊገደዱ ነው ከጤና ተቋ | TIKVAH-MAGAZINE

ወላጆች ከጤና ተቋም ውጪ የሚወለዱ ሕፃናትን ለሲቪል ምዝገባ እንዲያሳውቁ ሊገደዱ ነው

ከጤና ተቋም ውጪ የሚወለዱ ሕፃናትን ወላጆች ለሲቪል ምዝገባ ጽሕፈት ቤት እንዲያስታውቁ የሚያስገድድ ረቂቅ ሕግ ለፓርላማ መቅረቡን ሪፖርተር አስነብቧል።

ሕጉ በዝቅተኛው እርከን ላይ ያለው የመዋቅር ወይም የጤና ባለሙያ አግባብ ያላቸውን መረጃዎች የያዘ ቅጽ ሞልቶ፣ ውልደቱ የተከሰተበት ቦታ ለሚገኝ የሲቪል ምዝገባ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ወላጆች እንዲያሳውቁ ያስገድዳል ተብሏል።

ረቂቅ አዋጁ በርካታ ማሻሻያዎች ሲደረግበት በሥራ ላይ ባለው አዋጅ የሲቪል ምዝገባ ቦታ በመደበኛ መኖሪያ ቦታ የሚለውን አሁን ሁነቱ በተከሰበት ቦታ እንዲሆን በማድረግ፣ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሲቪል ምዝገባን እንዲያደርጉ እንደሚፈቅድ ተገልጿል።

በረቂቁ አዋጅ አስመዝጋቢው አካል ለዘገየበት በቂ ምክንያት በማስረጃ አስደግፎ ካላቀረበ በስተቀር፣ ልደትን በ90 ቀናት ሞትን በ50 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ እንዳለበት ተደንግጓል፡፡ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳያስመዘግቡ መቆየት የተከለከለ እንደሆነም ነው በረቂቁ የተብራራው።

@TikvahethMagazine