Get Mystery Box with random crypto!

የድሬዳዋ አከባቢ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ብድር እና የቁጠባ አገልግሎት ተጀመረ ካ | TIKVAH-MAGAZINE

የድሬዳዋ አከባቢ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ብድር እና የቁጠባ አገልግሎት ተጀመረ

ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ አ.ማ እና ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የድሬዳዋ እና አጎራባች አከባቢዎችን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ብድር እና ቁጠባ አገልግሎቶችን በጋራ አስጀመሩ።

የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ ለመሆን የድሬ ቁጠባ እና ብድር ተቋም ደንበኞች (Dire MFI) የተሰኘውን መተግበሪያ በማውረድ ወይንም በአጭር ፅሁፍ (USSD) *914# በመደወል መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በዚህም የደንበኞችን የመበደር አቅም በፋይናንሻል እና ፋይናንሻል ነክ ያልሆኑ መረጃዎችን መተንተን እና መመዘን የሚያስችል ቴከኖሎጂ በመጠቀም አነስተኛ እና የአጭር ጊዜ ዲጂታል ብድር አገልግሎቶች ስለመመቅረባቸውም ነው የተገለፀው።

@tikvahethmagazine