Get Mystery Box with random crypto!

ከአፍሪካ በየአመቱ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚተመን ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ እንደሚወጣ አዲስ ሪፖርት | TIKVAH-MAGAZINE

ከአፍሪካ በየአመቱ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚተመን ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ እንደሚወጣ አዲስ ሪፖርት አመለከተ

ከአፍሪካ ሀገራት በየአመቱ በ10 ቢሊዮን ዶላር የሚተመን ወርቅ በህገወጥ መንገድ እንደሚወጣ እና አብዛኛው የህገወጥ ወርቅ ንግድ መዳረሻ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት መሆኑን አዲስ ሪፖርት አመለከተ።

መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ያደረገው ስዊስሳይድ የተሰኘው የእርዳታ እና ልማት ቡድን ባወጣው በዚህ ሪፖርት በ2022 ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወይም ከ435 ሜትሪክ ቶን በላይ የሚገመት ወርቅ ከአህጉሪቱ በህገወጥ መንገድ መውጣቱ ተመላክቷል።

ሪፖርቱ ከአፍሪካ የሚወጣው የህገወጥ የወርቅ ንግድ ዋና መዳረሻ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ቱርክ እና ስዊዘርላንድ መሆናቸውን ሲያመለክት የአህጉሪቱን የወርቅ ንግድ ተዋናዮች ላይ ጫና በመፍጠር የአቅርቦት ሰንሰለቶችን የበለጠ ግልፅ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

@tikvahethmagazine