Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Freeseminar
Cloudbridge
Traininginstitute
Cryptocurrency
Аирдроп
Tikvahtechteam
Techdailly
Attention
Cbdc
Cryptocurrencies
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.51K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 259

2022-05-21 16:00:06
አዲሱ ''ጫካ ፕሮጀክት'' ምንድን ነው?

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር አዲስ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ይህም 130 ቢሊዮን ብር በላይ ከሚፈጀው ከህዳሴው ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ሀገራዊ ፕሮጀክት ይሆናል ተብሏል።

ይህ በመዲናዋ በየካ ክፍለከተማ በየካ ተራራ ላይ የሚገነባው አዲሱ ቤተመንግሥት በ503 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል ተብሏል። አምስት ወረዳዎችንም የሚነካ ሲሆን በውስጡም የአዳራሽ፣ የሰው ሰራሽ ሀይቅ፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የመንገድ ጨምሮ ሌሎች ግንባታዎችን ያካትታል።

በግንባታው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚፈናቀሉ ሲሆን ሆኖም ነዋሪዎቹ ቤተ መንግሥቱ የሚታነፅበት አካባቢ ካለው ደረጃ ጋር የሚስማማ ከሆነ በመሬታቸው ላይ የራሳቸውን ንብረት እንዲያለሙ ዕድል ይሰጣቸዋል ተብሏል።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት መንግስት የተወሰነውን ወጪ የሚሸፍን እንደሚሆን ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በአካባቢው 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ መገንባት የጀመረ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ ተሰርቶ ተጠናቋል። የመንገድ ግንባታው ብቻውንም 15 ቢሊዮን ብር ይፈጃል ተብሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዲሱን የቤተመንግሥት ግንባታ “ጫካ ፕሮጀክት” ብለው የሰየመው ሲሆን አዲስ የሚገነባው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አካል የሆኑ ሦስት ሰው ሰራሽ ሀይቆች ግንባታን በውስጡ ይዟል።

በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚንስትር መኖሪያና ጽ/ቤት ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው የምኒልክ ቤተ መንግሥትን በአንድ ቢሊዮን ብር እድሳት ላይ ካለው የኢዮቤልዩ ቤተ-መንግስት ጋር ወደ ብሔራዊ ሙዚየምነት ሊቀየር ታስቧል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
26.1K viewsedited  13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 15:57:21
ውብ በሆነ መልክ በመረጡት ፎቶ እና ጥቅስ በእንጨት እና ቆዳ ላይ በተለያየ ሳይዝ ለማሰራት ከፈለጉ በዚ 0927840730 ይዘዙ።
ዋጋ እና ለበለጠ መረጃ...
#share
#like
#join
@kiyaengraving
21.8K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 15:57:21
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+Zhm6yWqPh7U0N2E0
21.1K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 15:02:06
#Update: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህንፃ ቀለማት ስታንዳርድን (Brand ) አጥንቶ ለውይይት ይፋ አድርጓል። ለከተማዋ የሚስማሙ 13 አይነት ቀለማት ተለይተዋል ሲል ነው ያስታወቀው፡፡

ለከተማዋ በብራንድነት ከተመረጡት ቀለማት መሃከል የህንፃ ባለንብረቶች የሚመርጡትን ወስደው የመጠቀም መብት ያላቸው ሲሆን ይህ አሰራር በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክ/ከተሞች ተጀምሮ ወደ ትግበራ ገብቷል ብሏል፡፡

ፎቶ: የተመረጡት ቀለማት

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
22.0K viewsedited  12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 13:06:35
#WeeklyUpdate

ባሳለፍነው ሳምንት 102 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 14 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር የወጭ ፣ በድምሩ 116 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹ መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 30 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ 18ነጥብ 7 ሚሊዮን እና 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.5K viewsedited  10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 13:02:56
የአፍሪካ ልማት ባንክ የምግብ እጥረትን ለመከላከል የሚውል 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር አጸደቀ፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ በአኅጉሪቱ በሚገኙ ሀገራት የምግብ እጥረት እንዳይከሰት ለመከላከል ያስችላል ያለውን 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ያጸደቀው ድጋፍ በዩክሬን እና በሩስያ ጦርነት የተከሰተውን የአቅርቦት እጥርት ለመሸፈን ነው ብሏል።

ድጋፉ 30 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እህል እንደሚገዛበት ተገልጿል። ድጋፉ ከሩስያ እና ከዩክሬን ወደ አፍሪካ የሚገቡትን ስንዴ፣ ቦቆሎና አኩሪ አተር አቅርቦትን የሚተካ መሆኑ ተመልክቷል።

በተጨማሪም አሁን የጸደቀው ድጋፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረግ ጥረትን ለማገዝና ለአርሶ አደሮች ምርጥ ዘር ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ባንኩ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
21.6K viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:08:37
የአዲስ አበባ ፖሊስ 1ሺሕ 196 የፖሊስ አባላት ዛሬ አስመርቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለአራት ወር ከ15 ቀናት ያሰለጠናቸውን 1ሺሕ 196 የፖሊስ አባላት በዛሬው ዕለት አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 789 ወንዶች ሲሆኑ 407 ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.7K viewsedited  08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 10:52:24
#እንድታውቁት

ዛሬ በ13/09/2014 ዓ.ም ለጎንደር ከተማ ከእንጨት ወደ ኮንክሬት ፖል ለመቀየር በሚሰራው ስራ ጎንደር መጋቢ መስመር ከ2:30-900 ሰዓት የሚቋረጥ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጎንደር ዲስትሪክት ገልጿል።

በዚህም የሚቋረጥባቸው አካባቢዎችም፦

- አዘዞ ት/ቤት አካባቢ፣
- አባሳሙኤ ኮንዶሚኔም አካባቢ፣
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በከፊል፣ ጂቲዜድ አካባቢ፣
- ቀበሌ 16 በከፊል፣
- ቀበሌ 14፣15፣1፣2 መሉ በሙሉ እና 3 በከፊል መሆኑ ነው የተገለጸው።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.0K viewsedited  07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 10:45:35
የአዲስ አበባ ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ እንዲሆን ተወስኗል በሚል የወጣውን መረጃ አስተዳደሩ አስተባበለ።

በከተማው ለሚገኙ ሕንፃዎች ቀለማቸው ወጥ የሆነ ስታንዳርድ ለማዘጋጀት ላለፈው አንድ ወር ጥናት ተደርጎ አብዛኞቹ ሕንፃዎች ቀለማቸው ግራጫ ቀለም ያላቸው መሆኑን መረጋገጡንና የአዲስ አበባ ከተማ ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ እንዲሆን መወሰኑ የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ መናገራቸው ተዘግቦ ነበር።

ሆኖም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ ይህንን ጉዳይ አስተባብለዋል። እስካሁን ድረስ የከተማዋ ህንጻዎች ቀለም ምን አይነት ይሁን የሚለው ጉዳይ ለውይይት ቀረበ እንጂ የከተማ አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳላሳለፈ ለኢፒድ ገልጸዋል፡፡

ከተማዋ ላይ አንድ አይነት ቀለም ብቻ ለቀለም ቅብ ሥራ ያስፈልጋል የሚል እሳቤ መያዝ እንደሌለበት የተናገሩት ኃላፊ፤ ለአስፈላጊው ህንጻና አካባቢ የሚመጥን ዝብርቅርቅ ያልሆነና ለዓይን የሚማርኩ ቀለማትን የያዘ ስታንዳርድ እንደሚኖረን ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።

ውሳኔው የከተማው ነዋሪ ምክርና ስምምነት ያስፈልገዋል፤ በሂደቱ ላይም በርካታ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉና ተወያይቶ መግባባት ላይ መድረስን እንደሚጠይቅ ኃላፊው ጠቁመዋል።

ኃላፊው ጉዳዩን ''በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው'' በሚል የገለጹ ቢሆንም የዚህ መረጃ ምንጭ ግን ሪፖርተር ጋዜጣ በረቡዕ ዕትሙ የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ አቶ ስጦታው አካለን ጠቅሶ ያወጣው ነው።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
21.4K viewsedited  07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 10:45:04
የት ለመማር ወሰኑ?

በ Software Engineering እና በ Information Technology and Systems በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቶን ለመማር ወደ #ቢትስኮሌጅ ቢመጡ አብዝተው ያተርፋሉ።

በ4 ዓመት ውስጥ በዲግሪ ብቻ ሳይሆን ብቁ ሰራተኛ ሆነው ጭምር ይመረቃሉ።

ጥራታቸውን የጠበቁና የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያግዙ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን፣ በዘመናዊ መልክ የተደራጁ መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተመፃህፍት፣ የኮምፒዩተር ላብራቶሪዎች እና እጅግ ዘመናዊ የአይቲ መሠረተ ልማት #በቢትስኮሌጅ የተሟሉ ናቸው።

ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ፦

ድረ ገጽ www.bitscollege.edu.et

0982 363636 / 0978028655

#BITSCollege
20.8K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ