Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.56K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 253

2022-05-14 16:43:32
በደደር ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወደመ

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ደደር ከተማ ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ለግንቦት 6 አጥቢያ ከሌሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በአደጋው በደደር ከተማ የገበያ ስፍራ በተነሳ የእሳት አደጋ ሰባት የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥና የሕንፃ መሳሪያ መደብሮች የቃጠሎው ሰለባ ሆነዋል።

ህብረተሰቡ እሳቱን ለማጥፋት ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ ወደ ሌሎች ሱቆችና አካባቢዎች ሳይዛመት እና ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ ዛሬ ጠዋት 12፡30 አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋሉ ነው የተነገረው።

እሳቱ የተነሳበትን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የዞኑ ፖሊስ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ መግለጻቸውን የዘገበው ፋብኮ ነው።

@tikvahethmagazine
14.0K viewsedited  13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 15:56:02
በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ በቦንጎታ ቀበሌ አንዲት እናት ሶስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች።

በወላይታ ዞን በሆቢቻ ወረዳ በቦንጎታ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ አበበች ጀንበሬ ሦስት ልጆችን ያለምንም ጤና ችግር በሰላም መገላገላቸው ተገልጿል።

የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል እንዳሉት በጤና ጣቢያቸዉ ይህ የመጀመሪያ ክስተት መሆኑን ጠቅሰው አሁን ላይ ልጆቹና የልጆች እናት ፍፁም ጤነኛ መሆናቸውንም የዞኑ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethmagazine
14.4K viewsedited  12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 15:55:46
የሊንኮቹን ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+Zhm6yWqPh7U0N2E0
13.4K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 15:55:28
ጥሩ የሚባል ያገለገለ መኪና ለማግኘት የተለያየ አማራጮችን ማየት ይጠበቅባችኋል። አሁንም መኪና እየፈለጉ ከሆነ ከፍላጓታችሁ ጋር የሚጣጣም አዲስ እና ያገለገሉ መኪኖች ከፎቶ እና ሙሉ መረጃ ጋር አሰባስበን ይዘናል።

የሚፈልጉትን መኪና የሚያውቁ ከሆነ ብዙ የመኪና ስብስብ ያለውን ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

የሚፈልጉት መኪና ከታች ካለው ማስፈንጠሪያ በስተጀርባ ነው።

https://t.me/mekina

@mekina online መኪና መሸጫ
ቀላል ግን ውጤታማ
13.1K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 13:29:18
እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ።

በየጊዜው እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ሰለባ ላለመሆን ዜጎች ማንነታቸው ከማይታወቁ ግለሰቦች ጋር በበይነመረብ በሚደረጉት ግንኙነት ላይ ጥንቃቄ እንዲወስዱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጥምር ግብረ- ኃይል አሳስቧል።

የማጭበርበር ወንጀሎቹ በዋናነት የሚፈጸሙት በውጭ ሀገር የሚኖሩ፣ በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች መሆኑንም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

ኢትዮጵያዊያን በስፋት የሚጠቀሟቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች ማለትም ፌስቡክ፣ ኢ-ሜይል፣ ዋትስአፕ፣ ቴሌግራም፣ ኢንስታግራም፣ ኢሞና ቫይበርን በመጥለፍና ወዳጅ መስሎ በመቅረብ ወንጀሎቹ እንደሚፈጸሙ ከተደረገው ክትትል ማወቅ እንደተቻለም ተገልጿል።

ግለሰቦቹ የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን ተጠቅመዉ ወንጀሉን እንደሚፈጽሙ የተገለጸ ሲሆን በተለይ ዉድ እቃዎችን በማስመሰል እቃው ለተላከበት ክፍያ የሚሆን ገንዘብ በባንክ ገቢ እንዲያደርጉ አድርገው የገባዉን ገንዘብ ወዲያውኑ ወጪ በማድረግ ወንጀሉን ይፈጽሙታል ብሏል መግለጫው፡፡

በዚህ የማጭበርበር ድርጊቶች ላይ የተሰማሩት ግለሰቦች በተጨማሪም ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ማተም፤ ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀትና መገልገል እንዲሁም የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉር ወንጀል ጭምር ላይ ተሳታፊ ሆነዉ ተገኝተዋል ተብሏል።

በተደረገው ክትትል የውጭ አገር ዜጎች እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ተጣርቶባቸዉ በማረሚያ ቤት የሚገኙ፤ ከአገር እንዲወጡ የተደረጉ እና ጉዳያቸው በምርመራ ሂደት ላይ የሚገኙም እንዳሉ ተጠቅሷል፡፡

ሙሉ መግለጫው https://telegra.ph/ETH-05-14

@tikvahethmagazine
10.7K viewsedited  10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 13:09:24
በእሳት አደጋ ምክንያት የንብረት ጉዳት ለደረሰባችው በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ተደረገላቸው።

በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጅቡቲ ከተማ ፒካዱስ ልዩ ስሙ ፒኬ 12 አካባቢ በቅርቡ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ በንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ኢትዮጵያዊያንን ማቋቋሚያ የሚውል 3.1 ሚሊዮን በላይ የጅቡቲ ፍራንክ በኤምባሲው እና በህብረተሰቡ አስተባባሪነት ተሰብስቦ ድጋፍ ተደርጓላቸዋል።

@tikvahethmagazine
11.0K viewsedited  10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:46:19
#Silte

ዛሬ በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ለዝናብ እጥረት የሚሰገድ ሰላት (ሰላቱ ኢስቲስቃዕ) መሰገዱን የዞኑ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethmagazine
12.4K viewsedited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:45:45
#Wolkite

የወልቂጤ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ አበበ አሰፋን የከተማው ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አዲሱ ከንቲባም በምክርቤቱ ቀርበው ቃለ መሀላ መፈጸማቸው ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
11.3K viewsedited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:45:29
Sejoy Blood pressure

0911284606
    ሀኪሞን በእጆ , ጤናዎትን በየግዜዉ ሳይጨነቁ በፈለጉበት ቦታ ና ግዜ ይወቁ
የደም መጠን ሚለካ 
የልብ ምት መጠንን ሚለካ
ሰለደም ግፊት አጠቃላይ መረጃ ሚሰጥ
ዋጋ- 1900  birr
Bole medanialem
10.3K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:45:18
የአንፖል ካሜራ lamp camera

በከፍተኛ ጥራት የሚቀርፅ Full HD ካሜራ የተገጠመለት የአንፖል ከስልኮ ጋ በ app በማገናኘት ማንኛውንም አይነት ክትትል የሚያደርጉበት የአንፖል መሰኪያ ላይ በመግጠም ብቻ ማንኛውንም እንቅስቃሴ የሚቃኙበት ለሱቅ፣ ለቤት፣ የልጆችዎን እንቅስቃሴ ያለሃሳብ የሚቃኙበት እንዲሁም አካባቢዎን ከስርቆት የሚከላከሉበት የራሱ ሳውንድ ሪከርድ እንዲሁም ሚሞሪ የሚቀበል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል።

ዋጋውን ዋጋውን እና ሙሉ መረጃውን ከታች ባስቀመጥነው ሊንክ ገብተው ይመልከቱ

https://t.me/joinchat/Um_xfu9NW05k6L77
https://t.me/joinchat/Um_xfu9NW05k6L77

አድራሻ፦ ልደታ ፌዛክ የገበያ ማእከል 1ኛ ፎቅ ላይ
ስልክ:- 0913979989 0900664655

 Inbox @Tebe_mart09    
11.4K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ