Get Mystery Box with random crypto!

#ጥንቃቄ: በቦሌ ክ/ከተማ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ | TIKVAH-MAGAZINE

#ጥንቃቄ: በቦሌ ክ/ከተማ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

በዛሬው ዕለት ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የክረምት ወር መግባቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች 32 ሺሕ አባወራዎች ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡ መሆናቸው ሲገለፅ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ልደታ፣ ቂርቆስና አራዳ ክፍለ ከተሞች በተደጋጋሚ ጎርፍ የሚያጠቃቸውና በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች መሆናቸው በጥናት ተለይተው ታውቀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት የለየ ሲሆን ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ መልእክቱን አሰተላልፏል፡፡

@TikvahethMagazine