Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቤሩት አል ሃሪሪ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ምን | TIKVAH-MAGAZINE

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቤሩት አል ሃሪሪ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ምን ገጠመው?

የሊባኖስ አቬዬሽን ባለስልጣን “ቴል አቪቭ” የተሰኘ መለያ ያለበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቤይሩት ሲደርስ ተቃውሞ ማሰማቱን የሀገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የሀገሪቱ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን ቤይሩት ያረፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 787-9 አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ ከመመለሱ በፊት ምልክቱን እንዲሸፍን አድርጓል።

በተጨማሪም፥ አውሮፕላኖች በቤይሩት ከመድረሳቸው በፊት ሊባኖስ "ጠላቴ ናት" ከምትላት እስራኤል ጋር የተያያዘ ምንም አርማ እንደሌለ ማረጋገጥ እንዳለበት አሳስቧል።

ሊባኖስ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ኖሯት የማያውቅ ሲሆን እንደ ጠላት ሀገር የሚተያዩ ናቸው።

ሁለቱ ሀገራት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመሀከለኛው ምስራቅ ባለው ግጭትና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን የሆነው 'ሒዝቦላ' ጋር በሚያደርጉት ውጊያ ቀጠናው እና ሁለቱ ሀገራት የተካረረ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።

አየር መንገዱ አዳዲስ አውሮፕላን ሲያስገባ አውሮፕላኖቹ የመጀመሪያ በረራ ያደረጉበት የመጀመሪያው ከተማ ስም በውጨኛው ክፍል ላይ ይጻፋል። ይህም የአየር መንገዱ ልምድ ነው።

በዚህ መሰረትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ4 አመት በፊት ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኑን ወደ መስመር ሲያስገባ ቅድሚያ የበረረበትን የከተማ ስያሜ ' ቴል አቪቭ ' የሚል የሚል ስያሜ ሰጥቶት ነበር።

@TikvahethMagazine