Get Mystery Box with random crypto!

በደደር ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወደመ በም | TIKVAH-MAGAZINE

በደደር ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወደመ

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ደደር ከተማ ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ለግንቦት 6 አጥቢያ ከሌሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በአደጋው በደደር ከተማ የገበያ ስፍራ በተነሳ የእሳት አደጋ ሰባት የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥና የሕንፃ መሳሪያ መደብሮች የቃጠሎው ሰለባ ሆነዋል።

ህብረተሰቡ እሳቱን ለማጥፋት ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ ወደ ሌሎች ሱቆችና አካባቢዎች ሳይዛመት እና ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ ዛሬ ጠዋት 12፡30 አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋሉ ነው የተነገረው።

እሳቱ የተነሳበትን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የዞኑ ፖሊስ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ መግለጻቸውን የዘገበው ፋብኮ ነው።

@tikvahethmagazine