በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ በቦንጎታ ቀበሌ አንዲት እናት ሶስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች። በወላይታ ዞን በሆቢቻ ወረዳ በቦንጎታ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ አበበች ጀንበሬ ሦስት ልጆችን ያለምንም ጤና ችግር በሰላም መገላገላቸው ተገልጿል። የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል እንዳሉት በጤና ጣቢያቸዉ ይህ የመጀመሪያ ክስተት መሆኑን ጠቅሰው አሁን ላይ ልጆቹና የልጆች እናት ፍፁም ጤነኛ መሆናቸውንም የዞኑ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገልጿል። @tikvahethmagazine 14.4K viewsedited 12:56