Get Mystery Box with random crypto!

በጎፋ ዞን ቡልቂ ከተማ የ16 አመት ታዳጊ የደፈሩ 2 ግለሰቦችና ታዳጊዋ እንድትደፈር ያደረገች ሴት | TIKVAH-MAGAZINE

በጎፋ ዞን ቡልቂ ከተማ የ16 አመት ታዳጊ የደፈሩ 2 ግለሰቦችና ታዳጊዋ እንድትደፈር ያደረገች ሴት በፅኑ እስራት ተቀጡ

በጎፋ ዞን በቡልቂ ከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሱ 2 ግለሰቦችና ታዳጊዋ እንድትደፈር በማመቻቸት በአባሪነት የተከሰሰች አንዲት ሴት በጽኑ እሥራት መቀጣታቸውን የከተማው ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

1ኛ ተከሣሽ የሆነው አቶ በቃኃኝ ባቤና እና 2ኛ ተከሣሽ አቶ አበራ ሚኖታ የተባሉት ግለሰቦች የ16 ዓመቷን ታዳጊ በመድፈር ክስ ሲቀርብባቸው 3ኛ ተከሣሽ የሆነችው ወ/ሮ ብርቱኳን ከበደ ደግሞ በራሷ ምግብ ቤት በዕቃ አጣቢነት ቀጥራ የምታሠራትን ይህቺን ታዳጊ ሰራተኛ ያለፍቃዷ 1ኛ ተከሣሽ እንዲደፍራት በማመቻቸት መከሰሷ ተገልጿል።

የከተማው ፖሊስ የተፈፀመውን ወንጀል መነሻ በማድረግ ምርመራ አድርጎ ያጠናቀቀውን የምርመራ መዝገብ ለከተማው ዓቃቤ ሕግ አቅርቦ ዐቃቤ ሕግም የምርመራ መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ፍርድ ቤቱ 1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች ተበዳይን ያለፍላጎቷ አስገድደው ስለመድፈራቸው እና 3ኛ ተከሣሽም ተበዳይ በ1ኛ ተከሣሽ ያለፍላጎቷ እንድትደፈር ምቹ ሁኔታ መፍጠሯን በማስረጃ አረጋግጧል።

በዚህም የቡልቂ ከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተከሣሾቹን ማቅለያ እና የዐቃቤ ሕግን ማክበጃ ሀሳቦችን ከመረመረ በኋላ

#1ኛ ተከሣሽ አቶ በቃኻኝ ባቤና በ9 ዓመት ጽኑ እሥራት፤
#2ኛ ተከሣሽ አቶ አበራ ምኖታ በ7 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት፤
#3ኛ ተከሣሽ የሆነችው ወ/ሮ ብርቱኳን ከበደ በ6 ዓመት ጽኑ እሥራት እንዲቀጡ ወስኗል።

@TikvahethMagazine