Get Mystery Box with random crypto!

' በቀጣይ የበልግ ዝናብ ወቅት በሶማሌ ክልል ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንዲሁም በሌሎች ክልሎች | TIKVAH-MAGAZINE

" በቀጣይ የበልግ ዝናብ ወቅት በሶማሌ ክልል ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንዲሁም በሌሎች ክልሎች በመቶ ሺ የሚገመቱ ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ ይችላሉ " OCHA

በኢትዮጵያ በሶማሌ፣ ደቡብ፣ ኦሮሚያ፣ አፋርን ጨምሮ ሌሎችም ክልሎች እስከ ግንቦት ባለው የበልግ የዝናብ ወቅት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ እና ሊፈናቀሉ እደሚችሉ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

በሪፖርቱ መሰረት፦

- በ #ሶማሌክልል፡- በአፍዴር፣ ሊባን፣ ቆራሄ፣ ኤረር፣ ዳዋ፣ ጃራራ፣ ኖጎብ እና ሸበሌ ዞኖች ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጎርፍ በጎርፍ ሊጠቁ ይችላሉ ተብሎ የተገመተ ሲሆን ወደ 773,000 የሚጠጉ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ይጠበቃል።

- በ #ደቡብ፦ 145,000 የሚጠጉ ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ የሚችሉ ሲሆኑ 64,000 ሰዎች ቀደም ሲል በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በመካከለኛው ኢትዮጵያ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሲዳማ ክልሎች ተፈናቅለዋል።

- በ #ኦሮሚያክልል፦ 421,000 የሚገመቱ ሰዎች በጎርፍ ይጠቃሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን በቦረና፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ሀረርጌ እና ምስራቅ ሀረርጌ ወደ 104,000 የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

በ #አፋርክልል፦ 83,000 የሚጠጉ ሰዎች ለጎርፍ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ሲሆን 61,000 ሰዎች በተለያዩ ዞኖች ይፈናቀላሉ ተብሎ ይገመታል።

በ #አማራክልል ፦ ከሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ከኦሮሞ ልዩ ዞን የተፈናቀሉ 3,000 ግለሰቦችን ጨምሮ ወደ 45,000 የሚጠጉ ሰዎች የጎርፍ ተጠቂ ይሆናሉ ተብሎም ተጠቁሟል።

በ #ትግራይክልል፦ 4,000 የሚገመቱ ሰዎች የጎርፍ ተጠቂ ይሆናሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን 1,000 ሰዎች በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ሊፈናቀሉ  ይችላሉ።

የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከሰብአዊ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመሆን ከመጋቢት እስከ ግንቦት የጎርፍ አደጋን ለመከላከል በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና የደቡብ ክልሎች የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራ የሰራ ሲሆን የገንዘብ እጥረት ግን የእርዳታ አቅርቦቱን እየገደበ መሆኑ ተገልጿል።

ፎቶ፦ ፋይል

@TikvahethMagazine