Get Mystery Box with random crypto!

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ20 ከተሞችን የውሃ አገልግሎቶች አሠራር ለማዘመን ስምምነት ተፈራረመ። | TIKVAH-MAGAZINE

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ20 ከተሞችን የውሃ አገልግሎቶች አሠራር ለማዘመን ስምምነት ተፈራረመ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ20 ከተሞችን የውሃ አገልግሎቶች አሠራር የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓትን በማስፈን ለማዘመን ዳፍ ቴክ ሶሻል አይ ሲቲ ሶሉሽን፣ ኢንታፕስ ኮንሰልታንሲ እና ያዮቤ አይሲቲ ሶልሽን ከተባሉ ሦስት ተቋማት ጋር ስምምነት አድርጓል።

የመረጃ አስተዳደር ሥርዓትን ማስፈን የየከተሞቹን ውሃ አገልግለቶች የውሃ ቆጣሪ ንባብ ፣ ገቢ አሰባሰብ ፣ የብድር አስተዳደር፣ የደንበኞች መስተንግዶ፣አጠቃላይ የሂሳብ አያያዝ ሥራንና የሰው ኃይል አጠቃቀምን በዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር ያስችላል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ገልጸዋል።

በሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ከተቃቀፉ 22 ከተሞች በ20ዎቹ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ፕሮጀክቱ በ540 ቀናት ወይም በ18 ወር ጊዜ የሚጠናቀቅ ሲሆን 118.8 ሚሊየን ብር በጀት ተመድቦለታል፡፡

በተመሳሳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ላሊፍቱ አጠቃላይ ልማትና የማማከር አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ጋር የአማካሪ ቅጥር ውል የተፈራረመ ሲሆን አማካሪ ድርጅቱ በደቡብ ክልል ሲራሮ ወረዳ እና በሲዳማ ክልል አዋሳ ዙርያ ባሉ ወረዳዎች ጥናት ያደርጋል ተብሏል።

ጥናቱም፥ በተደጋጋሚ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚጠቁና የውሃ እጥረት ላለባቸው ቀበሌዎች ለትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማት ጨምሮ የውሃ አቅርቦት፣ የአካባቢ ጽደዳትና የግል ንጽህና ደረጃ ግምገማ ጥናት ማካሄድ፣ ሊኖር የሚችል የውሃ አማራጭ የአዋጭነት ጥናት ማከናወን እና አማራጩ የከርሰ ምድር ውሃ ከሆነ የጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ መከታተልን፣ በአዋጭነት ጥናቱ ላይ የተመረኮች ዝርዝር ንድፍ ማዘጋጀትን ያካትታል፡፡

@tikvahethmagazine