Get Mystery Box with random crypto!

Bilal Media & Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication B
የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication
የሰርጥ አድራሻ: @linkbi7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-02-09 19:19:56 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑨↠ Dr. Gustav Weil /ዶ/ር ጉስታቭ ዌይል/ (ጀርመናዊ የምስራቅ ታሪክ አጥኚ /ኦሪየንታሊስት/፣ ደራሲ እና ተርጓሚ)
‹‹ሙሐመድ ለሕዝቦቹ አንጸባራቂ ተምሣሌት ነበር፡፡ ምግባሩ ንጹህ እና ጉድፍ አልባ ነበር፡፡ ቤቱ፣ ምግቡ ሁሉ አስገራሚ ቅለት
የሚታይባቸው ነበሩ፡፡ እጅግ ከመተናነሱ የተነሳ ባልደረቦቹ የተለየ መጠሪያ እንዲያበጁለት እንኳ አይፈቅድም ነበር፡፡ ራሱ መሥራት የሚችለውን ነገር ነገር በአገልጋዮች አያሠራም ነበር፡፡ ለሁሉም ሰው በሁሉም ወቅት መገኘት የሚችል ነበር፡፡ የታመመን ጠያቂ፣ ለሕዝቦቹ የሚያዝን ነበር፡፡ ቸርነቱ እና ለጋስነቱ ዳርቻ አልባ የሆነውን ያክል ለሕዝቡ ደኅንነትም እጅግ ተጨናቂ ነበር፡፡››
History of the Islamic Peoples
31 viewsGlamor, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 16:50:23 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑧ Edward Gibbon /ኤድዋርድ ጊቦን/ (እንግሊዛዊ ጸሐፊ እና የፓርላማ አባል)
‹‹የማሆሜት (ሙሐመድ) መልካም ነፍስ መሳፍንታዊ ጉራን ትጠየፍ ነበር፡፡ የፈጣሪ ነቢይ ሆኖም በተራ ቤተሰባዊ ስራዎች
ሳይቀር ይሳተፍ ነበር፡፡ እሳት ያቀጣጥል፣ ወለል ይጠርግ፣ ወተት ያልብ እና ልብስና ጫማውን በስፌት ይጠግን ነበር፡፡ የባህታዊን
ራስ-ቀጪነት እና ውጤቱን ቢርቅም የዓረቦችን ቅንጦት አልባ አመጋገብ ያለችግር ለመኖር አልከበደውም፡፡ የማሆሜት (ሙሐመድ) ትልቁ ስኬቱ በግልጽ ሞራላዊ ኃይል ላይ የተመሠረተ መሆኑ ነበር፡፡››
☞History of the Saracen Empire, London, 1870
53 viewsGlamor, 13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 07:18:55
እነሆ ከብዙ ጊዜያት በኋላ የሰዎች የሕይወት ተሞክሮ በንባብ እየገለጥን ቆይታ የምናደርግበት የ #VENUE_TALK_SHOW ንባባችን በዚህ ሳምንት ይመለሳል።
በዚህ ሳምንት እንደ አላህ ፍቃድ ከአንድ እንግዳ ጋር እጠብቃችኋለሁ።
እኔ ዝግጅቴን እንዳሰናዳ እናንተ ደግሞ ቻናሉን ለሌሎች መጋበዝ እና ማስተዋወቅ ተሰጥቷችኋል። ቤተሰቦቻችንን አብዟቸው።
#Share_and_Join

@Venuee13
@Venuee13
13 viewsGlamor, 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 23:40:59 ፍሬን የሌለው መኪና እና ኒካህ የሌለው ፍቅር አንድ ናቸው
abu yehya
20 viewsGlamor, 20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 20:03:09 የአብሬት ጉዞ

አብሬት በጉራጌ ዞን በቸሀ ወረዳ የሚገኝ ቀበሌ ሲሆን በአካባቢው በሱፍያው አለም የነበሩ ሸይኾች የነበሩበት ቦታ ነው።

በቦታው በዋናነት የሚታወቀው የአብሬት ሼይኽ (ሰይድ ቡደላ) በመባል በሚታወቁ የሱፍያው ሸይኽ የነበሩበትና ዳዕዋቸውን ሲያካሂዱ የቆዩበት ቦታ ስለሆነ ከሌሎቹ በበለጠ ቦታው ወይም አካባቢው ገኖ ይታወቃል።


የአብሬት ሸይኽ መውሊድ ማክበር
/////////////////////////////////////

በየአመቱ ረጀብ 15 ቀን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ህዝቦች ወደ አብሬት ይጎርፋሉ።

ብዙዎቹ ዘንድ የድሆች ሀጅ በመባልም ይሰየማል ።አብሬት መሄድ እንደ መካ ሲሆን የቁባ ሸይኽ ቀብር ሄዶ መዘየር ደግሞ መዲና ሄዶ የነብዩ صلى الله عليه وسلم መስጂድና ቀብር እንደመዘየር ይቆጠራል በማለት የተጋነነ ምልከታቸውን ሲያንፀባርቁ ይስተዋላል።

እንዲህ አያሉም ሲያዜሙ ይደመጣሉ:_" አብሬት ያናሽ ተብራሸ ወሬ ምር ባይተ የኦድሸ" አብሬትን ያላየ ተበላሽቷል: ወሬ የምን ብሎስ ያወራል"

በጥቅሉ ይህ ቦታ መሄድ ከፍታኛ ረደኤት እና በረከት እንደሚያስገኝ ይታሰባል።ብዙ የተቸገሩ ፣ልጅ ያጡ፣ትዳር አልሳካ ያላቸው፣ስራ አልመቻች ያለው፣በህመም የተቸገሩ ሰዎች እና ሌሎችም ተመሳሳይ ችግር ላይ የወደቁ ሰዎች ወደ ቦታው በማምራት የተለያዩ ነገራቶ ለቁባ ሸይኽ ቀብርና ለአብሬት ሽይኽ ልጆች ስለት ተስለው እንደሚመለሱና በቀጣዩ ጊዜ ደግሞ የተሳሉትን ነገር በመያዝ ወደ ቦታው በማምራት ስለታቸውን ከአሏህ ውጪ ላለ አካል ተፈፃሚ ሲያደርጉ ብዙ አመታቶችን ያስቆጠሩበት የዘውትር ተግባራቸው መሆኑ ይታወቃል።

ቦታው ላይ በረካ አለው ተብሎ ስለሚታሰብ አንዳንዶቹ ወደዚህኛው ቦታ ለብሰው የሄዱትን ልብስ ታጥቦ እጣቢው መሬት ላይ መደፋት የለበትም በሚል እሳቤ ይህ ልብሳቸው የታጠበበት ቆሻሻ ውሃ የሚጠጡ በርካቶች ናቸው።

ብዙ በሽርክ የታጨቁ መንዙማዎችና ተግባረቶች የበዓሉ ዋና ማድመቂያዎች ናቸው።

ቦታው ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ይህ ፀያፍ የሆነው ዚና በተለያዩ ወንበዴ ወንዶችና ሴቶች አማካኝነት ይፈፀማል።እንደውም ይህ ፀያፍ ተግባር በማሰብ ወደ ቦታው የሚያቀኑ ብዙ ከእስልምና እምነት ውጪ ያሉ ብዙዎች መሆናቸው እንደ ቀን ፀሀይ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው።

አንዳንድ አባቶች ከቤታቸው ወደ አጠገባቸው የሚገኝ መስጂድ ገብቶ መስገድ አልችልም እያለ ወደ አብሬት ከአራት _ አምስት ሰአታት ጓዛቸውን ተሸክሞ ሲጓዝ ይስተዋላል።

ይህ ከላይ የጠቀስኳቸው ቦታ ላይ የሚፈፀሙ ተግባራቶች ለግንዛቤ ያክል ጠቀስኳቸው እንጂ እንደ ኢስላም እይታ ይህ በዓል ማክበር ብይኑ ምንድነው የሚለውን መመልከት ብቻውን ተግባሩ የተወገዘ መሆኑ ያስረዳናል።

1/ ከኢስላም ትርጉም ውስጥ " ለአሏህ ፍፁም ታዛዥ መሆንና ላወረደው ህግም (ሸሪዓ) ፍፁም ታዛዥ መሆን ይገኝበታል።

እንዲህ ከሆነ ይህ የአብሬ መውሊድ የሚባለው ነገር አሏህ አዞበታል? ነብያችን صلى الله عليه وسلم መልእክታቸው በሚገባ አድርሰው ሲያበቃ ይህ ተግባር መልእክታቸው ውስጥ አካተውታልን?


እንደሚታወቀው ኢስላም ትንሹም ትልቁ የእለተእለት ተግባራችን በዝርዝር ያብራራ ሲሆን የሽንት ቤት አጠቃቀማችን ሳይቀር በሃዲስ ተብራርቷል።

ይህ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች ተሰብስቦ እና በከፍተኛ ድግስ የሚከበረው ይህ በዓል ኢስላም እንዴት በዝምታ ያልፈዋል?

ነብያችን صلى الله عليه وسلم የጃሂሊያዎች በዓላት ሁሉ ቀርተው ሁለቱ በዓላት እንደ ቀየረልን ሲናገሩ የአብሬት ሸይኽ መውሊድ እውነት መከበር ካለበት ለምን በዝምታ አለፋት።

አላህ سبحانه وتعالى


الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا

ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡

ሲል =_የአብሬት መውሊድ እውነት የእስልምና አካል ከሆነ ለምን መውሊዱ ሳይካተት እምነታቹህ ሞላሁላቹ አለ?

ልብ በል
____
አሏህ እምነታቹህ ሞላሁላቹ ካለ በኃላ አዳዲስ መጤ ተግባራቶች እየጨመሩ ዲን ነው ብለው የሚያከናውኑ ሰዎች አሏህን እያስዋሹ እንደሆነ ሊዘነጉት አይገባም።

አሏህ ሞላሁት እያለ አንተ አአይ ይህ ይቀርሀል እያልክ መባዘን ምን የሚሉት አላዋቂነት ነው?

أَأَنتُمْ أَعْلَمُ أَمِ اللَّهُ

«እናንተ ታውቃላችሁን? ወይንስ አላህ?»

ዲን ላይ የሌለ አዲስ መጤ ነገር ስታመጣ ትልቅ ቅጥፈት እየቀጠፍክ መሆኑ ከግንዛቤ አስገባው።



أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُم مِّنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَن بِهِ اللَّهُ

ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አልሏቸውን?


ወደ አሏህ መዳረስ የምንችለው የአሏህ መልእክተኛን በመከተል እንጂ በተለያዩ ግለሰቦች ፍልስፍና እንዳልሆነ ነብያችን
صلى الله عليه وسلم ከእለታት አንድ ቀን ቀጥተኛ መስመር አሰመሩና ከዳርና ዳሩ ደግሞ የተለያዩ መስመሮች አሰመሩ ከዚያም እንዲህ የሚለው የቁርአን አንቀፅ አነበቡ

وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
↓↓↓→
إن شاء الله


አቡ ሙሀመድ አብዱልናስር መኑር አል_ ጃቢሪይ
↓↓↓↓↓↓→
https://t.me/twhidsunabegegnea
31 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 19:38:39 የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር "ሸይሁል ኢስላም፤ ሙሐመድ ኢብኑ-ተይሚያህ" የሚለው መፅሀፍ #ክፍል_6 በአላህ ፍቃድ እነሆ

#የኖሩበት_ዘመን_ባጭሩ

የተንጣለለው ፅኑው የኺላፋ ስርአት ዛሬ በትላንቱ መልክ የለም፡፡ የተለያዩ አካባቢዎች የራሳቸው ገዢ አላቸው፡፡ ግብፅና ሻም በመምሉካውያን መዳፍ ስር ናቸው፡፡ በቋፍ የነበረው የዐባሳውያን ኺላፋ ባግዳድ ላይ በተታሮች ፈርሷል፡፡ መምሉካውያን የዐባስ ዘሮችን እያስመጡ ስለሚሾሙ የፈረሰው የዐባሳውያን ኺላፋ ለይስሙላ ካይሮ ላይ ቀጥሏል፡፡ እውነተኛው ስልጣን የነበረው ግን በመምሉካውያኑ ሱልጣኖች እጅ ነው፡፡ በራሳቸው በመምሉካውያኑ መካከል ደግሞ የተጧጧፈ የስልጣን ሽኩቻ አለ፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ!

የአውሮጳውያኑ የመስቀል ጦርነት እያባራ ነው፡፡ ከዛሬዋ ሞንጎሊያ አካባቢ የተነሱት ተታሮች ግን በሙስሊሙ ላይ በሰው ልጅ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ እልቂት ፈፅመዋል፡፡ ሰራዊታቸው እየሰለመ፣ አንፃራዊ በሆነ መልኩ ጭፍጨፋቸው እየቀነሰ ቢመጣም አረመኔያዊ ጥቃታቸው ገና አልተገታም፡፡

መምሉካውያኑ ከሞላ ጎደል ለዲን ክብር አላቸው፡፡ ግና በጊዜው ወደተንሰራፋው የሱፍያ መዝሀብ ያዘነበሉ ነበሩ፡፡ በውጭ ከሃዲያን እየተጠቃ ያለው ሙስሊሙ አለም ከውስጥም በቢድዐ እግር ከወርች ተጠፍሯል፡፡ ዘርፈ ብዙ የሺርክ አይነቶች እዚህም እዚያም እንደ አሸን ፈልተዋል፡፡ በአፈንጋጭ ሺዐዎች የተጀመረው የቀብር አምልኮ ዱላውን በተቀበሉት ሱፍዮች ቀጥሏል፡፡ ኢብኑ ዐረቢ፣ ኢብኑ ፋሪድ፣ በደዊ፣ ቲልሚሳኒ፣ ሻዚሊ እና መሰል የሱፍያ አውራዎች ግብአተ መሬታቸው የተፈፀመው ኢብኑ ተይሚያ በተወለዱበት በሰባተኛ ክፍለ ዘመን ነው፡፡ ፈተናቸው ግን ከህልፈታቸው በኋላ ይበልጥ ጨምሯል፡፡ ከራማና ሰይጣናዊ የጥንቆላ ስራ ብዙው ሰው ዘንድ ተቀላቅሏል፡፡

የመዝሀብ ጎጠኝነት ነግሶ በየከተማው ለአራቱም መዝሀብ ቃዲ የሚመደብበት ዘመን ነው፡፡ በአንድ መስጂድ ውስጥ ለአንድ ሶላት አራት ጀመዐ የሚቋቋምበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ ሆኖም ግን መንግስታዊ ልዩ ድጋፍ ከሚደረግለት የሻፍዕይ መዝሀብ ጀምሮ የማሊኪያ እና የሐነፍያ መዝሀብ ተከታዮችም ዘንድ የሰለፎች ዐቂዳ ተረስቷል፡፡ በጥቂት አካባቢዎች በስሱ ከሚገኘው የአህሉል ሐዲሥ አስተምህሮት ውጭ የአሻዒራ ዐቂዳ ከጫፍ እስከጫፍ ተንሰራፍቷል፡፡ ይህንን የዒልመል ከላም ዐቂዳ መፃረር ህይወትን ሊያስከፍል ይችላል፡፡

ራፊዳ ሺዐዎች መነቃቃታቸው ጨምሮ ሙስሊሞችን ከሚፈጁ ወራሪዎች ጋር እየተባበሩ አደጋቸው ከመቼውም በላይ ጨምሮ ነበር፡፡ በሙስሊሙ ግዛት ውስጥ የሚገኙት ክርስቲያኖች በአንድ በኩል ከውጭ ወራሪ ጋር የሚያብሩበት ሁኔታ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ለአመታት የሚዘልቁ ከውስጥ የሚፈጠሩ ሁከቶችም ነበሩ፡፡

በሌላ በኩል እንደ ኢብኑ ደቂቀል ዒድ፣ አልሓፊዝ ሸምሰዲን አዝዘሀቢ፣ ኢብኑ ቀይም አልጀወዚያ፣ ዒማድ ኢብኑ ከሢር፣ ኢብኑ ዐብዲል ሃዲ እና ሌሎችም ታላላቅ ዐሊሞች የነበሩበት ዘመን ነው፡፡ አንባቢ ስለ ኢብኑ ተይሚያ ዘመን ጥቅል ምስል እንዲይዝ በማለም ነው በወፍ በረር ስለዚህ ርእስ የቃኘሁት፡፡

``ኢንሻአላህ ይቀጥላል``
t.me/linkbi7
30 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 18:42:32 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑦☞ Dr. Arthur Bertrand  ዶ/ር አርተር በርትራንድ (የፈረንሳይ የሕክምና ሳይንቲስት እና ደራሲ)
“ ትልቅ አላማን በጥቂት የገቢ ምንጭ በመጠቀም አስደናቂ ውጤት ማስገኘት መቻል የሰው ልጅ የላቀ አዕምሮ መለኪያ ሶስት መስፈርቶች ቢሆኑ ማን ነው በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ ያለ ትልቅ የሚወዳደር? አብዛኛዎቹ የታወቁ የሚባሉ ገናና ሰዎች ሰራዊት፣ ህግና ግዛቶችን ይመሰርታሉ፡፡ እነዚህ የመሰረቷቸው ቁሳዊ ሃይሎች ብዙውን ጊዜ አይናቸው ፊት ለፊት ሲፈርሱ ይታያሉ፡፡ ይህ ሰው ያንቀሳቀሰው ሰራዊትን፣ ስነ ህግን፣ ግዛቶችን ፣ህዝቦችን እና ስርወ መንግስታትን ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠር የአለምን አንድ ሦስተኛ ነዋሪ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንበሮችን ጣዖቶችን ሃይማኖቶችን ሃሳቦችን እምነቶችን እና ነፍሶችን የነቀነቀ ነበር….
ለድል ያለው ትዕግስት ፣የጋለ ፍላጎቱ ባጠቃላይ ለአንድ ሃሳብ ነበር፡፡ የንጉሠ ነገሥት ግዛት የመመስረት ፍላጎት አልነበረውም፡፡
30 viewsGlamor, 15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 14:31:23 የኡስታዝ ሙሀመድ አህመድ ሙነወር "ኢብኑ ተይሚያህ፤ የሱናው አንበሳ" #ክፍል_5 በአላህ ፍቃድ እነሆ #መዝሀባቸው፦ የፊቅህ መዝሀባቸው የሐንበልያ መዝሀብ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የኢጅቲሃድ መስፈርቶችን በሚገባ ያሟሉ ሁለ ገብ ሙጅተሂድ እንደመሆናቸው ኢጅቲሃዳቸው ያደረሳቸውን ይመርጣሉ እንጂ ከሐንበልያ መዝሀብ አጥር ውስጥ የተገደቡ አልነበሩም፡፡ ይህንን ሐቅ ከሚያጎሉ በርካታ ገጠመኞች ውስጥ አንዱን…
41 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 07:19:16 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑥☞ Alfonso de lamartin አልፎንስ ደ ላማርቲን/ (ፈረንሳዊ ፀሐፊ፣ ገጣሚ፣ በፈረንሳይ አብዮት እና በናፖሊዮን አገዛዝ መካከል የነበረው ‹‹ሁለተኛው ሪፐብሊክ›› መንግሥት እንዲመሠረት ዓይነተኛ ሚና የተጫወተ፣ እንዲሁም የፈረንሳይ ባንዲራ አሁን በሚታወቅበት መልኩ እንዲቀጥል ያደረገ የፖለቲካ ሰው) ‹‹የዓላማ ግዝፈት፣ የማሳኪያ መንገድ ማነስ እና አስገራሚ ድል ለሰው ልጅ ድንቅ ስኬት መለኪያ መሥፈርቶች ከሆኑ በዘመናዊው የዓለም ታሪክ ማነው ደፍሮ ሙሐመድን ከሌላ ጋር ማወዳደር የሚችል? ከሰዎች መካከል ዝነኛነትን የተጎናጸፉትኮ የፈጠሩት መሣሪያን፣ ሕግን እና ግዛትን ብቻ ነው፡፡ ከቁሳዊ ኃይል የዘለለ ስኬት የላቸውም… እርሱም በዓይናቸው ሥር ሲፈረካከስ ያዩት (ጊዜያዊ) ኃይል ነው፡፡… ፈላስፋ፣ አንደበተ ርቱእ፣ ነቢይ፣ ሕግ አውጪ፣ የሐሳብ አስገባሪ፣ የምክንያታዊ እና ምስል አልባ እምነት መልሶ አቋቋሚ፣ የሃያ ምድራዊ እና የአንድ መንፈሳዊ ግዛት መሥራች -ሙሐመድ! የሰው ልጅ ታላቅነት ሊለካባቸው በሚችሉ መሥፈርቶች ብንለካው ‹ከእርሱ የላቀ ሰው አለን?› ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን፡፡››
Histoire de la Turquie, Paris 1854, Vol II, pp. 276-77:
https://t.me/linkbi7
10 viewsGlamor, edited  04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 07:14:32 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑤☞ Micheal H. Hart /ማይክል ኤች ሃርት/ (አሜሪካዊ የሥነ-ጠፈር ተመራማሪ /አስትሮፊዚስት/፤ The 100: A Ranking of the Most Influential Persons in History (100ዎቹ፡ በሰው ልጅ ታሪክ ተጽእኖ ያሳደሩ ሰዎች በደረጃ) በሚለው መጽሐፉ እውቅና ያገኘ፤ ‹‹በታሪክ ተጽእኖ ያሳደሩ ሰዎችን ደረጃ ስመድብ ሙሐመድን በአንደኝነት ማስቀመጤ ብዙዎችን ሊያስገርም እና ሊያጠራጥር ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እሱ በሃይማኖታዊም ሆነ በዓለማዊ ደረጃ እጅግ በላጭ ስኬት ማስመዝገብ የቻለ ብቸኛ ሰው ነበር፡፡››
The 100: A Ranking of the Most Influential Persons in History, New York: Hart Publishing Company, Inc. 1978, page. 33
https://t.me/linkbi7
30 viewsGlamor, edited  04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ