Get Mystery Box with random crypto!

Bilal Media & Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication B
የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication
የሰርጥ አድራሻ: @linkbi7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-01-17 20:33:02 #መላ_ዐረቢያን_የሚያስተዳድረው_የኢስላማዊ
ስረወ መንግስቱ መሪ ዑመር ረዐ የመስጂደል ሀራምን ግቢ ለማስፋፋት የዐባስ ቤት እንዲፈርስ እና ለዐባስም በምትኩ ቆንጆ ቤት ሌላ ቦታ እንዲገነባለት ትዕዛዝ አስተላለፈ።

አባስም፦‹‹ቤቴ እንዲፈርስ እልፈቅድም›› አሉ።
(መብት)

ዑመርም፦‹‹ዐባስ! የአላህን ቤት ቤት ለማስፋፋት እኮ ነው›› አለው።
(ማባበል)

ዐባስም፦‹‹አልፈቅድም አልኩኝ እኮ ዑመር!›› ብሎ መለሰ።
(መሪ ፊት መብትን ማስከበር)

ዑመርም፦‹‹እንግዲያውስ ወደ ሸንጎ ሂደን እንዳኝ፤ ሚዳኘንን ዳኛም አንተው ምረጥ›› አለው።
(ፍትህ እና መተናነስ)

ዐባስም፦‹‹ዳኛ ሹረይሕ ይዳኘን›› አለ።
(ጥሩ ስም ሲኖር)

ዑመርም፦‹‹ተስማምቻለሁ››አለ።
(መተናነስ)

ዐባስም፦‹‹የምእመናን መሪ ሆይ! በል ዳኛ ሹረይሕን ጥራው'ና ይዳኘን›› አለ።

ዑመርም፦‹‹ዳኛ ወደሚዳኛቸው ሰዎች አይሄድም፤ እነሱ ናቸው ወደ እሱ መሄድ ያለባቸው። ተነስ እኛ እንሂድ›› አለው።
(መርህ)

ሁለቱም ተያይዘው ወደ ሸንጎው ዳኛ አመሩ። ሸንጎው ፊት ሲቆሙም ዳኛው፦‹‹የምእመናን መሪ...›› ብሎ ዑመርን ሲጠራ ዑመርም፦‹‹ዑመር ብለህ ጥራኝ፤ ሸንጎ ላይ እስካለሁ ድረስ›› አለው።
(የሸንጎ እና የዳኛ ክብር)

ሸንጎው ተጀመረ። ሁለቱም ስሞታቸውን ለዳኛው ካሳሰቡ በኋላ ዳኛው እንዲህ ስል ውሳኔ አስተላለፈ፦‹‹ከሀራም የፀዳ ቦታ ማለት መስጅድ ነው።መስጂድን ለማስፋፋት ያለ በጎ ፈቃዱ የዐባስን ቤትም ማፍረስ ደግሞ ሀራም ነው››
(ፍትህ ፣ ሀላፊነት፣ ድፍረት)

ዑመርም ክሱ ውድቅ ሲሆንበት፦‹‹ምንኛ ፍትሀዊ ዳኛ ነህ! ሸንጎህ ያማረ›› አለው።
(ዕውነታን መቀበል)

ዑመር እዝያው ሽንጎ ላይ ሁኖ ይህንን ዳኛ የዳኞች ሁሉ የበላይ አድርጎትም ሾመው።
(ዕምነት)

ይህን የተመለከተው ዐባስም፦‹‹እንግዲያ ነገሩ እንዲህ ተሆነማ ፤ እኔም ቤቴን በገዛ ፈቃዴ ለአላህ ብዬ ለቅቄያለሁ›› አለ
(ከድል በኋላ ያለ ለጋስነት)

Sefwan Sheik Ahmedin

ምንጭ፦البدايه والنهايه
22 viewsGlamor, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 20:26:26 በቅርብ ቀን በአዲስ ማንነት በአዲስ አቀራረብ በአዲስ መንፈስ አዳዲስ ያልተሰሙና ያልተደመጡ ታሪኮችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን። አስደናቂና አስተማሪ የሰሐቦችን ገድል የታቢኢዮችን ውሎ የሷሊሆችን ታሪክ እያነበቡ ትምህርት እየሰሙ ወደመልካም ነገር የጠቆመ ሰው የሚያገኘውን አጅር ይጎናፀፉ ዘንድ ወደቻናላችን ወዳጅዎን ይጋብዙ ጉሩፓችንም ላይ ኢንቫይት በማድረግ ከኸይሩ ይቋደሱ @yesheh_kalidrashid_daewawoch
22 viewsGlamor, 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 20:23:31 በቅርብ ቀን በአዲስ ማንነት በአዲስ አቀራረብ በአዲስ መንፈስ አዳዲስ ያልተሰሙና ያልተደመጡ ታሪኮችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን። አስደናቂና አስተማሪ የሰሐቦችን ገድል የታቢኢዮችን ውሎ የሷሊሆችን ታሪክ እያነበቡ ትምህርት እየሰሙ ወደመልካም ነገር የጠቆመ ሰው የሚያገኘውን አጅር ይጎናፀፉ ዘንድ ወደቻናላችን ወዳጅዎን ይጋብዙ ጉሩፓችንም ላይ ኢንቫይት በማድረግ ከኸይሩ ይቋደሱ

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
25 viewsGlamor, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 16:30:18 #እያሰብን 31
:
<< በጣም ተደስተን ባለንበት ጊዜ ላይ የደስ ደስ በሚመስል መልኩ ከአምላካችን ጋር የምንቀያየም ሰዎች ምንድን ነው ችግራችን ግን? የደስ ደስ ማመፅ እንደሆነ ወንጀልን አያሳንስም። ወገን ኧረ እያሰብን! >>
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
@Venuee13
45 viewsGlamor, 13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 22:02:52 ሐባን ኢብኑ ሙንቂዝ [ረዐ] እንደዘገቡት:

«አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: ‐ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዱዓዬን ሲሶ ለርሶ ሶለዋት ላድርገው?»
እርሳቸውም:‐ «ከፈለግክ አዎን!» አሉት።
«ሁለት ሶስተኛውን ላድርገው?» አላቸው።
«አዎን!» በማለት መለሱለት።
«ሁሉንም ለርሶ ሶለዋት ላድርገው?» ጠየቀ።
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ አሉ:‐ «እንደዚያ ከሆነ ያሳሰበህን የዱንያም ሆነ የአኺራን ነገር አላህ ይገላግልሀል።»
ሹዐቡል‐ኢማን ላይ በይሀቂይ ዘግበውታል።
51 viewsGlamor, 19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 21:17:15 የወረዳ 10 አዲስ ተመራጮችን በተመለከተ

ታህሳስ መጀመሪያዎቹ ላይ በእለተ ሀሙስ ቀን የየካ ክ/ከተማ አመራሮች ደብዳቤ በመላክ ኢማሞች፣ሙአዚኖች እና የአስተዳደር ሰራተኞች በአጠቃላይ ስለ መስጅዶቻችን ይመለከተናል የሚል ሁሉ በእለተ እሁድ በአሊ ሚራ መስጅድ እንዲገኝ የሚል መልእክት ያለው ደብዳቤ ተላለፈ። ገና ይህ ጥሪ ሲተላለፍ ጀምሮ በቃ ልንባረር ነው በማለት ምንም ባልተወራበትና ንግግር ባልተደረገበት መንጫጫትና አላስፈላጊ ንግግሮችን መስማት ጀመርን

እኔ ይህ ከሆነ (በነሡ የምመራ ከሆነ) በተለይም አንድ ተራን ሠው በመጥቀስ እሱ ካልተነሣ እከፍራለው እስከመባል ደረጃ ደረሠ ልብ በሉ ይህንን የተናገረው
እብድ ወይም ስካር ላይ ሆኖ አይደለም ጤነኛ ነው
ተራ ሰው ወይም ሌላ ችግርም ያለበት እንዳይመስለን!!! ራሡን "የጃቢር መስጅድ አስተዳዳሪና ወቅፍ አድርጊ" ብሎ የሚጠራው (ብሎ የሚጠራው ነው ያልኩት) ግለሠብ ነው። በርግጥ ለዚህ ንግግር በወቅቱ ከነበረ አንድ አባት መልስ ተሠቶታል
ይህንን ንግግር (...... እከፍራለው) ያለውን ማለቴ ነው፤የቀድሞዎቹ መጅሊሶች እንኳ አልተናገሩትም
እንግዲህ የሚያወራውም እያወራ ያልተባለን በሹክሹክታ እየዘባረቀ እኛም ሹክሹክታቸውን በስፒከር እየሠማን
በዚህ ውዝግብ ውስጥ ተሁኖ የጥሪው ቀን ደርሶ እሁድ በወረዳው የሚገኙ 4 መስጅዶች ላይ ካሉ ጀመዐዎች ወደ ስብሰባው አቀናን
ከኦካሻ 5 ሰው
ከሁነይን 7 ሰው
ከአቡበከርም ተቀራራቢ የሆነ ሠው ሲመጣ
ከጃቢር ሁለት ሰው መጣ ኢማምና ቅድም እከሌ ካልተነሣ እከፍራለው ባዩ ተውፊቅ። ሌሎቹ ስለማያገባቸው ቀርቶ ሳይሆን ስላልነገራቸው ነው ም/ቱም ብዙዎቹን ለምን እንደቀሩ ስጠይቅ የሠሙት ነገር እንደሌለ እና ደብዳቤው የደረሠው አካል እንዳላስተላለፈ ነው የተረዳሁት በተጨማሪም በጁምዐ እና ቅዳሜ እለት እዛው ጃቢር መስጅድ ስገዱና የሚተላለፍ መልእክት ካለ ታሣውቁኛላቹህ ያልኳቸው ወጣቶች ምንም እንዳልነበረ አሣወቁኝ እዚህ ጋር አንድ ነጥብ ያዙና እንቀጥል...

አሊ ሚራ መስጅድ ስንደርስ ፕርግራሙ ተጀምሮ የወሌ ሙሀመድ መስጅድ ኢማም ስለ አማና ከባድነት ዳእዋ እያደረጉ ነበር እጅግ ልብን የሚያርሱና የበደልን መጥፎነት ግልፅ አድርገው የሚያሣዩ እንዲሁም ሹመትን መመኘት ከአልላህ እገዛን እንደማያስገኝና ሣይፈልግ የተጫነበት ግን አልላህ እንደሚረዳው በመረጃ እያጣቀሱ ታላላቅ አሊሞች በተገኙበት ድንቅ ምክር አስተላለፉልን አልላህ የተግባር ሠዎች ያድርገን
መድረክ መሪዎቹም ስለ ተቋም ምንነት አላማውና ተግባሩ በግልፅ ቋንቋ አስቀመጡ ለምሣሌ
ተረኛ እነሡ ናቸው የሚባል ነገር መኖር እንደሌለበት
በአንድነት ለጋራ አላማ መጓዝ እንዳለብን
ሀገራዊና ልማታዊ ጉዳዮች ላይ መሣተፍ እንዳለብን
መስጅዶችን በአስተዳደርም ይሁን በጀመዐ ማስተካከል ማጠንከርና ከመጠፋፋት መተቃቀፍ ከመጣላት መፋቀርን በአጠቃላይ በአንድነት በመጓዝ ላይ አደራ አደራ አደራ ብለው አሳሰቡን በቀጣይም

ከታዳሚው ሀሣብ እንዲነሣ መድረኩ ተከፈተ በርግጥም ጠቃሚ የሆኑ ሀሣቦች ተነስተዋል ከተነሡት አስተያየቶች መካከል፦
በወረዳ 10 ላይ የጃቢር መስጅድ አስተዳደር ነኝ የሚለው አንድ ሠው (ከላይ የተጠቀሰው) የሚከተሉትን ሀሣቦች አነሣ
መስጅዱን ወቅፍ ያደረኩት እኔ ነኝ
አስተዳዳሪውም ራሴ ነኝ
ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ ንግግራቸው እንዴት ይጣፍጣል ለነሡ ለማስረከብ ዝግጁ ነን ከጎናቹህ ነን...
የሠፈር አንዳንድ ኡማውን የሚከፋፍሉ ሠዎች አሉ ለህፃናት ጥላቻን የሚሰብኩ
አሽአሪያና ማቱሪዲያ የጀሀነም ናቸው የሚሉ አሉ መረጃ እንዲያመጡ 4 ወር ሙሉ ጠብቀናቸው በዛው የጠፉ አሉ ሠዎችን እንዳይበክሉ ብዬ ህዝቡ ግራ እንዳይጋባ ሀላፊነት ስላለብኝ አስትቻለው...
በአጠቃላይ ይሄ ለውጥ ደስ የሚልና የሚበረታታ ነው ከጎናቹህ ነን....

እነዚህን ወሬዎቹን አስታውሳለው የሚገርመው ደብዳቤውን እንኳን በአግባቡ ያላስተላለፈ አካል ነው እንግዲህ የኡማ ሀላፊነት አለብኝ እያለ ዓሊሞች ፊት የሚያወራው???

ወደ መጨረሻ ላይ ትውውቅ ይደረግ ተብሎ የየወረዳው አመራሮች መድረክ ላይ ወታቹህ ራሣችሁን አስተዋውቁ ተባልንና አስተዋውቀን ስንመለስ ወረዳ 10 ተቃውሞ አለ ማለት ጀመረ። ከመድረክ መሪዎቹ ሌላ ግዜ በሰፊው እንደምንገናኝና እንደሚያወሩበት ቢነገረውም ተደጋጋሚ የእድል ይሰጠኝ ምልክት አሣየ። ዙሁር ደርሷል ኢማሞች ደሞ ወደየ መስጅዶቻቸው መሔድ አለባቸው ቢባልም ፕሮግራሙ በዱዓ ከተዘጋ በኋላ ወደ መድረክ በመሄድ መስጅድ ውስጥ በከፍተኛ ጩኸት መናገር ጀመረ።ቅድም ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ ንግግራቸው እንዴት ይጣፍጣል እንዳላለ በደቂቃ ውስጥ ተቀይሮ አይሆንም አላስረክብም ጲሪሪም ጳራራም ማለት ጀመረ ከወንድሞችም መካከል ይህ ሠው ማን እንደሆነና በ2004/5 ግዜ ምን እንደሠራ የሚያውቁ ወንድሞች ፊትለፊት አፋጠጡት የአልላህ ቤት ላይ መጮህ የለመደ ማንም ይኑር ማን ግድ የለውምና ጃቢር እንደለመደው በመጮህ የሚያሣምን መስሎታል ሣይሳካለትም ቀርቶ ፊቱ ቀልቶ እያጉረመረመ መኪናውን አስነስቶ ያመጣቸውን ሠዎች እንኳ ሙሉ ሳይዝ ተመለሠ

ስንት ነገሮችን ይሁን ይለፍ ብለን ዝም አልን
ISIS ናቹህ ቦክዋራ፣አልሸባብ ተባልን አላዋጣ ሲል
17 ኮሚቴ ትሳደባላቹህ ተባለ አላዋጣ ሲል
ሙፍቲን ተሣድባችኋል ተባለ ለዚህም መረጃ ሲጠየቅ ተቀየረችና ሳዳቶች ናቸው ብሎ እርፍ አሁንም በየግዜው ይቀያየራል ትችቱ የአሁኑ ደሞ ሌላ ናት

4 ወር ሙሉ ጠብቀን መረጃ አልመጣልንም ስላለበት ስለ መፀሀፏ ደሞ ሌላ ሠፊ ታሪክ ነው ራሡን ችሎ እመጣበታለው ኢን ሻ አ አልላህ
54 viewsibnu rebah, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 15:27:32 ተማሪ እያለው ወንድራድ ስንማር ሠላት ለማስፈቀድ በወቅቱ መጅሊስ ይሰራ የነበረ ሰው ስናናግር የተሠጠን ምላሽ፦አንድ ጁምዐ ስገዱ ሁለት ጁምዐ ይለፋቹህ የሚል ነበር ከ6/7 አመት በፊት መሆኑ ነው
ሳምንታዊ ሙሀደራ ለማድረግ 02 ሙስዐብ መስጅድ ገብተን "ማንም ስለናንተ ሀላፊነት አይወስድም" "እዚህ ማንን አስፈቅዳቹህ ነው የተሠበሠባቹሁት?" የሚሉ ንግግሮችን በወቅቱ ከነበሩ ኮሚቴዎች አንዱ ለኔ ለራሤ ነገሮኛል "ክ/ከተማም እንደሄዳቹህ ሠምተናል ማን ሂዱ አላቹህ? አይነት ንግግርም ተናግሮኛል
ት/ቤቱ መግቢያው በር ላይ የነበረው በርበሬ ማስፈጫ ወፍጮ ቤት የምንገናኝበት ነበር ግን የኛው ተቋም ላይ የነበሩት ሰዎች ሰውየውን አስፈራርተው እዛ እንዳንሠግድ ታግደን ነበር
ወንድራድ ት/ቤት አንድ ሙስሊም አስተማሪ የአንዲትን ሙስሊም ተማሪ ሂጃቧን አውልቆ ዳስተር አደረገው" ብሎኛል ከአሁኑ ወረዳ 12 መጅሊስ አመራር መካከል አንዱ

አሁን እነዚህ ናቸው በአልላህ ለኡማ ተጨናቂ???
አየር መንገድ በሒጃብ ሠበብ በፂምና በሱሪ ም/ት ስንት ሙስሊሞች ተገለሉ አሁን ግን ገና ብዙ ቢቀርም ያ በነበረበት አይደለም
ተማሪ በሰላት ወቅት በነፃነት እየወጣ እንዲሰግድ ያመቻቹልንና ተቋም አለን ብለን እንድናስብ ያደረጉንን ከአልላህ በመቀጠል ብዙ የለፉልንን አዲሡን የመጅሊስ አመራሮች አለማመስገን አይቻልም ጀዛኩሙልላህ አልላህ የወንድም እህቶቻችንን ጭንቀት እንዳቀለላቹህ የአኺራ ሀሣባችሁን ያቅልልላቹህ
60 viewsibnu rebah, 12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 07:13:15 #ሓቲም_አልዓሶም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«የፈጅር ሶላት ማምለጥ ማለት እዝን መደራረስና አደራ መባባል የሚያስፈልገው ከባድ ነገር ነው።»


۞ صــلاح الأم【2/420】۞
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
·•● የሰለፎች ኮቴ ●•·
በየቀኑ የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች እንዲደርስዎ ይቀላቀሉን ፣ ለሌሎችም ያሰራጩ
https://t.me/selefs_footstep
57 viewsGlamor, 04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 20:42:55 << ነፍሳችን ሳንሰስት የምንሰጥላቸው ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ እንዳሉ አለማወቅ ያማል አይደል? ፍቅር እና መውደዳችን ያለ ገደብ የምንሰጣቸው ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ እያሳለፉ እንዳሉ ማወቅ አለመቻል ያማል አይደል?
(እንዲሁ በደፈናው ያማል እንዳትሉ የምትወዱትን በማጣት እስካልተፈተናችሁ ድረስ ህመሙን በጥልቀት ልታውቁት አይቻላችሁም!) ከመሀከላችን የሚወዷቸውን እቅፍ የናፈቁ አሉ። ጠረናቸው የናፈቃቸው፣ ምክር ተግሳፃቸው ውል የሚልባቸው አሉ። አንዳንድ የሚስቁልን ሰዎች ወዳጆቻቸውን የማጣትን ሀዘን ውጠው ነው። ታጋሾች ሲታገሱ ሀዘናቸውን የሚረሱት እንዳይመስላችሁ። ውስጥ ውስጡን እየታመሱ ያሉ ብዙ ሳቂታዎች በመሀከላችን አሉ። ስንት መዓት ሀዘን ተሸክሞ የሚያባብለን ብዙ ሰው አለ። አስታዋሾቻችሁ የማያዝኑ
ምንም የማይሰማቸው አድርጋችሁ አታስቡ! ብዙ ታጋሾች ጠልቆ የሚያማቸው ሀዘን አላቸው። ፈገግታዎችን ፈትሹ እንባ ይዘዋል። ሳቆችን አዳምጡ ጩኸት አላቸው። አይኖችን ተመልከቱ ናፍቆት ጋርዷቸዋል። ምኞቶችን ቃኙ ስክነት ተራቢ ናቸው። ግዴላችሁም አፅናኝ አስታዋሾቻችንም ከህመም ሽረው ላይሆን ይችላል ተስፋ የሚያቀብሉን። የልብ ትካዜዎች በሳቀና በፈገግታ መንፀባረቅ ከጀመሩ ሰንብተዋል። በእርግጥ በደንብ የሚያስተውሉቱ ይረዱታል። ብቻ #አብሽሩ! ልቤ እንዲህ ይለኛል። >>
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
@Venuee13
57 viewsGlamor, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 22:39:35
ራህማኔ ቶሎ ድኖ ዳግም አለመታመምን እንጂ ሌላ አልሻም ልክ እንደ አዩብ መታገስንም አልችልም ያው ሞት አፋፍ ላይ እንደመሆኔ መጠን በዚህ ሀለቴ እንድታገኘኝ ስለማልፈልግ አድነኝ።
64 viewsGlamor, 19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ