Get Mystery Box with random crypto!

> (አብዱልሀኪም ሰፋ) : @Venuee13 @Venuee13 | Bilal Media & Communication

<< ነፍሳችን ሳንሰስት የምንሰጥላቸው ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ እንዳሉ አለማወቅ ያማል አይደል? ፍቅር እና መውደዳችን ያለ ገደብ የምንሰጣቸው ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ እያሳለፉ እንዳሉ ማወቅ አለመቻል ያማል አይደል?
(እንዲሁ በደፈናው ያማል እንዳትሉ የምትወዱትን በማጣት እስካልተፈተናችሁ ድረስ ህመሙን በጥልቀት ልታውቁት አይቻላችሁም!) ከመሀከላችን የሚወዷቸውን እቅፍ የናፈቁ አሉ። ጠረናቸው የናፈቃቸው፣ ምክር ተግሳፃቸው ውል የሚልባቸው አሉ። አንዳንድ የሚስቁልን ሰዎች ወዳጆቻቸውን የማጣትን ሀዘን ውጠው ነው። ታጋሾች ሲታገሱ ሀዘናቸውን የሚረሱት እንዳይመስላችሁ። ውስጥ ውስጡን እየታመሱ ያሉ ብዙ ሳቂታዎች በመሀከላችን አሉ። ስንት መዓት ሀዘን ተሸክሞ የሚያባብለን ብዙ ሰው አለ። አስታዋሾቻችሁ የማያዝኑ
ምንም የማይሰማቸው አድርጋችሁ አታስቡ! ብዙ ታጋሾች ጠልቆ የሚያማቸው ሀዘን አላቸው። ፈገግታዎችን ፈትሹ እንባ ይዘዋል። ሳቆችን አዳምጡ ጩኸት አላቸው። አይኖችን ተመልከቱ ናፍቆት ጋርዷቸዋል። ምኞቶችን ቃኙ ስክነት ተራቢ ናቸው። ግዴላችሁም አፅናኝ አስታዋሾቻችንም ከህመም ሽረው ላይሆን ይችላል ተስፋ የሚያቀብሉን። የልብ ትካዜዎች በሳቀና በፈገግታ መንፀባረቅ ከጀመሩ ሰንብተዋል። በእርግጥ በደንብ የሚያስተውሉቱ ይረዱታል። ብቻ #አብሽሩ! ልቤ እንዲህ ይለኛል። >>
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
@Venuee13