Get Mystery Box with random crypto!

Bilal Media & Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication B
የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication
የሰርጥ አድራሻ: @linkbi7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-12-29 20:22:37 ምክር ለእህቶች
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሒመሁል'ሏህ) እንዲህ ይላሉ:-

«ሴት ልጅ ትዳር ላይ ዲን ያለውና ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው እንጂ እንዳትመርጥ እመክራታለሁ፤ ለትዳር የጠየቃት ሰው ሁሉም ስለ አጠቃላይ ምንነቱ ከመጣራቱ በፊት ቸኩላ እሺ እንዳትል እመክራታለሁ፤
:
ይህን ስል ግን ምንም አይነት ወንጀልን የማይሰራ እንዳታገባ እያልኩኝ አይደለም፣
ምክንያቱም ይህ የማይቻል ነገር ነውና ነገር ግን አመቻቹ ፍትሀዊም ሁኑ ለማለት ነው።»

ምንጭ:- ፈትዋ ኑሩን አለ ደርብ (10/34)
23 viewsibnu rebah, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 15:08:34 ከሰው ስትቀርብ ተረድቶ የሚረዳህ ልታገኝ ትችል ይሆናል፤ በዛውም ልክ በችግርህም ቅልብልቦሽ ሚጫወት አይጠፋም።
ብቻህን ስትሆን ለራስህ ጎድለህ ትገኝ ይሆናል እንጂ ጎዶሎህን እስካላሳየህ በሰው ዘንድ አትጎድልም ፤ የመቸገርህን አሻራ አትተውም! ብቻህን ስትሆን ሃላፊነትን አትጋራም ፤ ከሰው ምትጠብቀው ነገር አይኖርም ፤ እያንዳንዷን ሁነት በመለማመድ ትጠነክራለህ………
24 viewsGlamor, 12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 18:59:44 የኔ እይታ 28

ሲያገኛት ከአባቷ እና ከወንድሟ ውጭ ማንንም ወንድ እወድሀለሁ ብላ የማታውቅ፣ ሲበዛ ሀያዕ የተላበሰች፣ አጅ ነብይ ወንድ "አሰላሙ አለይኩም "ሲላት ወአለይኩም ሰላም" ለማለት የምታፍር፣እድሜዋ ደርሶ አግቢ ስትባል ነውር መስሏት ያለቀሰች፣ ድንገት አንድ ወንድ ጋር አይን ለአይን ስትገጣጠም በሀፍረት ጉንጮ የሚቀላ፣ ቁጥብ ሴት ነበረች.......አንድ ምሽት ስልኮ ላይ የተላከው የፅሁፍ መልዕክት ሂወቷን ቀየረው።ማንም አድንቋት በማያውቀው ልክ በሚያምሩ ቃላት ውበቷን ሲያደንቅ የተለየ ስሜት ተሰማት፣ "እንደኔ ልጅ በዚህ አለም ቆንጆ የት አለ!" እያለ በየጊዜው ከሚፎክረው አባቷ በላይ የእሱ ለስላሳ ቃላት ልቦን አሸፈተው። ለመጀመሪያ ግዜ ባል ቢኖረኝ ብላ ልታሳልፈው ስለምትችለው የሚያምር ሂወት ማሰብ ጀመረች። ከአንድ ግዜ በላይ አጅ ነብይ ወንድ ማየት የሚፈሩ አይኖቿ የላከላትን ፎቶወች ደጋመው አዩ፤ ለመጀመሪያ ግዜ ከወንድሟ ውጭ ወንድ ጋር መፃፃፍ ጀመረች። ይሄኔ ልቧ አላህን እንዳታምፅ እና ወደ መጥፎ መንገድ እንዳታመራ "ተይ አትፃፊለት"ሲላት ነፍስያዋ ደግሞ ሰው ስንት ነገር ያደርጋል አንቺ መፃፃፍን ታካብጂዋለሽ እንዴ?"ትላታለች። ነፍስያዋ አሸንፋ መፃፃፉ አድጎ ግንኙነታቸው ወደ መደዋወል እና ፎቶ ወደ መላላክ ሲያድግ ቀጣዩ እርምጃዋ አላህ ጋር ሊያጣለት እንደሚችል ብታስብም እምቢ የማለት አቅሞን እና የድሮ ሀያዖን ፍቅር የሚሉት ሀይል አሳጣት። በቅርብ ቀን ሊያገባት እንደወሰነ እና ሊመሰርቱት ላሰቡት የትዳር ሂወት ተገናኝተው ማውራት እንዳለባቸው ሲነግራት "አንድ ሴት እና ወንድ ብቻቸውን አይገለሉም ሶስተኛው ሸይጦን ቢሆን እንጂ" የሚለውን የመልክተኛውን ሀዲስ አስታውሳ አላገኝህም ብትልም ከብዙ ንግግር በኋላ ሰው ባለበት እንደሚገናኙ እና ስለሰርጋቸው ብቻ አውርተው እንደሚለያዩ አሳምኗት ተገናኙ። ልቦ በሚያደርገው ነገር ተረብሾ እንዴት ለቤተሰብ አሳውቀው ቶሎ እንደሚጋቡ በተደጋጋሚ ብትጠይቀውም ከዛ ይልቅ ከተጋቡ በኋላ ስለሚያሳልፉት romance ሂወት እጆን ይዞ እያወራ ደስ የማይል ስሜት ውስጥ ሲያስገባት "ዝሙትን አትቅረቡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ስራ ነው እና። መንገዱም ከፋ!"የሚለውን የጌታዋን ቃል አስታዉሳ ከአጠገቡ ተስፈንጥራ ተነሳች። እንዳይከተላት ነግራው ነፍሶን እየወቀሰች ወደ ቤቷ አቀናች። ለወራት አይኖን ጋርዶ የጌታዋን ትዕዛዝ እንዴት ሲያስጥሳት እንደነበር የተፃፃፉትን መልዕክቶች፣የላከችለትን ፎቶወች እያየች ማልቀስ እና እራሷን መውቀስ ጀመረች። እንዴት ነው ያወራሁት?እንዴትስ ነው ጓደኞቼ ስልክ ላይ እንኳን የለሉ ፎቶወቼን ለእሱ የላኩት? አሞኝ ነበር?አቅሌን ስቼ ነበር?እንዴት ይሄን ሁሉ ሳደርግ አላህ ዝም አለኝ? ለቀናት በፀፀት ተገርፋ አላህን በእምባ እየታጠበች እንዲምራት ለመነችው።በተደጋጋሚ መደወሉ አሰልችቷት ከቀናት በኋላ ስልኩን አንስታ ትወቅሰው ጀመር።
"ምን አድርገኸኝ ነው አንድ ሰው አውርቼ የማላቀውን ያን ሁሉ ጊዜ ሳወራህ ፣ስፅፍልህ፣ፎቶ ስልክልህ የነበረው?ምን ብታስነካኝ ነው ላገኝህ ያለህበት የመጣሁት? አላህ ንፁህነቴን አይቶ ከገባሁበት አፀያፊ ነገር ባያወጣኝ ምን ልታደርገኝ ነበር ሀሳብህ? ጨክነህ ከዚህ በላይ ልታቆሽሸኝ ነበር? እኔ እንኳን ባላሳዝንህ አላህን አትፈራም? እውነት ልታገባኝ ነበር ወይስ አቆሽሸህ ልትተወኝ?" ውስጧ የነበረው ፍቅር ሙሉ ለሙሉ በጥላቻ ተገልብጧል።
"ስለምን ንፁህነት ነው የምታወሪው? ንፁህ ሁነሽ አጊኝቼሽ ይሆናል ግን አሁንም ንፁህ ነኝ ብለሽ አትመፃደቂ። ማንንም አውርቼ አላውቅም አንተንም አላወራም አልሽኝ እኔ ግን ሳታወሪኝ እንዳትውይ አደረኩሽ፣ ፎቶሽን ላኪልኝ ስልሽ አልነሳም አልሽኝ እኔ ግን ከመነሳት አልፎ እንድትልኪልኝ አደረኩሽ፣ማንም ነክቶኝ አያውቅም አልሽኝ እኔ ግን እነዛን ንፁህ እጆችሽን ለደቂቃ ያዝኳቸው። የዛን ቀን ክብርሽን ሳታስነኪ ስለሄድሽ ንፁህ ነሽ ማለት አይደለም! አሁን አንቺ አጅ ነብይ የምትይውን ወንድ ያወራሽ በዛ ወንድ ንፁህ የምትይውን ገላ ያስነካሽ ሴት ነሽ! ቆይ እንዴት ያገባኛል ብለሽ አሰብሽ? እኔ የማገባት ሴት አይደለም ወንድ ማግኘት ቀና ብላ የማታይ እንደሆነች አታውቂም?"አላት እራሷን እንድትጠላ አድርጎ እንደሚፈልገው ሊነጅሳት።
"ባንተ የቆሸሸው ልቤ እና እጄ በተውበት ይጠራል። አንተ ግን አላህን ብትፈራ እና ወደ እሱ ብትመለስ ይሻልሀል! ንፁህ ሴቶችን እየነጀሱ ንፁህ ሴትን መመኘት ቂልነት ነው። ጥሩ ሴቶች ለጥሩ ወንዶች እንጂ ለአንተ አይነቱ ወንድ አይገቡም"ብላ ስልኩን ዘጋችው።

የሰወች ንፅህና የሚያስጎመዣቸው፣ ሰወችን መነጀስ የሚያስደስታቸው፣ ብቻቸውን መቆሸሽ የሚጠሉ፣ እነሱ ቆሽሸው ንፁሆችን የሚመኙ ሰወችን አላህ ከዙሪያችን ያርቅል!

rehima hussen

እንደዚህ አይነት ሰወች አጋጥመዋችሁ ያውቁ ይሆን??



ለአስተያየትዎ
38 viewsGlamor, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 16:34:01 ከስራ የበለጠ ጭንቀት ብዙ ሰው ገዳይ የሆነው ብዙ ሰው ከመስራት ይልቅ ስለሚጨነቅ ነው!
       
             -- Robert Frost --
35 viewsGlamor, 13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 06:58:37 ፣ አትመቀኛኙ፣ ጀርባ አትሰጣጡ፣ የአላህ ባሪያዎች ወንድማማቾች ሁኑ»።
ﷺ !!
7 viewsGlamor, 03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 22:50:58 ኩሩ፣ በኃይማኖትህ የምትተማመን፣ በዲንህ የማትደራደር፣
"እስልምናዬ አይፈቅድልኝም፣ ከአላህ ጋር ያጣላኛል!…" ለማለት የማትፈራና የማታፍር ሙስሊም ሁን።
15 viewsGlamor, 19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 23:37:59 #ኢብኑ_ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«የሆነን ሰው በአፈጣጠሩ ካነወርከው (ካንቋሸሽከው) ፈጣሪን እንዳነወርክ ነው። ጉዳዩ አደገኛ ነው!!»


۞ لقــاء البــاب المفتــوح【1/215】۞
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
●•· የሰለፎች ኮቴ ·•●
በየቀኑ የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች እንዲደርስዎ ይቀላቀሉን ፣ ለሌሎችም ያሰራጩ
https://t.me/selefs_footstep
https://t.me/selefs_footstep
11 viewsGlamor, 20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 16:40:47 እህቴ እጆችሽን ለሀራም አትዘርጊ። አልላህን የማይፈራው ያ አጅነቢ BF የምትይው ወይም classmateሽ ዛሬ በሰላምታ የጀመረ ነገ ወደ ማቀፍና መ..... መሸጋገሩ እንደማይቀር ተገንዘቢ ም/ቱም አልላህን አይፈራማ አልላህ ይፈራል ወይም አይናፋር ነው የምትይ ከሆነ እጅግ ተሸውደሻል።አልላህን ቢፈራማ ኖሮ መጀመሪያውኑ ክልከላውን ባልተዳፈረና ክብር ያሉትና የአልላህ አማና የሆኑትን መዳፎቹን ባልዘረጋልሽ ነበር፤ይህ ሠው እኮ
የጋለ ብረት እንድትጨብጪ የሚገፋፋሽ ጨካኝ
አልላህን እንዳትታዘዢ ለማድረግ የሚለፋ ምቀኛ
አንቺ የገባሽ የአራድዬ ልጅ አይደለሽ እንዴ!? ጭሷ... እያለ ሚሸውድሽ የሸይጧን ልዑክ እኮ ነው

በልቅ ሀያት መኖር ይብቃን እስከዛሬ ያጠፋነው ይምከረን ወደ አልላህ እንምጣ፤ወደ አልላህ እናልቅስ።ዛሬ ለሡ ብለን ፍላጎታችንን ትተን ነገ አልላህ ፊት የፈለግነውን እንድናገኝ ዘንዳ

ye ustaz suleyman ማስታወሻ
25 viewsGlamor, 13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 10:07:02 #ኢማሙል_ዓውዛዒይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«የቀደምቶችን ቅሪት ያዝ አደራህን። የሰዎችን ግላዊ እይታዎች ተጠንቀቅ፣ በቃላት ቢያሸበርቁልህም እንኳን። አንተ በቀጥተኛው መስመር ላይ ከሆንክ ነገሩ ሲገለጥ ይገለጣል!!።»


۞ الشــريــعــة【63】۞
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
30 viewsGlamor, 07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 21:45:54 ኸሚስ 9
.
(ረያን_አቡዲ)

አሁን ተረዳሁኝ የፍቅር ትርጉሙን
አካል ሚያመነምን የናፍቆት ህመሙን
እሱን ያዩ ለታ ሚገረስስ ጥሙን፥

ትንሽ ስለሱ.......

የፍንጭቱ ነገር
የሚያደነጋግር
የግንባሩማ ኑር
ይገዳል ለመንገር
የፊቱማ ማማር
አስፈዝዞ ሚያስቀር፥

አንደበተ ርቱዕ አፈ ማር ዘነቡ
አዛኝ ቸር ለጋስ ገራገር ለአስሀቡ
የጀነት በር ከፋች ንጉስ ከነዘቡ፥

የሱን ውበት ሊገልፅ ያነሳ ሁሉ መድ
ቃላት እያጠረው ለማቆም ሲገደድ
ብሎ ያሳርጋል፥
ሙሀመድ ፍቅር ነው ፍቅርም ሙሀመድ።
━━━━✦✗✦━━━━━━━
   ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
@Mejnun_Leyla_poem
14 viewsGlamor, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ