Get Mystery Box with random crypto!

Bilal Media & Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication B
የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication
የሰርጥ አድራሻ: @linkbi7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-01-09 22:28:13 አጅነቢን ስለመጨበጥ ብዙ ሰው ያለው አመለካከት ይገርማል አልጨብጥም ስላልክ ልክ እንደናቅካቸው ወይም እንዳዋረድካቸው ያስበሉ ለምን??
ይባስ ብሎም ሙስሊሙ ስለ አጅነቢ ያለው እይታ ገና ብዙ ስራ ይጠይቃል። አንድ ሰው አጂነቢ አልጨብጥም ካለ ልክ እንደ ዓሊም በጣም የቀራ ተደርጎም ይወሰዳል ይሄ ስህተት ነው ምንም ብዙ ከመቅራት ከዓሊምነት ጋር የሚያይዘው ነገር የለም።
ጃሂልም ቢሆን ዓሊም አጅነቢን መጨበጥ ሃራም እንደሆነ ካወቁ መተግበር ግድ ይላቸዋል ምክኒያቱም ህጉ ለሁለቱም ስለሚሰራ።
ነብያችን ( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ) በዚህ ዙሪያ ምን እንደተናገሩ እንመልከት:-
” ﻷﻥ ﻳﻄﻌﻦ ﻓﻲ ﺭﺃﺱ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﺑﻤﺨﻴﻂ ﻣﻦ ﺣﺪﻳﺪ ﺧﻴﺮ
ﻟﻪ ﻣﻦ ﺃﻥ ﻳﻤﺲ ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻻ ﺗﺤﻞ ﻟﻪ ”
“የማትፈቀድለትን ሴት ከሚነካ የአንደኛችሁ ጭንቅላት
በብረት መርፌ ቢወጋ ይሻለዋል።” (ጦበራኒ ዘግበውታል)
ነገር ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ቡዙ መስሊም ወንዶችና
ሴቶች የማይፈቀድላቸውን ሰዎች በመጨበጥ እራሳቸውን
እየበደሉ ይገኛሉ። አልፎ ተርፎም ከወንጀሉ የበለጠ የሚያስጠሉ ምክንያቶችን ይደረድራሉ ለናሙና ያህል:-
* “ልባችን ንፁህ ናት” ይላሉ! የነዚህ ሰዎች ልብ ከነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ልብ የበለጠ ንፁህ ናትን? ለመሆኑ በዚህ ዓለም ላይ ከነቢዩ(ﷺ) የበለጠ ልቡ ንፁህ የሆነ ሰው አለ? ከርሳቸው በላይ ልቡ መልካም ነገር የሚያስብ ሰው አለን?
* “ይህንን መተው ለኛ ሀገር ይከብዳል” ይላሉ እስልምና የመጣው ነብያችንም ( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ) የተላኩት ለዓለም እንጂ ለሳውዲ፣ ለኢትዮጲያ፣ ለዓረብ፣ ለፈረንጅ፣ ለጥቁር ለሀብታም፣ ለድሀ ብለው በመለየት አይደለም አላህ እንዲህ ይላል:-
ﻭﻣﺎ ﺃﺭﺳﻠﻨﺎﻙ ﺇﻻ ﺭﺣﻤﺔ ﻟﻠﻌﺎﻟﻤﻴﻦ
“ለዓለማት እዝነት ቢሆን እንጂ አላክንህም”
ስለዚህ ሸሪዓችን ማንንም ሳይለይ ሁሉንም ይመለከታል! እስቲ ሁላችንም አንዴ ቆም ብለን እናስተውል በሚስማር ጭንቅላታችን ተወግቶ በአንድ ጎን ገብቶ በሌላ ጎን ቀዶ
መውጣቱ የማትፈቀድን ሴት ከመጨበጥ ይሻላል መባሉ
አያሰደነግጥምን? አላህ እርሱን የሚፈራ ልብ ይስጠን!!

#Share
#Share
#Share

https://t.me/twhidfirstt
https://t.me/twhidfirstt
37 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 21:08:59 አንድ ውሸት በርካታ እውነቶችን ጥርጣሬ ውስጥ ይከታል!
       -- Shaykh Kalid Yasin --
40 viewsGlamor, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 22:37:35 <አላህ ከባድ ፈተናን ፈተነኝ!>

< ደሞ አንቺ ምን ጎሎብሽ ተፈተንኩ ትያለሽ… ወይ ጉድ!>

< ጤናዬን አሟልቶ… እድሜዬን አስረዝሞ… ጥሩ ቤተሰብን ሰጥቶ… ፀጋውን አትረፍርፎ ፈተነኝ… እድሌ እንዳመጣው አስቤ እዘናጋ ይሆን ወይስ አመስጋኝ እሆን ለማየት ፈተነኝ…>

< በድሎት መፈተን ምነኛ የከበደ ፈተና ነው!>


መድ

67 viewsGlamor, 19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 11:22:18 #የኔ እይታ 29

አስታውሳለሁ ከ 2 አመት በፊት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለማለፍ ካለን ፍላጎት የተነሳ የማንተኛባቸው ለሊቶች ይበዙ ነበር። በግላችን ለሰአታት ስናነብ ቆይተን ሰብሰብ ብለን ደግሞ ከጓደኞቻችን ጋር ጥያቄወችን እንሰራለን። አንድ ቀን ከስብስባችን መሀል አንድ ጓደኛችን ለምን ይህን ያህል ዩኒቨርስቲ ለመግባት እንደምንፈልግ እያንዳንዳችንን መጠየቅ ጀመረ።
" እሺ አቡኪ ለምንድን ነው ይህን ያህል አይኖችህ እንቅልፍ እስኪያጡ ስታነብ የምታድረው?"አለው የትምርት ቤታችንን ጎበዝ ተማሪ
"ያው ዩኒቨርስቲ ገብቼ ለመማር ነዋ" አለ ትካሻውን እየሰበቀ
"ከዛስ?ማለቴ የምትማረው ለምንድን ነው?"
"ከተማርኩ እና በጥሩ መአረግ ከተማርቅኩ በኋላ ህልሜን እኖራለሁ፣ጥሩ ስራ እና ጥሩ ገቢ ይኖረኛል እና ደግሞ ጥሩ ሀብት አካብቼ ቤተሰቦቼንም እራሴንም እየደገፍኩ በደስታ እኖራለሁ"
"እሺ ዩሀንስ አንተስ?"አለው እያነበበ የነበረውን መፀሀፍ ከዘጋበት በኋላ
"ያው እኔም አቡኪ እንዳለው ተምሬ ቤተሰቦቼን እና እራሴን ለመርዳት ነው እና ደግሞ ጥሩ የሚባል ሂወት ለመኖር " አህላም እና አህመድ ሲቀሩ ሁላችንም በየተራ ተጠየቅን። የሁላችንም መልስ ተመሳሳይ ነበር።
"እሺ አህላም አንቺስ?"አላት የተለየ ነገር እንደማይሰማ በማሰብ ስልኩን እየነካካ
"አህላም ሂጃቦን እያስተካከለች እኔ አላህ ፈቅዶ የዩኒቨርስቲ ማለፊያ ውጤት ከመጣልኝ የዩኒቨርሲቲው ሰቃይ ተማሪ ሁኜ እዚህ ሀገር ላይ በየ ትምህርት ቤቱ ሂጃብ ለሚከለክሉ ሰወች ሂጃብ ከምንም እንደማያግደን ማሳየት እና በመልበሳቸው ምክንያት እየተሰቃዩ ላሉ ሙስሊም ሴቶች እስከዛሬ ካሳየሁት በላይ በእምነታችን ፀንተን ከቆየን አላህ ከሁሉም በላይ እንደሚያልቀን ዋንጫውን በልቼ ማሳየት ነው ፍላጎቴ"አለች ስሜታዊ በሆነ አነጋገር። ከዱንያ ምኞት ያለፈ ነገር በመስማታችን ተደስተን አጨበጨብን
" እሺ አህመድ አንተስ?"አለው የተሻለ ነገር ለመስማት እየተቁለጨለጨ
"እኔም አላህ ፈቅዶ ዩኒቨርስቲ ከገባየሁ በጥሩ ውጤት መመረቅ እና በተመረቅኩበት ሙያ ከኔ አልፎ ሀይማኖቴን ማገልገል ነው ፍላጎቴ " ብሎ ከመጨረሱ ዩሀንስ ቀበል ብሎ
"ሀይማኖቴን ማገልገል ስትል? ህክምና መማር አልነበር እንዴ የምትፈልገው ወይስ ዶክተር አህመድ ተብለህ መስጂድ አዛን ማለት ነው እቅድህ "ሲለው አህመድ ፈገግ ብሎ
"እንደዛ አይደለም ኢስላም ዱንያን ብቻ እንድንኖር ወይም ዱንያን ትተን ለአኼራ ብቻ እንድንኖር አይደለም የሚያዘው! ሙስሊም ዱንያውንም አኼራውንም እኩል የሚያስኬድ ነው! ለምሳሌ እኔ የምማረው አንድም እራሴን በእውቀት እና በኢኮኖሚ ለማሻሻል ሲሆን በዋናነት ደግሞ በተሰማራሁበት የስራ መስክ እምነቴን እያስተማርኩ እና ለአኼራዬ የሚጠቅም ስራ እየሰራሁ የሁለቱንም አለም ሂወቴን ለማስተካከል ነው። ሁሉም ነገር የአላህን ፊት ፈልገን ከሰራነው አጅር ያስገኝልናል። እኔ አሁን ለሊት ለጌታዬ መስገድ ስችል ሳነብ፣ቀን መስጂድ ዳዕዋ መስማት እየቻልኩ ላይብረሪ ስውል ለይል ሰላት ከሚሰግዱት እና ዳዕዋ ሲሰሙ ከሚውሉት ሰወች ጌታዬ ጋር ባለኝ ደረጃ አንሻለሁ ብዬ አላስብም! ምክንያቱም የምማረው ጥሩ የእውቀት እና የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ሁኜ እምነቴን ለማስፋፋት እና ከፍ ለማድረግ ነው። ያ ማለት መማሬ ኢባዳ ነው። ምን አልባት ፈተና ባላልፍ በማንበቤ አልቆጭም ምክንያቱም የጌታዬን እምነት ከፍ ለማድረግ በማንበቤ አጅር እንደማገኝ አውቃለሁ።" ብሎ ከተናገረ በኋላ ዩሀንስን ገብቶሀል በሚል ጀርባውን መታ አደረገው
"የሚገርም ነው! እና እኛስ እስከዛሬ እንደዚህ ብለን ያልነየትነው አጅር አናገኝም ማለት ነው?"አለ አቡበከር
"ከአሁን በኋላ ኒያችሁን ማስተካከል ትችላላችሁ! ስትማሩ ዱንያ ላይ ከምትመኙት ስኬት በላይ እምነታችሁን ለማገልገል( አኼራችሁ ላይም ስኬታማ ለመሆን)ተማሩ፣ ስራ ስትሰሩ እራሳችሁን ከመለወጥ አልፎ የሰወችን ሂወትም እንደምትቀይሩ ነይቱ ፣ስታገቡ ስሜታችሁን ለማርካት፣የምትወዱትን ሰው የራሳችሁ ለማድረግ እና ቤተሰባችሁን ለማስደሰት ከምታስቡት በተጨማሪ የረሱላችሁን መልዕክት ለመተግበር እና ለኡማው የሚጠቅም ትውልድ ለመፍጠር ነይታችሁ አግቡ፣ ቤት ስትገዙ ከኪራይ ነፃ ለመሆን እና ቤት ገዛ ለመባል ሳይሆን የአላህን እንግዶች ለመቀበል እና አላህን ማወደሻ ምቹ ቦታ ለማግኘት ነይታችሁ ግዙ፣ መኪና ስትገዙ ከታክሲ ሰልፍ ለመገላገል እና ሀብታም ለመባል ብቻ ሳይሆን የደከሙ እና የተቸገሩ ሰወችንም እሸኝበታለሁ ብላችሁ ነይቱ ፤ አጠቃላይ የምታደርጉትን ነገር ከጌታችሁ ውዴታን እና አጅርን ፈልጋችሁ ካደረጋችሁ ምንዳ ታገኙበታላችሁ።"ብሎ የማይረሳ እና ሂወታችንን የቀየረ ምክር መከረን። የዛን ቀን ሁላችንም ኒያችንን አስተካከልን። በእያንዳንዱ ሂወታችን ላይ የጌታችንን ውዴታ ልናስብ እና የምንማረው የተማረ ሙስሊም ሁነን ሀይማኖታችንን ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ነይተን ተለያየን። የዛን ቀን ከነበርነው ልጆች ግማሹ ዩኒቨርስቲ፣ግማሹ የግል ኮሌጅ፣ ግማሹ ደግሞ ወደ ስራ አለም ገብቷል። ኢንሻ አላህ ከጥቂት አመታት በኋላ ሁላችንም ዲናችንን በተሰማራንበት ሙያ እንደምናገለግን አምናለሁ።
የምታደርጉትን ነገር ሁሉ ለአላህ ብላችሁ አድርጉ ታተርፋላችሁ። ሀታ ባል እና ሚስት በሚያሳልፉት ግዜ እኮን አጅር እንደሚያገኙ ያስተማረ ዲን አይደል ያለን? ለአላህ ብለን የምንሰራው ስራማ....

rehima hussen

@rehimahu
@rehimahu
ለአስተያየትዎ
@rehimahubot
37 viewsGlamor, 08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 15:54:39
     ወደ ሱቁ እየገባች ነው……
ድምፇ ከፍ አድርጋ ትስቃለች
ቢያንስ 10 ሜትር ድረስ የሚያውድ እጣን ታጥናለች
ከንፈሯ ጠግቦ ሳይጠጣ ከቄራ የተባረረ ውሻ ይመስላል
ሰውነቷ ለማስታወቂያ በሚመስል መልኩ ተገላልጣለች

በሚቅለሰለስ ድምፅ ለባለ ሱቁ
  “ዋጋ የሚቀንሰው ርካሹ እቃ የትኛው ነው "
ብላ ጠየችው; 
ባለ ሱቁ ቀና ብሎ አያትና
.
.
.
.
.
       አንቺ!
49 viewsGlamor, 12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 10:24:33 (ተቀንጭቦ የቀረበ)

ፈገግ የሚያሰኝ እውነተኛ ገጠመኝ

ሟቹ "ጌታ!"
~~
ወሎ ውስጥ ነው። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል።
·
* ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ።
– "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት።
·
ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው
ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ
አይቶ ተመለሰ።
·
ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው።
* "እሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ።
– "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤
እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ።
·
አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ
የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ።
የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ
ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል።
·
* "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው።
– "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት።
* "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ።
– "አዎ" አሉት።
·
ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:–
"እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!!"

የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው።…
52 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, edited  07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 18:59:32 ስለ ፍቅር ልንገርህ.....

አሊይ ረ.ዐ ለሚስቱ ፋጢማ ያላት ጊዜ...

"በመፋቂያሽ ቀናሁ ከንፈርሽን
አልፎ ጥርስሽን ሲነካው.."
48 viewsGlamor, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 01:09:41
በትሬኒንጉም ብቅ ብለናል


አማና የወጣቶች ልማት ኔትዎርክ ( amana youth development network) በቢላሉል ሀበሽይ አዳራሽ ለተከታታይ 5 ቀናት ያዘጋጀውን ልዩ የ #project_cycle_manegmnet ስልጠና ዳሩል አርቀም ከ 6 አገር አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን 7 አመራሮቹን በዚህ ስልጠና ላይ አሳትፏል

ይህ ስልጠና በ ብቁ አሰልጣኞች ታግዞ 3ኛው ቀን ላይ የደረሰ ሲሆን በስልጠናው የተለያዩ ተሞክሮዎችን በመውሰድ አሰራራችንን በማዘመኑ ረገድ አንድ እርምጃ እየተጎዝን ነው ብለን እናስባለን :: ኢንሻ አላህ::
52 viewsibnu rebah, 22:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 18:17:54 ደስታ በድህነት እና በሀብት ላይ የተንጠለጠለ አይደለም። ደስታ ባለህ ነገር ተብቃቅተህ መደሰት ነው! ከዛም በላይ በነፍስያህና በሴጣን ምክንያት ነው ደስታን የምታጣው ወዳጄ እናማ ነፍሴንም አንተንም የምመክርህ ነፍስያህን ተቆጣት አላህን መፍራት አለማምዳት ወንጀልን እንድትርቅ አጥብቀህ ገስጻት ፤ የዛኔ ነፃ ትወጣለህ ደስታህም ይመለሳል::

ከትንሽ ጭማሪ ጋር copy የተደረገ!
51 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, edited  15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 17:20:53 አንዳንድ ህመሞች ነፍስ ላይ ናቸው በጣም የሚያም መናገር የሚከብድ ቃላት የለሽ ህመም ከራስህ እና ከሰው በቀር የሚያሳምምህ የለም፤ ከአላህ በቀር የሚያክምህ የለም ኢላሂ ነፍሴን ከነዛ አስቀው ከሚገድሉት፣ ገድለው ከሚጥሉት፣ ጥለው ከሚረግጡት እንዲሁም ከራሴ ወንጀል ጠብቀህ ቀጥተኛውን መንገድ ምራኝ ያረብብብብብብብብብብብብብ

አሚን


ከ ዘመናት በፊት፡ ከትንሽ ጭማሪ ጋር
29 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ