Get Mystery Box with random crypto!

አጅነቢን ስለመጨበጥ ብዙ ሰው ያለው አመለካከት ይገርማል አልጨብጥም ስላልክ ልክ እንደናቅካቸው ወይ | Bilal Media & Communication

አጅነቢን ስለመጨበጥ ብዙ ሰው ያለው አመለካከት ይገርማል አልጨብጥም ስላልክ ልክ እንደናቅካቸው ወይም እንዳዋረድካቸው ያስበሉ ለምን??
ይባስ ብሎም ሙስሊሙ ስለ አጅነቢ ያለው እይታ ገና ብዙ ስራ ይጠይቃል። አንድ ሰው አጂነቢ አልጨብጥም ካለ ልክ እንደ ዓሊም በጣም የቀራ ተደርጎም ይወሰዳል ይሄ ስህተት ነው ምንም ብዙ ከመቅራት ከዓሊምነት ጋር የሚያይዘው ነገር የለም።
ጃሂልም ቢሆን ዓሊም አጅነቢን መጨበጥ ሃራም እንደሆነ ካወቁ መተግበር ግድ ይላቸዋል ምክኒያቱም ህጉ ለሁለቱም ስለሚሰራ።
ነብያችን ( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ) በዚህ ዙሪያ ምን እንደተናገሩ እንመልከት:-
” ﻷﻥ ﻳﻄﻌﻦ ﻓﻲ ﺭﺃﺱ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﺑﻤﺨﻴﻂ ﻣﻦ ﺣﺪﻳﺪ ﺧﻴﺮ
ﻟﻪ ﻣﻦ ﺃﻥ ﻳﻤﺲ ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻻ ﺗﺤﻞ ﻟﻪ ”
“የማትፈቀድለትን ሴት ከሚነካ የአንደኛችሁ ጭንቅላት
በብረት መርፌ ቢወጋ ይሻለዋል።” (ጦበራኒ ዘግበውታል)
ነገር ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ቡዙ መስሊም ወንዶችና
ሴቶች የማይፈቀድላቸውን ሰዎች በመጨበጥ እራሳቸውን
እየበደሉ ይገኛሉ። አልፎ ተርፎም ከወንጀሉ የበለጠ የሚያስጠሉ ምክንያቶችን ይደረድራሉ ለናሙና ያህል:-
* “ልባችን ንፁህ ናት” ይላሉ! የነዚህ ሰዎች ልብ ከነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ልብ የበለጠ ንፁህ ናትን? ለመሆኑ በዚህ ዓለም ላይ ከነቢዩ(ﷺ) የበለጠ ልቡ ንፁህ የሆነ ሰው አለ? ከርሳቸው በላይ ልቡ መልካም ነገር የሚያስብ ሰው አለን?
* “ይህንን መተው ለኛ ሀገር ይከብዳል” ይላሉ እስልምና የመጣው ነብያችንም ( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ) የተላኩት ለዓለም እንጂ ለሳውዲ፣ ለኢትዮጲያ፣ ለዓረብ፣ ለፈረንጅ፣ ለጥቁር ለሀብታም፣ ለድሀ ብለው በመለየት አይደለም አላህ እንዲህ ይላል:-
ﻭﻣﺎ ﺃﺭﺳﻠﻨﺎﻙ ﺇﻻ ﺭﺣﻤﺔ ﻟﻠﻌﺎﻟﻤﻴﻦ
“ለዓለማት እዝነት ቢሆን እንጂ አላክንህም”
ስለዚህ ሸሪዓችን ማንንም ሳይለይ ሁሉንም ይመለከታል! እስቲ ሁላችንም አንዴ ቆም ብለን እናስተውል በሚስማር ጭንቅላታችን ተወግቶ በአንድ ጎን ገብቶ በሌላ ጎን ቀዶ
መውጣቱ የማትፈቀድን ሴት ከመጨበጥ ይሻላል መባሉ
አያሰደነግጥምን? አላህ እርሱን የሚፈራ ልብ ይስጠን!!

#Share
#Share
#Share

https://t.me/twhidfirstt
https://t.me/twhidfirstt