Get Mystery Box with random crypto!

#የኔ እይታ 29 አስታውሳለሁ ከ 2 አመት በፊት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለማለፍ ካለን ፍላጎት | Bilal Media & Communication

#የኔ እይታ 29

አስታውሳለሁ ከ 2 አመት በፊት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለማለፍ ካለን ፍላጎት የተነሳ የማንተኛባቸው ለሊቶች ይበዙ ነበር። በግላችን ለሰአታት ስናነብ ቆይተን ሰብሰብ ብለን ደግሞ ከጓደኞቻችን ጋር ጥያቄወችን እንሰራለን። አንድ ቀን ከስብስባችን መሀል አንድ ጓደኛችን ለምን ይህን ያህል ዩኒቨርስቲ ለመግባት እንደምንፈልግ እያንዳንዳችንን መጠየቅ ጀመረ።
" እሺ አቡኪ ለምንድን ነው ይህን ያህል አይኖችህ እንቅልፍ እስኪያጡ ስታነብ የምታድረው?"አለው የትምርት ቤታችንን ጎበዝ ተማሪ
"ያው ዩኒቨርስቲ ገብቼ ለመማር ነዋ" አለ ትካሻውን እየሰበቀ
"ከዛስ?ማለቴ የምትማረው ለምንድን ነው?"
"ከተማርኩ እና በጥሩ መአረግ ከተማርቅኩ በኋላ ህልሜን እኖራለሁ፣ጥሩ ስራ እና ጥሩ ገቢ ይኖረኛል እና ደግሞ ጥሩ ሀብት አካብቼ ቤተሰቦቼንም እራሴንም እየደገፍኩ በደስታ እኖራለሁ"
"እሺ ዩሀንስ አንተስ?"አለው እያነበበ የነበረውን መፀሀፍ ከዘጋበት በኋላ
"ያው እኔም አቡኪ እንዳለው ተምሬ ቤተሰቦቼን እና እራሴን ለመርዳት ነው እና ደግሞ ጥሩ የሚባል ሂወት ለመኖር " አህላም እና አህመድ ሲቀሩ ሁላችንም በየተራ ተጠየቅን። የሁላችንም መልስ ተመሳሳይ ነበር።
"እሺ አህላም አንቺስ?"አላት የተለየ ነገር እንደማይሰማ በማሰብ ስልኩን እየነካካ
"አህላም ሂጃቦን እያስተካከለች እኔ አላህ ፈቅዶ የዩኒቨርስቲ ማለፊያ ውጤት ከመጣልኝ የዩኒቨርሲቲው ሰቃይ ተማሪ ሁኜ እዚህ ሀገር ላይ በየ ትምህርት ቤቱ ሂጃብ ለሚከለክሉ ሰወች ሂጃብ ከምንም እንደማያግደን ማሳየት እና በመልበሳቸው ምክንያት እየተሰቃዩ ላሉ ሙስሊም ሴቶች እስከዛሬ ካሳየሁት በላይ በእምነታችን ፀንተን ከቆየን አላህ ከሁሉም በላይ እንደሚያልቀን ዋንጫውን በልቼ ማሳየት ነው ፍላጎቴ"አለች ስሜታዊ በሆነ አነጋገር። ከዱንያ ምኞት ያለፈ ነገር በመስማታችን ተደስተን አጨበጨብን
" እሺ አህመድ አንተስ?"አለው የተሻለ ነገር ለመስማት እየተቁለጨለጨ
"እኔም አላህ ፈቅዶ ዩኒቨርስቲ ከገባየሁ በጥሩ ውጤት መመረቅ እና በተመረቅኩበት ሙያ ከኔ አልፎ ሀይማኖቴን ማገልገል ነው ፍላጎቴ " ብሎ ከመጨረሱ ዩሀንስ ቀበል ብሎ
"ሀይማኖቴን ማገልገል ስትል? ህክምና መማር አልነበር እንዴ የምትፈልገው ወይስ ዶክተር አህመድ ተብለህ መስጂድ አዛን ማለት ነው እቅድህ "ሲለው አህመድ ፈገግ ብሎ
"እንደዛ አይደለም ኢስላም ዱንያን ብቻ እንድንኖር ወይም ዱንያን ትተን ለአኼራ ብቻ እንድንኖር አይደለም የሚያዘው! ሙስሊም ዱንያውንም አኼራውንም እኩል የሚያስኬድ ነው! ለምሳሌ እኔ የምማረው አንድም እራሴን በእውቀት እና በኢኮኖሚ ለማሻሻል ሲሆን በዋናነት ደግሞ በተሰማራሁበት የስራ መስክ እምነቴን እያስተማርኩ እና ለአኼራዬ የሚጠቅም ስራ እየሰራሁ የሁለቱንም አለም ሂወቴን ለማስተካከል ነው። ሁሉም ነገር የአላህን ፊት ፈልገን ከሰራነው አጅር ያስገኝልናል። እኔ አሁን ለሊት ለጌታዬ መስገድ ስችል ሳነብ፣ቀን መስጂድ ዳዕዋ መስማት እየቻልኩ ላይብረሪ ስውል ለይል ሰላት ከሚሰግዱት እና ዳዕዋ ሲሰሙ ከሚውሉት ሰወች ጌታዬ ጋር ባለኝ ደረጃ አንሻለሁ ብዬ አላስብም! ምክንያቱም የምማረው ጥሩ የእውቀት እና የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ሁኜ እምነቴን ለማስፋፋት እና ከፍ ለማድረግ ነው። ያ ማለት መማሬ ኢባዳ ነው። ምን አልባት ፈተና ባላልፍ በማንበቤ አልቆጭም ምክንያቱም የጌታዬን እምነት ከፍ ለማድረግ በማንበቤ አጅር እንደማገኝ አውቃለሁ።" ብሎ ከተናገረ በኋላ ዩሀንስን ገብቶሀል በሚል ጀርባውን መታ አደረገው
"የሚገርም ነው! እና እኛስ እስከዛሬ እንደዚህ ብለን ያልነየትነው አጅር አናገኝም ማለት ነው?"አለ አቡበከር
"ከአሁን በኋላ ኒያችሁን ማስተካከል ትችላላችሁ! ስትማሩ ዱንያ ላይ ከምትመኙት ስኬት በላይ እምነታችሁን ለማገልገል( አኼራችሁ ላይም ስኬታማ ለመሆን)ተማሩ፣ ስራ ስትሰሩ እራሳችሁን ከመለወጥ አልፎ የሰወችን ሂወትም እንደምትቀይሩ ነይቱ ፣ስታገቡ ስሜታችሁን ለማርካት፣የምትወዱትን ሰው የራሳችሁ ለማድረግ እና ቤተሰባችሁን ለማስደሰት ከምታስቡት በተጨማሪ የረሱላችሁን መልዕክት ለመተግበር እና ለኡማው የሚጠቅም ትውልድ ለመፍጠር ነይታችሁ አግቡ፣ ቤት ስትገዙ ከኪራይ ነፃ ለመሆን እና ቤት ገዛ ለመባል ሳይሆን የአላህን እንግዶች ለመቀበል እና አላህን ማወደሻ ምቹ ቦታ ለማግኘት ነይታችሁ ግዙ፣ መኪና ስትገዙ ከታክሲ ሰልፍ ለመገላገል እና ሀብታም ለመባል ብቻ ሳይሆን የደከሙ እና የተቸገሩ ሰወችንም እሸኝበታለሁ ብላችሁ ነይቱ ፤ አጠቃላይ የምታደርጉትን ነገር ከጌታችሁ ውዴታን እና አጅርን ፈልጋችሁ ካደረጋችሁ ምንዳ ታገኙበታላችሁ።"ብሎ የማይረሳ እና ሂወታችንን የቀየረ ምክር መከረን። የዛን ቀን ሁላችንም ኒያችንን አስተካከልን። በእያንዳንዱ ሂወታችን ላይ የጌታችንን ውዴታ ልናስብ እና የምንማረው የተማረ ሙስሊም ሁነን ሀይማኖታችንን ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ነይተን ተለያየን። የዛን ቀን ከነበርነው ልጆች ግማሹ ዩኒቨርስቲ፣ግማሹ የግል ኮሌጅ፣ ግማሹ ደግሞ ወደ ስራ አለም ገብቷል። ኢንሻ አላህ ከጥቂት አመታት በኋላ ሁላችንም ዲናችንን በተሰማራንበት ሙያ እንደምናገለግን አምናለሁ።
የምታደርጉትን ነገር ሁሉ ለአላህ ብላችሁ አድርጉ ታተርፋላችሁ። ሀታ ባል እና ሚስት በሚያሳልፉት ግዜ እኮን አጅር እንደሚያገኙ ያስተማረ ዲን አይደል ያለን? ለአላህ ብለን የምንሰራው ስራማ....

rehima hussen

@rehimahu
@rehimahu
ለአስተያየትዎ
@rehimahubot