Get Mystery Box with random crypto!

(ተቀንጭቦ የቀረበ) ፈገግ የሚያሰኝ እውነተኛ ገጠመኝ ሟቹ 'ጌታ!' ~~ ወሎ ውስጥ ነው። አን | Bilal Media & Communication

(ተቀንጭቦ የቀረበ)

ፈገግ የሚያሰኝ እውነተኛ ገጠመኝ

ሟቹ "ጌታ!"
~~
ወሎ ውስጥ ነው። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል።
·
* ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ።
– "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት።
·
ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው
ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ
አይቶ ተመለሰ።
·
ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው።
* "እሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ።
– "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤
እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ።
·
አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ
የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ።
የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ
ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል።
·
* "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው።
– "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት።
* "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ።
– "አዎ" አሉት።
·
ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:–
"እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!!"

የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው።…