Get Mystery Box with random crypto!

Bilal Media & Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication B
የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication
የሰርጥ አድራሻ: @linkbi7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-12-13 21:53:03 "የቤቴ ና የመፅሀፌ ጓደኛ ከመሆኔ በፊት የህይወትን ጥፍጥና ቀምሼ አላውቅም ነበር" ይላሉ ቃዲ ኢብን አብዱል አዚዝ አል ጁርጃኒ
16 viewsGlamor, 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 07:23:25 ግጥም እና ወግ ( ረሂማ ሁሴን)
ጥበብ የሙስሊም ሀብት ናት! ካገኘባት ቦታ ይውሰዳት ረሱል(ሰ.ዐ.ወ)

ጥበበኛው ጌታ የሰጠኝን ሂክማ ተጠቅሜ እይታወቼን እና ሀሳቦቼን በግጥም እና በወግ አዚህ ቻናል ላይ አጋራችኋለሁ።
.
.ተቀላቀሉን

ለአስተያየትዎ @rehimahubot
https://t.me/rehimahu
30 viewsGlamor, 04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 08:25:35
7 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 21:06:13 ቢያጧቹ ግድ ለማይኖራቸው፣ባጣ ቆዩኝ ለሚያደርጓችሁ ወይም እንደአማራጭ ለሚያስቀምጧችሁ ነፍሶች ራሳችሁን ከማርገድ ተቆጠቡ። እናንተ ውድ ናችሁ፣ ከውድነታችሁ በላይ ተመን የለሽ ልብ እናንተው ጋር አለና be careful ስለዚህ ውድ ነገር!
(አብድልቃድር ኑር)
20 viewsGlamor, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 20:58:48 ሌላኛው የሚጠቅሱት “ማስረጃ” በታዋቂ ዑለማዎች ማስፈራራት ነው። ቁርኣንና ሐዲሥ ስትጠቅሱላቸው እነሱ “ነወዊይ፣ ኢብኑ ሐጀር፣…” ይላሉ። ከቁርኣንና ሐዲሥ በተቃራኒ ፍፁም ያልሆኑ ሰዎችን ማጣቀስ ነውር ነው። “እናንተ ቁርኣኑንና ሐዲሡን ከነሱ በላይ ልታውቁት ነወይ?” ይላሉ። መልካም! እነሱስ ቁርኣኑንና ሐዲሡን ከሰለፎች በላይ ሊያውቁት ነወይ? እስኪ የሰለፎቹን ተፍሲር መርምሩና አደብ ይኑራችሁ።
የአሕ -ባሽ አቋም ሌላው ቀርቶ “እንከተላቸዋለን” ከሚሏቸው የአቡል ሐሰን አልአሽዐሪ አቋም ጋር እንኳን አይገጥምም፡፡ አቡል ሐሰን የአህሉ ሱና፞ን ዐቂዳ ሲዘረዝሩ እንዲህ ብለዋል፡-
وأن الله سبحانه على عرشه كما قال: الرحمن على العرش استوى وأن له يدين بلا كيف كما قال: خلقت بيدي وكما قال: بل يداه مبسوطتان.
“የጠራው አላህ ‘አረ፞ሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ’ እንዳለው በዐርሹ ላይ ነው። ሁለት እጆች እንዳሉትም እንዲሁ ያለ አኳኋን (ያፀድቃሉ)። ‘በሁለት እጆቼ ፈጠርኩ’ እንዳለው፤ ‘ይልቁንም ሁለት እጆቹ የተዘረጉ ናቸው’ እንዳለውም (እንዲሁ ያፀድቃሉ)።” [መቃላቱል ኢስላሚዪ፞ን፡ 290]
ከዚያም የአህሉ ሱና፞ን አቋም በሰፊው ከዘረዘሩ በኋላ “እነዚህ ባጠቃላይ (የሱና፞ ሰዎች) የሚያዝዙባቸው፣ የሚተገብሯቸውና የሚያምኑባቸው ናቸው። በዘረዘረነው አቋማቸው ሁሉ እናምናለን። እንጓዝበታለንም” ብለው ቋጭተዋል። [መቃላት፡ 297]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር፡ 12/2012)
37 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 20:58:47 እውን አላህ እጅ የለውም?
~
ህሊና ላለው ሰው “አላህ እጅ የለውም” የሚል እምነት አስቀያሚና እጅጉን የሚያሳፍር ነው። ግና አእምሯቸው በእምነት የለሾች ፍልስፍና በመበከሉ የተነሳ ይህንን አጉል እምነት ተውሒድ ያደረጉ፣ ይባስ ብሎም ያልተጋራቸውን በሙሽ^ሪክነት የሚወነጅሉ አንጃዎች ተፈልፍለዋል። በዘመናችን ይህንን ጥፉ አመለካከት ከሚያራምዱ አንጃዎች ውስጥ “አሕ -ባሽ” ፊታውራሪ ነው። ይህ የአሕ -ባሽ አመለካከት ከሙዕተዚላ የተኮረጀ እምነት ነው። ለዚህም ሁለት አይነት መረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል።
1ኛ፡- የሙዕተዚላዎችን ስራዎች። ለምሳሌ የቃዲ ዐብዱል ጀባር አልሙዕተዚሊን ስራዎች። [ሸርሑ ኡሱሊል ኸምሳ፡ 228] [ሙተሻቢሁል ቁርኣን፡ 231]
2ኛ፡- አሕ -ባሾች እንከተላቸዋለን የሚሏቸው ኢማሞች ምስክርነት። ለምሳሌ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪና አቡ መንሱር አልበግዳዲ ይህ እምነት የሙዕተዚላ ዐቂዳ እንደሆነ መስክረዋል። [መቃላቱል ኢስላሚዪ፞ን፡ 157፣ 167] [ኡሱሉዲን፡ 228]
ስለ ራሱም ይሁን ስለሌሎች ከማንም በላይ አዋቂ የሆነው ጌታ ግን እጅ እንዳለው በግልፅ ቋንቋ ይናገራል። መልእክተኛውም ﷺ እንዲሁ። ጥቂት ማስረጃዎችን እንመልከት፡-
(قَالَ یَـٰۤإِبۡلِیسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسۡجُدَ لِمَا خَلَقۡتُ بِیَدَیَّۖ )
{ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ?} [ሷድ፡ 75]
ከዚች አንቀፅ አባታችን ኣደም በአላህ እጆች የተፈጠሩ ክቡር ፍጡር እንደሆኑ ማንም ይረዳል፡፡ አሕ -ባሽ ሲቀር። እነሱ ግን “እጅ”/ “የድ” የሚለውን “ችሎታ / ፀጋ ማለት ነው” ይላሉ።
- ለችሎታማ ሁሉም የተፈጠረው በአላህ ችሎታ ነው። እዚህ ላይ በልዩ ሁኔታ አክብሮ እንደፈጠራቸው ሲናገር ነው “በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት” ማለቱ። የ“እጅ” ትርጓሜው “ችሎታ” ቢሆን ኖሮ ኣደም ከኢብሊስ ልዩነት ባልነበራቸው ነበር። ኢብሊስም በአላህ ችሎታ የተፈጠረ ነውና።
- እጅ ማለት ችሎታ ቢሆን ኖሮ {በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት} ሲለው ኢብሊስ “እኔስ በችሎታህ አይደል የተፈጠርኩት?” ይል ነበር። ግን አላለም። ከኢብሊስ ከፍ ብለህ አስብ እንጂ!!
አዎ የጥፋት ቁንጮው ኢብሊስ በአላህ እጆች አልካደም። “የለም! በእጆችህ አልፈጠርከውም። ሲጀመር እጅ የት አለህና?!” አላለም!! “ከኛ ወዲያ ተውሒድ አዋቂ ላሳር” የሚሉ አሕ -ባሾች ግን “እጅ የለውም” ሲሉ ኢብሊስ እንኳን ያልደፈረውን ጥፋት እየፈፀሙ ነው።

ሌላ ማስረጃ፡-
(وَقَالَتِ ٱلۡیَهُودُ یَدُ ٱللَّهِ مَغۡلُولَةٌۚ غُلَّتۡ أَیۡدِیهِمۡ وَلُعِنُوا۟ بِمَا قَالُوا۟ۘ بَلۡ یَدَاهُ مَبۡسُوطَتَانِ یُنفِقُ كَیۡفَ یَشَاۤءُۚ)
{አይሁዶችም “የአላህ እጅ የተጠፈረች ናት” አሉ። እጆቻቸው ይጠፈሩ!! ይልቅ ሁለቱም እጆቹ የተዘረጉ ናቸው። እንደሚሻ ይለግሳል፡፡} [ማኢዳህ፡ 64]
አስተውሉ! አይሁዶቹ የተረ-ገሙት “የአላህ እጅ የተጠፈረች ናት” በማለታቸው እንጂ ከነ ጭራሹ “አላህ እጅ የለውም” ብለው አይደለም። አሕ -ባሾችስ? አይሁዳውያን ያልተዳፈሩትን እንኳን በመሻገር ጭራሽ ለአላህ እጅ መኖሩን አስተባብለዋል።
በሐዲሥም ከነብዩ ﷺ የተላለፉ ብዙ ማስረጃዎች አሉ። ለምሳሌ፡-
يُجْمَعُ المُؤْمِنُونَ يَوْمَ القِيَامَةِ فَيَقُولُونَ: لَوِ اسْتَشْفَعْنَا إِلَى رَبِّنَا فَيُرِيحُنَا مِنْ مَكَانِنَا هَذَا، فَيَأْتُونَ آدَمَ فَيَقُولُونَ لَهُ: أَنْتَ آدَمُ أَبُو البَشَرِ، خَلَقَكَ اللَّهُ بِيَدِهِ، وَأَسْجَدَ لَكَ المَلاَئِكَةَ، وَعَلَّمَكَ أَسْمَاءَ كُلِّ شَيْءٍ فَاشْفَعْ لَنَا إِلَى رَبِّنَا حَتَّى يُرِيحَنَا
{በቂያማ ቀን አማኞች ይሰበሰቡና ‘ወደ ጌታችን አማላጅ ብንልክና ከዚህ ቦታችን ቢያሳርፈን’ ይላሉ። ከዚያም ኣደም ዘንድ ይመጡና ‘አንተ የሰው ዘር ሁሉ አባት የሆንከው ኣደም ነህ። አላህ #በእጁ ፈጥሮሃል። መላእክትን አሰግዶልሃል። የሁሉን ነገር ስሞችም አስተምሮሃል። ያሳርፈን ዘንድ ጌታችን ዘንድ አማልደን’ ይላሉ። … } [ቡኻሪ፡ 7516]
يَأْخُذُ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ سَمَاوَاتِهِ وَأَرَضِيهِ بِيَدَيْهِ، فَيَقُولُ: أَنَا اللهُ - وَيَقْبِضُ أَصَابِعَهُ وَيَبْسُطُهَا - أَنَا الْمَلِكُ " …
{አላህ - ዐዘ ወጀል - ሰማያቱንና ምድሮቹን #በሁለት_እጆቹ ይይዝና ‘እኔ ነኝ አላህ! - ጣቶቻቸውን እየጨበጡና እየዘረጉ- እኔ ነኝ ንጉሱ’ ይላል።} … [ሙስሊም፡ 2788]
አያዎችንና ሐዲሦችን በዚህ ላይ ልግታ። ለማሳጠር ስል የሰለፎችን ንግግርም አላካትትም። እውነታው እንደ ፀሐይ ፍንትው ብሎ ሳለ የሚጨናበሱ ሰዎች መኖራቸው የቢድዐ ዳፍንት ምን ያክል ከባድ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። “አሕ -ባሾችስ ለአቋማቸው ማጠናከሪያ ምን ይጠቅሳሉ?” ካላችሁ “እጅ የለውም” የሚል ቀጥተኛ ማስረጃ መቼም አያመጡም። የሚጠቅሱት ሁለት ማምታቻ ነው።

[ማምታቻ አንድ]፡-

“የሚመስለው የለም” የሚለውንና መሰል አንቀፆችን በመጥቀስ ከሶሐቦች ያልተገኘ የራሳቸውን ትርጉም መስጠት። “ምን አገናኘው?” ካላችሁ እነሱ ዘንድ “እጅ አለው” ማለት ማመሳሰል ነው። በቃ! “እንዲያ ከሆነ ቁርኣኑ የማመሳሰልና የሺርክ ሰነድ ነው ማለት ነው” ብትሏቸው ምንም ሳያፍሩ “አዎ ዟሂሩ ኩ^ፍ^ር ነው” ይላሉ። እንዲያ ከሆነ የመጀመሪያ አመሳሳዮች አላህና መልእክተኛው ናቸው ማለት ነው!! አዑዙ ቢላህ! ሐቂቃው ግን አላህን እራሱን በገለፀበት፣ ነብዩም ﷺ አላህን በገለፁበት መግለፅ ፈፅሞ ማመሳሰል አለመሆኑ ነው። የቡኻሪ ሸይኽ የሆኑት ኢማም ኑዐይም ብኑ ሐማድ ረሒመሁላህ የተናገሩትን ተመልከቱ፡-
مَنْ شَبَّهَ اللَّهَ بِشَيْءٍ مِنْ خَلْقِهِ فَقَدْ كَفَ-رَ وَمَنْ أَنْكَرَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ فَقَدْ كَفَ-رَ فَلَيْسَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ وَرَسُولُهُ تَشْبِيهٌ
“አላህን ከፍጡሩ በየትኛውም ያመሳሰለ በርግጥም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበትን የካደም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበት እና መልእክተኛው (እሱን የገለፁበት) ማመሳሰል አይደለም።” [ላለካኢ፡ ቁ. 936]
ይሄ የኑዐይም ንግግር በአላህ መገለጫዎች ዙሪያ ቁልፍ የሆነ ቀመር ነው። ከውስጡ ሶስት ወሳኝ ህጎችን እናገኝበታለን። እነሱም፡-
1ኛ፡- አላህን በፍጡር ማመሳሰል ክህ -ደት ስለሆነ መጠንቀቅ እንደሚገባ።
2ኛ፡- አላህ እራሱን የገለፀበትን ማስተባበል ክህ -ደት እንደሆነ።
3ኛ፡- በቁርኣንና በሐዲሥ ውስጥ ፈፅሞ ማመሳሰል እንደሌለ። (አሕ -ባሽ ግን ቁርኣንና ሐዲሥ በማመሳሰል የታጨቀ ነው ብለው ነው የሚያምኑት።)

[ማምታቻ ሁለት]፡-
33 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 17:38:38
ፈገግ በሉ........
44 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 20:14:56 በታሪክ ትልቁ ይቅርታ
...

አቡ ዘር ቢላልን ‹አንተ የጥቁር ልጅ!› በማለት ወረፈው፡፡

ቢላል በአቡ ዘር ንግግር ተቆጣ፣ በእጅጉ  አዘነም፡፡ ይህን ጉዳይ ለአላህ መልዕክተኛ ነው የምናገረው በማለት ወደርሣቸው ሄደ፡፡

በሰሙት ነገር የአላህ መልዕክተኛ ፊት በአንዴ ተለዋወጠ፡፡ እንዴት በእናቱ ታነውረዋለህ!፣ አንተ ገና የመሃይምነት ቅሪት ከዉስጥህ አልወጣም፡፡› ሲሉ ወቀሱት ለአቢ ዘርን፡፡

አቢ ዘር የሠራው ስህተት ከባድ መሆኑ ተገለጠለት፡፡ አለቀሰም፡፡

የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ‹አጥፍቻለሁ ምህረት ይለምኑልኝ!› አላቸው፡፡

እያለቀሠም ከመስጂዱ ወጣ፡፡

ሄደና ቢላል እግር ሥር ወደቀ፡፡ ጉንጩንም ከአፈር አገናኘ፡፡

‹አንተ የተከበርክ፤ እኔ ወራዳ ነኝ፡፡ በእግርህ ፊቴ ላይ ካልቆምክ በስተቀር ፈጽሞ አልነሳም› አለው፡፡

ቢላልም እንዲህ አለ ‹ በአላህ እምላለሁ፤ በእግሬ ለአላህ ብላ ሱጁድ ያደረገች ፊት ላይ አልቆምም፡፡›

አቡ ዘር ከተደፋበት ተነሳ፡፡ ተቃቅፈው አለቀሱ፡፡ ይቅርም ተባባሉ፡፡

እኛስ በወንድሞቻችን ላይ ስንቴ ድንበር አልፈናል! ስንቴስ አጥፍተናል!፡፡

ስላጠፋነው ጥፋት ይቅርታ ጠይቀን እናውቅ ይሆን!!

ዘረኝነት ክፉ ደዌ ነው!
123 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 19:07:21
ምንም ልል አይደለም...ፎቶውንም ሳላካፍላችሁ ማለፍ አልሆነልኝም። ምድር ላይ ለሴት ከአባቷ የበለጠ ወንድ ሊወዳት የሚችል አይመስለኝም። ቁጣው፣ ጩኸቱ ሁሉ ከክፉው ትጠበቅለት ዘንድ ነው። የሰርጓ ቀን ምን ያኽል ስጋው ከአካሉ እንደሚለያይ እራሱ ያውቀዋል። ሲድራትም እሷ ሳታውቅ ስንት አጣርቶ...በሱ አይን ለልጄ ይሆናታል የሚለውን በደንብ ከቃኘ ኋላ ነው።
እናም የአባቷን የልብ አፀድ...የአይን አበባ... እንዲሁ አታድርቃት...ብትችል ለማበቧ ሰበብ ሁን...ካልሆነም ከነበረችበት ትኮሰምን ዘንድ አትፍቀድ ባል ሆይ!
(ነጃት ሀሰን)
:
✎የፍቅር ጥቅሶች||
29 viewsGlamor, 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 06:41:14 "የአማኝ ነገር ይገርማል ሁሉም ነገር ለእሱ መልካም ነው"
--የአላህ መልክተኛ(ﷺ)--
9 viewsGlamor, 03:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ