2022-10-28 23:15:24
ዑመር ሞቷል? አልሞተም? የህፃኑ ጥያቄ
ዛሬ ሚስቴ በሩን ስትከፍትልኝ ፊቷ ላይ የሀዘን ድባብ ይታያል።
"ምን ተፈጠረ?"አልኳት።"ልጁ,,," አለችኝ።በፍጥነት ወደ ሶስቱ ልጆቼ ክፍል አመራሁ።አንገቱን ሰብሮ አልጋው ላይ ቁጭ ብሏል።እንባወቹ ትንንሽ ጉንጮቹን አርሰውታል።እቅፍ አድርጌ "ምን ሆንክብኝ ልጄ?!" አልኩት።መልስ ሊሰጠኝ አልፈቀደም።ግንባሩን በጄ ደባበስኩ፤አልታመመም።ጥያቄየን ለእናቱ ደገምኩላት ምን ሆኖ ነውበእምቢታዋ ፀናች።ህፃኑ ፊት መናገር እንዳልፈለገች ስረዳ ወደኛ መኝታ ክፍል እንድትሄድ ጠቆምኳት።ህፃኑን ደበስበሰ አድርጌ ወደሷ ዘንድ ሄድኩ።ዛሬ የገጠማትን ስትነግረኝ በደንብ ገባኝ።የታሪኩን መጀመሪያ እሷም አታውቀውም ነበር።የመጨረሻውን ክፍል ብቻ ነው ያየችው።ሙሉ ታሪኩን ባጭሩ እንዲህ አጫወትኳት።
፠ ሁሌ ከመተኛቴ በፊት ከሶስቱ ልጆቼ ጋር ማምሸት ያስደስተኝ ነበር።ረዥሙን ሰውነቴን አጭሯ አልጋቸው ላይ አሳርፌ ከመሀከላቸው ስሆን የሚሰማኝ ደስታ ልክ የለውም።እነሱም በጣም ይደሰታሉ።ታዲያ ታሪክ ሳላወራላቸው በፊት አይተኙም ነበር።አስማ ስለነቢዩሏህ ዩሱፍ ሰምታ አጠግብም፤ፋጢማ ደግሞ ስለ ነቢዩሏህ ሙሳና ፊርዐውን ወይም በሷ አጠራር ስለመልካሙ ሰውየና ስለ መጥፎው ሰው።ህፃኑ ልጄ ግን የተወራለትን ታሪክ ሁሉ በስርአት ያዳምጥ ነበር።
አንድ ምሽት እንደተለመደው የሙሳ ወይስ የዩሱፍ ስል ሁለቱ የየራሳቸው ምርጫ እንዳወራላቸው ሲወተውቱኝ ህፃኑ ልጄ
"_#ስለ_ዑመር_ብኑል_ኸጧብ "
በማለት አስደመመኝ።እንዴት ዑመርን አወቀው?! በፍጹም ስለዑመር ታሪክ አውቼለት አላውቅ!!! ኧረ እንዲያውም ስሙን እንኳ እሱ ፊት ጠርቼ አላውቅም።ለማንኛውም እንዳይከፋ ብዬ ትዝ ያለኝን ታሪክ አወራሁለት።በሌሊት ተነስተው ከተማውን ሲያስሱ አንዲት ልጆቿን ለማስተኛት ምግብ አስመስላ ውሃ እያበሰለቸ ያለችን ሴት አይቶተው እያለቀሱ ተመልሰው በወገባቸው ዱቄት ተሸክመው ራሳቸው አብስለው እንደመገቧቸው ነገርኩት።ደስ ብሎት ተኛ።
በማግስቱ"ዛሬ እኔ ነኝ የምተርክላችሁ" አለ።"እርግጠኛ ነህ?"አልኩት እየቀለድኩ።"አወ" ሲል መለሰል በኩራት መንፈስ።ትላንት ያወራሁለትን ታሪክ ቅንጣት ሳያዛንፍ እንደ ሪከርደር ደገመልኝ።በጣም ገረመኝ።በሚቀጥለው ቀን ስለዑመር እንዳወራለት በጠየቀኝ መሰረት የግብፅ አስተዳደር የነበረው የዐምር ብኑል ዓስ ልጅ የመታው ግብፃዊ ዑመር ጋ ሄዶ ሲከሰው ዑመር ዐምርንም ልጁንም አስመጥተው ቂሷሱን እንዲከፍል እንዳደረጉት ነገርኩት።
በዚህ መልኩ ወር አካባቢ አሳለፍን።አንዳንዴ ስለ ዑመር ተቅዋ
–ሌላ ጊዜ ስለ ፍትሀዊነቱ
–አልፎ አልፎ ስለ ጀግንነቱ ስለ ዙህዱ አወራለት ነበር።አንድ ምሽት "ዑመር ሞቷልን?"ሲል ጠየቀኝ።"አወ"ልለው አሰብኩና ልቡ በዑመር ፍቅር እንደተሞላ አስብኩና መልስ ሳልሰጠው ወጣሁ።በማግስቱ ጥያቄውን ደገመልኝ።አሁንም አረሳስቼ ወጣሁ።ከዛን ቀን በሁዋላ ከልጄ ጥያቄ ለመሸሽ ስል ከልጆቼ ጋ የማምሸት ልምዴን አቆምኩ።
ዛሬ ከእናቱ ጋር ወደ ከተማ ሲወጡ አንዲት ህፃን ልጅ የታቀፈች ሴት ልጇን የምታበላበት ሳንቲም እንዲሰጧት ሰወችን ስትለምን አየ።ህፃኑም "አይዞሽ! አሁን ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ለንቺም ለልጅሽም ምግብ ይዞልሽ ይመጣል" አላት።በአካባቢው የነበሩ ሰወች በግርምት እናቱና እሱ ላይ አፈጠጡባቸው።እናቱም የተወሰነ ብር ለሴትዮዋ ካስጨበጠቻት በሁዋላ ልጁን ይዛ ከአካባቢው ተሰወረች።ትንሽ እንደሄዱ አንድ ጡንቻው የፈረጠመ ሰው አንዱን ደካማ ሲደበድበው ያየው ልጄ አላስችል ብሎት "ሰወች ሆይ! ዑመር ብኑል ኸጧብ ደካማውን ሰውየ እንዲያግዘው ጥሩት!"እያለ ጩኸቱን አቀለጠው።ሰወች በህፃኑ ተደንቀው አተኩረው ተመለከቱት።እናቱ ሌላ ጉድ ሳይመጣብኝ ብላ የወጣችበትን ጉዳይ እንኳ ሳታሟላ ወደ ቤት ለመመለስ ተገደደች።እየተመለሱ ሳለ ሌላ ለማኝ አገኛቸው።አሁንም ለሱ ሳንቲም ሰጥታ አለፈች።ቤት ሲደርሱ የዘበኛው ሚስት ባሏ በጠና እንደታመመ የሚታከምበት ገንዘብ እንደሌለውና እርዳታ እንደሚያስፈልገው ስትነግራት ህፃኑ አስገራሚ ጥያቄ ጠየቃት።
–"ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ሞቷል???"
እናቱ ደንግጣ መልስ ሳትሰጠው ወደ ቤት ገባች።
ወደ ሳሎን ሲገቡ ቴሌቪዥኑ ተከፍቶ ነበር።ጋዜጠኛ አይሁዶች መስጅደል አቅሷን እንደተቆጣጠሩትና ሰጋጆችን ሲደበድቧቸውና ሲያንገላቷቸው እንደነበር እየዘገበ ነበር።የዚህን ጊዜ ልጄ "ዑመር ብኑል ኸጧብ ሙቷል ማለት ነው"አለና በጣም እየጮኸ ያለቅስ ጀመር።
ዑመር ብኑል ኸጧብ ሞተ
ዑመር ብኑል ኸጧብ ሞተ
ዑመር ብኑል ኸጧብ ሞተ"
ይህን እያወራን ሳለ ልጄ ከክፍሉ ወጣና ወደኔ እየተጠጋ "ዑመር ብኑል ኸጧብ ሞቷል አይደል?" አለኝ።እኔም "እናትህ
እርጉዝ ነች ከሁለት ወር በሁዋላ በአላህ ፈቃድ ዑመርን ትወልዳለች" አልኩት።"ዑመር ብኑል ኸጧብን?" አለኝ።"አወ ዑመርን "አልኩት።ፊቱ ጥርስ በጥርስ ሆነ።እየሳቀ መጣና ተጠመጠመብኝ።
"ዑመር ኢብኑል ኸጧብ
ዑመር ኢብኑል ኸጧብ "እያለ።
እኔም እንባየን እያበስኩ "ረዲየሏሁ ዐንከ ያ ዑመር!" አልኩኝ።
-አወ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ሞቷል–
እሱ የላቀበት ኢስላም ግን አልሞትም!!!
-ዑመር ሙቷል እሱ የሰራበት ቁርኣን ግን አልሞተም!!!
-ዑመር ሙቷል እሱን የወለደች ህዝብ ግን አልሞተችም!!!
-ዑመር ሙቷል በአላህ ፈቃድ ግን ሺህ ዑመር ይወለዳል!!!
ይህ ጥሪየ ነው፦ልጆቻችሁን በኢስላማዊ ተርቢያ አሳድጉዋቸው።ዑመር የሚወለደው ዑመር ከተወለደበት ህዝብ ነውና !!!
ሱብሀነሏህ
72 viewsGlamor, 20:15