Get Mystery Box with random crypto!

Bilal Media & Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication B
የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication
የሰርጥ አድራሻ: @linkbi7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-10-15 16:23:53
የዛሬ አዳዲስ እቃዎች ቶሎ ይፍጠኑ
አንድላይ ከነ original ከለራቸው
ይፍጠኑ ይደውሉልን
ጨርቁ ; ላይነን (ሲታጠብ የሚለቅ: እድፍ የማይዝ) እና normal ጨርቅ
አንገት ; ኦ እና ኮሌታ ያላቸው
ዋጋ;የ አንዱ ዋጋ950 ብር ብቻ
ያሉበት እናደርሳለን 三
ይደውሉልን 0968054849 ማሂ
0906264689 ሳላ
0979246250 አኑ
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ

ዉድ የ ሙሳላን ጀለቢያ ቤተሰቦች በዚህ ቻናል የተለያዩ የሚያማምሩ ጀለቢያዎች በማይታመን ዋጋ ያገኛሉ ይደውሉልን ያሉበት እናደርሳለን 三
ቻናላችንን ይቀላቀላሉ https://t.me/musalan
ይደውሉልን 0968054849 ማሂ
0906264689 ሳላ
0979246250 አኑ
93 viewsibnu rebah, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 19:11:06 "ከማይገቡኝ ነገሮች ውስጥ..."1(ጭቅጭቅ ከምለው)

የኔ አበባ...የኔ ጃስሚን...ፀዳልሽ የደመቀችዋ... ቢያዩሽ ቢያዩሽ የማትጠገቢዋ...የኔ ሴት!!
አንቺማ አሏህዋ በተወዳጁ ነቢይ አለይሂ ሰላቱ ወሰላም በመጨረሻ ንግግራቸው በኩል አደራ የተባለልሽ...!
በየሄድሽበት ጥበቃ ሊደረግልሽ የተገባ(ንፁህ መስታወት በንፁህ እጅም ቢነኩት ያድፋል ኮ)...ነሽም አይደል?

ከዛ አንቺዋ ደግሞ በጥበብ አብቢ ... ባለሽበት ዘርፍ ሁሉ ላቂ...ቤት ውስጥ የምትውይ ብትሆኚ ወጥ መስራቱን ማስተር አድርጊ...ልጅ እንክብካቤ ላይ ልምድ የሚጠይቁሽ ሁኚ... !
አቅምሽና ጊዜሽ በፈቀደው ልክ ተማሪ... የራበው ሰው ሲመገብ እንደሚስገበገበው-እውቀት ስታዪ፣ የሚነበብ፣ የማታውቂውና የሚጠየቅ ሲገኝ፣ ተስገብግበሽ ለማወቅ፣ ለመቆፈር ታትሪ!
ስለ መጨቆን፣ ስለ አንገት መድፋት ሰርክ ከሚለፈለፍበት ሜዳ ገለል ብለሽ...አንገትሽን ቀና ማድረጊያ እውቀት ቃርሚ...ጃስሚኔ ሞክረሽው ያቃተሽ አለ በአሏሁ እገዛ?
እምልልሻለሁ ምጥን ያህል ህመም የቻልሽ፣ በየወሩ የወርአበባ ህመም ሲንጥሽ ዋጥ የምታደርጊ አንቺ፡ሌላ ሌላው ኢምንት ነው ሚሆንልሽ...ብቻ ሞክሪው።

ከዛ ውጪ በየወቅቱ ሁለት ሶስት ስለሚያገቡት ስትነዛነዢ አትገኚ... መጀመሪያ ራስሽን ስለራስሽ አብቂ!
በየጊዜው ስለጭቆና አትደስኩሪ... ማማ ላይ መቆሚያን አስሺ!

እናም እህትሽ ነጃት ትወድሻለች።
:
29 viewsGlamor, 16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 21:16:17
በ ላኢላህ ኢለላህ መጨፈር
~
የተውሒድን ቃል (ላኢላህ ኢለላህ) ለጭፈራ ማዋል በጣም አስነዋሪ ተግባር ነው። ኢብኑል ጀውዚይ (597 ሂ.)፡-
የሱፍያ ክፍሎችን ተግባር አንስተው ሲያወግዙ እንዲህ ይላሉ:–
“በየምግቡ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ሲጠግቡ ጊዜ ይደንሳሉ፡፡ … ከመዐቶቻቸው ሁሉ የከፋው መዐት ግን ይህንን (ጭፈራ) መቃረቢያ (ዒባዳ) አድርገው መሞገታቸው ነው፡፡ ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው ከኢስላም እንደሚወጣ በርግጥም የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጥሯል፡፡” [ሶይዱል ኻጢር፡ 168]
በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ለመውሊድ የሚጨፍሩ ሱፊዮች ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
27 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 21:53:58
"ጤነኞች አይደሉም" የምንለው በምክንያት ነው!
~
ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ “እኛ ዘንድ ሱፊያ የሚባሉ ሰዎች አሉ፡፡ በብዛት ይበሉና ከዚያ ያንጎራጉራሉ፡፡ ከዚያም ተነስተው ይጨፍራሉ” ተብለው ቢጠየቁ:–

“ህፃናት ናቸው?” አሉ።
“አይደሉም” አሏቸው፡፡
“እብዶች ናቸው?” ብለው ጠየቁ።
“አይደሉም፣ ሸይኾች ናቸው” አሏቸው፡፡
ኢማሙ ማሊክ:– "እኔ ከኢስላም ሰዎች ይህን የሚሰራ አንድም አልሰማሁም” አሉ።
[ተርቲቡል መዳሪክ: 2/53]

አልዒዝ ኢብኑ ዐብዲሰላም ረሒመሁላህ፡-

“ጭፈራ ቢድዐ ነው፡፡ #አእምሮው_ጎደሎ_የሆነ እንጂ አይፈፅመውም” ብለዋል።
[ፈታዋ አልዒዝ ኢብኒ ዐብዲሰላም፡ 318-319]

ከስር የምትመለከቱት ሱፍዮች የሚጨፍሩበትን ድቤ የተሸከመ አሳዛኝ ፍጡር ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
53 viewsGlamor, 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 12:11:06
ትብብር

የዚህ admission card ባለቤት ካርዱን ባስ ውስጥ ወድቆ ስለተገኝ በዚ ስልክ ደውላ ማግኝት ስለምትችል 0910222366 ማስታወቂያውን ያያቹ ደግሞ ልጅቷ ጋር እንዲደርስ ሼር በማረግ ተባበሩ

[ልጅቷ ያለID ስለማያስፈትኗት እባካችሁ ቶሎ ቶሎ ሼር እናርግላት]

ኢትዮጵያዊነት መልካምነት

"SHARE". @ETHIO_ARSENAL
63 viewsGlamor, 09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 23:53:51 "እኛ ሃገር ሳይሆን ልቦችን ልንከፍት ነው የመጣነው" ይህ የሙሐመድ አል ፋቲህ ንግግር ነው

"የነብያችን የትንቢት ቃል በሙራድ ቤት ተወለደ" ወንድ ልጅ የተወለደላቸው ሡልጣን ሙራድ ደስታቸውን የገለፁበት ቃል ነበር። ቀናት ቀናትን ወልደው አመታት ነጎዱ። ልጅም ዲነል ኢስላምን በጥልቅ ያውቅ ዘንድ በበርካታ ዑለማዎች ትምህርት ይሰጠው ጀመር። እናቱ ዘወትር ማለዳ እጁን ይዛ የቆስጠንጢኒያን አጥሮች እያሳየችው "ልጄ ሆይ! ያ የቆስጠንጢኒያ አጥር ነው ድል አድርገህ በመክፈት የነቢዩን ትንቢት የምታረጋግጠውም አንተ ነህ" እያለች ግብና ዓላማውን እንዳይዘነጋ አድርጋ ኮትኩታ አሳደገችው። የሴቶች ማህፀን የሙሐመድ አል ፋቲህ አይነትን ጀግናን ትናፍቃለች በተርቢያ ኮትኩታ በአላማ አንፃ የምታሳድግን እናት አለም ተርባለች!
ቆስጠንጢኒያ በጠንካራ ግንቦች የታጠረች የሮሞች መናገሻ ከተማ ናት። በየግንቦቹ መካከል ታላላቅ ሰው ሰራሽ ሀይቆች ይፈሷታል። የባህር በሮቿ በትላልቅ ፀረ መርከብ ጦሯ የታጠሩ በመሆናቸው ለወራሪዎች ፍፁም አይመችም። በእያንዳንዱ ግንብ ላይም በሺዎች የሚቆጠሩ የሮም ጦረኞች ሁሌም በተጠንቀቅ እንደቆሙ ነው።
እስልምና ወደ አውሮፖ እስዳይስፋፋ ዋናው ፈተና የሆነችውም እሷው ናት። ለዚህም ነው የኮንስታንቲኖፖል በድል መከፈት እስልምናን ወደ አውሮፓ ለማስፋፋት ወሳኝ ምዕራፍ የሆነው።
ከ22 በላይ የሙስሊም መሪዎች ይህቺን ከተማ ለመክፈት ከበባ ቢያደርጉም አንዳቸውም ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል። ከታላቁ ሰሐባ አቡ አዩበል አንሷሪ እስከ ነጎድጓዳማው መብረቅ ባየዚድ ከሱልጣን ሙሐመድ አልብ አርሰላን እስከ ሱልጣን መሊክሻህ ከኡመያድ ኺላፋ እስከ አባሲያ ኺላፋ ሁሉም የሙስሊም መንግስታቶች የአለማችን መገናኛ የሆነችውን ኮንስታንትኖፕልን ለመክፈት ከተማዋንም ከበዋል። በመስጂድ ሚናራዎች ተውባ አዛን ከየጨቅጣጫው የሚሰማባት ከተማ ለማድረግ ለአመታት ለፍተዋል ግና ሳይሳካላቸው በአጥሯ ስር ወድቀው ይህችን ዓለም ተሰናበቱ።
"ቆስጠንጢያን ትከፍታላችሁ - ምን ያምር አሚር ነው አሚሯ፣ ምን ያምር ጦር ነው ያም ጦሯ” በማለት ነብያችን የተናገሩትን ትንቢት ሊፈፅም የዓለም ከተሞች ሁሉ ቁንጮ የሮማን ኢምፓየር ዋና ከተማ፣ የሁለት አህጉሮች እና የአራት ባህሮች ማሳለጫ የአሁኗ ኢስታንቡልን ለመክፈት አይበገሬው ጀግና፣ እጅግ ሚስጥረኛው የጦር ስልት አዋቂ የሙጃሒዶች መሪ ከዕድሜው የማይጠበቀውን ሊሰራ የነብዩን ትንቢት ሊፈፅም በ19 ዓመቱ የአባቱን ዙፋን ተረከበ። ወታደሮቹን አደራጅቶ በ 19 አመቱ ቆስጠንጢኒያን ድል አድርጎ ከፈተ።
ከድሉ በኋላ ሱልጣን ሙሐመድ አል ፋትህ የዑስማንያ ስርወ መንግስት መናገሻ ከተማ አደረጋት። ስሟንም "ኢስላም ቡል" ብሎ ሰየማት "የኢስላም በር" እንደማለት ነው።
የምዕራቡ አውሮፓ ክርስቲያኖች በሙስሊሞች ድል በጣሙኑ ተገርመዋል፣ ተደናግጠዋልም አዝነዋል። ከኢስላም ቡል አንድ ሐይል ተነስቶ እንደሚያጠፋቸው በደራሲዎቻቸው፣ በጋዜጠኞቻቸውና በመንግስቶቻቸው እየተለፈፈ የክፋት ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨቱን ተያያዙት።
የአውሮፓ መሪዎችም ብዙ ሰዓታት የወሰዱ ስብሰባዎችና ምክክሮችን በተለያዩ ቀንና ቦታ ከማድረግ ወደ ኋላ ብለው አያውቁም። በመካከላቸው ያሉትን ችግሮች ትተው ሙስሊሞች ላይ በጋራ እንዲዘምቱ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ግፊቶች ተበራከቱባቸው። ፓፓ ኒኮላ አምስት በቆስጣንጢኒያ መውደቅ ከፍተኛ ፀፀትና ንዴት ተሰምቷቸዋል።

የአውሮፓ የታሪክ ፀሐፊዎች "የመሀከለኛው ዘመን ታሪክ መጨረሻና አዲሱ ታሪክ መጀመሪያ" ብለው ይጠሩታል።

ፅሑፎቼን አንብቦ ለሌሎች ወንድምና እህቶች ሼር በሚያደርግ ሰው ላይ ሁሉ የአላህ እዝነት ይስፈን
17 viewsGlamor, 20:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 15:31:40
መውሊድ ይቻላል ለሚልህ ይህንን አቅርብለት


ጥያቄ አንድ
መውሊድ ማክበር አላህን መታዘዝ ነው ወይስ አላህን ማመፅ በለው?

①) መውሊድ አላህን ማመፅ ነው ካለ አላህን ለማመፅ መውሊድ ማክበር አይቻልም በማለት ፋይሉ መዝጋት ይቻላል። ነገር ግን በፍፁም ይህንን አይሉም።

②) አላህን መታዘዝ ነው ካለ (የሚሉትም ይህ ነው) ወደ ሁለተኛው ጥያቄ ትሸጋገራለህ

ጥያቄ ሁለት
ይህንን አላህ መታዘዝ ነው ኢባዳ ነው የምትለው መውሊድ የአላህ መልእክተኛ ያውቁት ነበር ወይስ አያውቁትም ዘንግተውታል በለው።

①) መልእክተኛው አያውቁትም ዘንግተውታል ካለ ይህ ግልፅ የሆነ ኩፍር ነው። ነገር ግን ይህንን በፍፁም አይሉም።

②) የአላህ መልእክተኛ አውቀውታል ካለ (የሚሉትም ይህ ነው) ወደ ቀጣዩ ጥያቄ ትሻገራለህ።

ጥያቄ ሶስት
መውሊድ የአላህ መልእክተኛ አውቀውት ከሆነ ለህዝባቸው አድርሰውታል ወይስ አላደረሱትም በለው።


①) ለህዝባቸው አላደረሱትም ካለ አላህ ታማኝነታቸውን የገለፀውን ነብይ በመጥፎ መጠርጠር ስለሆነ ግልፅ የሆነ ኩፍር ነው። ነገር ግን ይህንን አይሉም።

②) ለህባቸው አድርሰውታል ካለ፦ በሙግትህ ላይ እውነተኛ ከሆንክ መረጃ አምጣ በለው? ነገሩ እዚህ ላይ ያበቃል። መረጃ ደሞ ከየትም ሊያመጣ አይችልም።

ምክንያቱም መውሊድን በተመለከተ አንድም የቁርአን ወይም የሀዲስ መረጃ የለምና። ይህም ማረጋገጫው እነሱ ራሳቸው መውሊድ ቢድአ ሀሰና ነው ማለታቸው ነው። መረጃ ያለው ነገር ደሞ ቢድአ ሀሰና ሊሆን አይችልምና።

ነገር ግን አላዋቂዎችን ለማታለል ከቁርአን ከሀዲስ መረጃ አለ ብለው ሊያጣቅሱ ይችላሉ። እውነታው ግን ለመውሊድ ብለው የሚያመጧቸው የቁርአንና የሀዲስ መረጃዎች በነሱ ላይ መረጃ የሚሆኑ እንጂ ለነሱ መረጃ የሚሆኑ አይደሉም።

http://t.me/ALHidayatv
46 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 22:35:53 ቅኔው ከገባህ የሚከተለውን ንግግር መቼም አትረሳውም...

<<የኛ ችግር.... በነብዩ {ሰ.ዐ.ወ} ጊዜ የነበሩ ሰዎች "ጀነትን ይፈልጉ" ነበር!... አሁን ላይ ያሉ ሙስሊሞች ግን "ጀነትንም ጭምር ይፈልጋሉ"... ልዩነቱን ልብ በል>>

-ሙሀመድ ሆብሎስ
49 viewsGlamor, 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 21:18:38
ሸይኽ ሰዒድ አሕመድ ሙስጦፋ
58 viewsGlamor, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 12:22:42 ሴት ወንዱን በየሰርግ ቤቱ እየቀላቀለ ሚያስጨፍር ማዲህ ሲባል
ሙስሊም በየግሩፑ ተቧድኖ በሰው አፈጣጠር ሳይቀር ሲቀልድ
ሴት ልጅ ሀያዕ ጠፍቷት በየ ቲክቶኩ መጨፈርዋ ሳያንስ ወላጅ እናቷን ለገንዘብ ብላ ገላልጣ ይዛ ስትወጣ
በአጠቃላይ ስነ ምግባር በዚህ ልክ ከሙስሊሙ ላይ ሲወገድ

ያ ጀግናው ዑመር አል ፋሩቅ ከነ አለንጋው ይበልጥ ይናፍቃል
64 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ