2022-09-13 13:26:09
የኢኽዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት
(ተከታታይ፣ ክፍል-3)
ሰይድ ቁጥብን ለማያውቀው
~
1. ሰይድ ቁጥብ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን አይቀበልም። ኢስቲዋእን ልክ አሕባሾች እንደሚያደርጉት በጀህ^ሚያ፣ በሙዕ^ተዚላና በአሻ^ዒራ ተፍሲር ነው የፈሰረው። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 4/2328፣ 5/2807፣ 6/3480] በዚህ ጉዳይ የአሕ^ባሽን ጥመቶች ለማጋለጥ የምትታትሩ ወንድሞችና እህቶች ሆይ! የጥመት ቡላና ዳለቻ የለውም! የሰይድ ቁጥብን ጥመትም እንዲሁ አትርሱ።
2. ሰይድ ቁጥብ አደገኛውን የ“ወሕደተል ውጁድ” በተጨማሪም የጀህ^ሚያዎችን፣ የቀደ^ሪያዎችንና የጀብ^ሪያዎችን ዐቂዳ አስፍሯል። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 4/2249፣ 5/2719፣ 6/4002]
3. ሰይድ ቁጥብ {የኡሉሂያ ጉዳይ የውዝግብ አጀንዳ አልነበረም። ይልቁንም የሩቡቢያ ጉዳይ ነው የውዝግብ አጀንዳ የነበረው። መለኮታዊ ተልእኮዎች (ሪሳላዎች) ሲጋፈጡት የነበረውም ይህን ነው። የመጨረሻው ተልእኮም (ሪሳላም) ይጋፈጠው የነበረው ይህ ነው} ይላል። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 4/1846]
እውነታው ግን በነቢያትና በህዝቦቻቸው መካከል የነበረው ፍጭት ዋና መንስኤው ተውሒደል ኡሉሂያን አለመቀበላቸው ነበር። እንጂ ተውሒደ ሩቡቢያህ አልነበረም። ለምሳሌ የመካ ሙሽሪኮች የአላህን ፈጣሪነትና ጌትነት ያውቁ ነበር። ችግራቸው እሱን በብቸኝነት ለማምለክ ፈቃደኞች አለመሆናቸው ነው።
4. ሰይድ ቁጥብ ላኢላሀኢለላህ ማለት “በመፍጠርና በመምረጥ ተጋሪ የለውም ማለት ነው” ይላል። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 5/2707] ይሄም ግልፅ ስህተት ነው። ላኢላሀኢለላህ ማለት ከአላህ በስተቀር በሐቅ አምልኮት የሚገባው የለም ማለት ነው። የአላህን ፈጣሪነትማ ብዙሀኑ የመካ አጋሪዎችስ መቼ ካዱ? ይሄውና የቁርኣን ዘላለማዊ ምስክርነት:-
{ قُلۡ مَن یَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَاۤءِ وَٱلۡأَرۡضِ أَمَّن یَمۡلِكُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَـٰرَ وَمَن یُخۡرِجُ ٱلۡحَیَّ مِنَ ٱلۡمَیِّتِ وَیُخۡرِجُ ٱلۡمَیِّتَ مِنَ ٱلۡحَیِّ وَمَن یُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۚ فَسَیَقُولُونَ ٱللَّهُۚ فَقُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ}
{“ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረስ ማን ነው? ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከህያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?” በላቸው። በእርግጥም “አላህ ነው” ይሉሃል። እናም “ታዲያ (እንደሚገባው) አትፈሩትም?” በላቸው።} [ዩኑስ፡ 31]
5. ሰይድ ቁጥብ ኢማንን ወጥና የማይከፋፈል ነው ይላል። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 2/798] ይሄ አደገኛ አንድምታ ያለው የሙር^ጂአ እና የኸ^ዋሪጅ አቋም ነው።
6. ሰይድ ቁጥብ እንደ ራፊ^ዷ/ ሺ^0 የነብዩን ﷺ ሶሐቦች ያንቋሽሻል።
[ሀ]:- አቡ ሱፊያንን ረዲየላሁ ዐንሁ "የአቡ ሱፊያንን እስልምና የከንፈርና የምላስ እስልምና እንጂ የልብ ኢማንና እውነቱን የማግኘት አይደለም። ኢስላም ወደዚህ ሰውየ ልብ አልሰረፀም፣ ከሰለመ በኋላም የሙስሊሞችን ሽንፈት ሲመኝ የነበረ ነው!!” በማለት በኒፋ^ቅ ይወነጅላል። ይስተዋል! ነብዩ ﷺ ግን የአቡ ሱፊያንን እስልምና ተቀብለዋል። አቡ ሱፊያን ሙስሊም ሆነው ጂሃድ ሲዋጉ አንድ አይናቸውን እንዳጡ እና ነብዩም ﷺ “ከፈለግክ ዱዐ ላድርግልህና አይን ይመለስልሃል። ከፈለግክ ደግሞ (ታገስና) ጀነት አለህ” ሲሏቸው “ጀነት ይሻለኛል” እንዳሉ ኢብኑ ሐጀር ጠቅሰዋል። [አልኢሷባህ፡ 4066]
[ለ]:- ሰይድ ቁጥብ ሙዓዊያንና ዐምር ብኑል ዓስን በውሸት፣ በማጭበርበር፣ በማታለል፣ በንፍ^ቅና፣ በሙሰኝነት … ይወነጅላቸዋል። [ኩቱቡን ወሸኽሲያት፡ 242] ሙዓዊያን ረዲየላሁ ዐንሁ ደግሞ ደጋግሞ በሚያስቀይሙ ቃላት ወርፏቸዋል። አሁን በነዚህ አስቀያሚ ቃላት የተወነጀለው ሰይድ ቁጥብ ቢሆን ኖሮ ኢኽዋኖች ምን ይሉ ነበር? ለመሆኑ ከሶሐቦቹና ከሰይድ ቁጥብ ማነው የሚበልጠው? ዛሬም ተከታዮቹ ሰይድ ቁጥብ ተሳስቷል ከማለት ይልቅ ሶሐቦችን መወንጀል ነው የሚቀናቸው። ለሶሐቦች የማይሰጡትን ምክንያትም ለሰይድ ቁጥብ ይደረድራሉ።
ኢብኑ ሙባረክ፡ ከሙዓዊያና ከዑመር ብኑ ዐብዲልዐዚዝ የትኛው እንደሚበልጥ ሲጠየቁ “ወላሂ ሙዓዊያ ከነብዩ ጋር ሆኖ ባፍንጫው የገባው አቧራ ከዑመር ሺህ ጊዜ ይበልጣል” ብለው ነው የመለሱት። ልብ በል! ከሙዓዊያና ከሰይድ ቁጥብ ማን ይበልጣል አይደለም የተጠየቁት። ሌላም ጊዜ “ሙዓዊያ እኛ ዘንድ ፈተና ነው። እሱን በመጥፎ ሲመለከት ያየነውን በሶሐቦች ጉዳይ አናምነውም” ብለዋል። ኢማሙ አሕመድ “ከሙዓዊያና ከዑመር ብኑ ዐብዲልዐዚዝ ማን ይበልጣል?” ተብለው ሲጠየቁ፣ “ሙዓዊያ ነው የሚበልጠው። የነብዩን ሶሐቦች ከማንም ጋር አናወዳድርም” ብለዋል። አንድ ሰው ኢማሙ አሕመድን “አንድ ሙዓውያን የሚያንቋሽሽ አጎት አለኝ” ቢላቸው “ከሱ ጋር አብረህ እንዳትበላ!” ብለውታል። ብዙ ኢኽዋኖች ግን ብዙ ፀያፍ ጥፋቶች ያሉበትን ሰይድ ቁጥብን ሸሂድ እያሉ እያወደሱ እነ ሙዓዊያን ለማብጠልጠል ግን ሁለት ጊዜ እንኳን ማሰብ አይፈልጉም።
[ሐ]:- ሰይድ ቁጥብ ከዚህም ተሻግሮ በኑ ኡመያን በጅምላ በኒፋ^ቅ ይወነጅላል፡፡ “በኑ ኡመያ በጥቅሉ ኢማን ከልባቸው አልሰረፀም፡፡ ኢስላም ለነሱ እንደ ጥቅማቸው ሲያሻቸው የሚለብሱት ሲፈልጉ የሚያወልቁት ካፖርት ማለት ነው። ስነ ምግባር፣ ዲን፣ ልቦና የማይገታቸው ሰዎች ናቸው…” ይላል። [አልዐዳላህ ፡172]
ከግለሰብ ክብር በላይ ለእውነት የምትወግኑ ሁሉ ቆም ብላችሁ አስተውሉ! ሰይድ ቁጥብ በዚህ መልኩ የሚገልፀው እናንተን ቢሆን ምን ትሉ ነበር? በነዚህ አስቀያሚ ቃላት የሚገልፀው የነብዩን ﷺ ሶሐቦች ሲሆንስ? የነብዩን ሶሐቦች በማብጠልጠል የተለከፈው ሰይድ ቁጥብ የተከተለው የራፊ^ዷዎች/የሺ^0ዎች መንገድ ነው። ሶሐባ የሚሳደብን ሰው በተመለከተ ነብዩ ﷺ “የአላህ፣ የመላእክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በሱ ላይ ይሁን” ብለዋል። ኢማሙ ማሊክ፡- “የአላህ መልእክተኛን ﷺ ሶሐቦች የሚሳደብ ሰው በኢስላም ውስጥ ምንም ድርሻ የለውም” ብለዋል። ኢማሙ አሕመድ፡ “አንድ ሰው የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶሐቦችን በክፉ ሲያነሳ ካየህ ሙስሊምነቱን ተጠራጠረው” ብለዋል። አቡ ዙርዐህ፡- “አንድ ሰው ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶሐቦች የየትኛውንም ክብር ሲያጎድፍ ካየኸው እወቅ እሱ አፈንጋጭ ነው” ብለዋል።
[መ]:- ሰይድ ቁጥብ ከዚህም አልፎ በጀነት የተመሰከረላቸውን፣ ነብዩ ﷺ ሁለት ሴቶች ልጆቻቸውን የዳሩላቸውን፣ “ሶስተኛ ቢኖረኝ እድረው ነበር” ያሏቸውን፣ ሶስተኛውን ፍትሃዊ ኸሊፋ ዐሥማን ብኑ ዐፋንንም እንዲህ ሲል ይወነጅላል:-
* የኡሥማን ረዲየላሁ ዐንሁ የኺላፋ ዘመን በሶስቱ ኸሊፋዎች ዘመን ውስጥ የገባ ክፍተት እንጂ የእውነት የነገሰው እሱ ሳይሆን መርዋን ነው።
* ዑሥማን በስልጣኑ ተከልሎ የሙስሊሙን ገንዘብ ያላግባብ የተጠቀመ፣
* ለዘመዶቹ እያዳላ የነብዩን ወዳጆች ያራቀ፣
74 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 10:26