2022-08-19 21:54:07
ሸይጧን በነብዩ ሠለልላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደማይመሠል እና መመሠልም እንደማይችል የታወቀ ጉዳይ ነው።በዚህም ላይ ቡኻሪ እና ሙስሊም የዘገቧቸው ሀዲሶች ጠንካራ ሀዲሶች አሉ።
ታዲያ ምንድነው ጥፋቱ?????????
ቀደምቶች አንድ ሠው መጥቶ ሀቢብን ሠለልላሁ ዐለይሂ ወሰለም በህልሜ አይቻለው ቢለን እስኪ ያየከውን ሰው መልክ ቁመናና ዝርዝር ነገሮችን ግለፅልን እንለዋለን ይሉ እንደነበር ሸይኽ ዐብዱርረዛቅ ያወሣሉ።ነብዩ ሰለልላሁ ዐለይሂ ወዐላ አሊሂ ወሰለም እኔ ሙሀመድ ነኝ እስካላሉት ወይም እሣቸው ለመሆናቸው እውቅና ካልሠጡት ጉዳዩን በደንብ ማጤን ያስፈልጋል ሸይጧን እሣቸውን መመሠል ስለማይችል አንድ ሠው ሌላን ግለሠብ ሲመለከት ይህ ሠው ሙሀመድ ነው ይለዋል። ያ ሠው ደሞ በዚህ ባየው ህልምና ልቡ ላይ በተመሣሠለበት ነገር ፍርድ ይሠጥና አይቻለው ከማለት አልፎ ባጢል እየሰራ ሀቅ ላይ ባልሆን ኖሮ እንዴት እሳቸውን አያለው??? ብሎ እንዲያስብና ከመረጃ ይልቅ ህልሙን እንዲከተል ሸይጧን ይወሰውሰዋል በዚህም ብዙዎች ተሸውደዋል እየተሸወዱም ይገኛሉ።አንደኛው ሰው እንደዚሁ እሣቸውን አይቻለው ብሎ ደስ ብሎት እስኪ ያየከው ሰውዬ ምን አይነት ነበር ሲባል እንዲህ ብሎ መለሠ
ፂሙን የተላጨ
ጥቁር ግን በጣም ያልሆነ ብሎ መለሠ
ልብ በሉ በምንም ታአምር ሰይጣን እሣቸውን ሊመሠል አይችልምና የሚያዩት ነገር ሁሉ ተቃራኒ የሆነ ነገር ነው።
ዋናውና ትልቁ ነገር ስራ ነው ስራችን ላይ ማተኮር እንጂ በተራ ማስመሰያ ግራ ልንጋባ አይገባም።ስራው ወደኋላ ያዘገየው ሰው ዘሩ አያስቀድመውም ብለው የለ ሀቢቡና???
አቡ ለሀብ ምን ጠቀመው ዝምድናው?
አቡ ጧሊብ አጎትነቱ ከቅጣት አላስጣለው?
አልላህ ፊት የምንተሣሠበው በስራ እንጂ በሌላ ነገር አይደለምና ስራችን ላይ እናተኩር። አንዳንድ ግዜ አየን የሚሉት ሰዎች ለአካሔዳቸው ከቁርዐንና ሀዲስ ይልቅ እንደዚህ አይነት ክስተቶችን እንደመረጃ ያዘወትራሉ። እኛ ሀቅ ላይ ባንሆን ኖሮ....... እያሉም ይያገራሉ ወይም መልእክትን ያስተላልፋሉ። አንዳንዶች ደሞ አሉ ይሄን ሠጡኝ፤ከሣቸው የተቀበልኩት ጠሪቃ ነው ምናምን የሚሉ ቆይ ግን ዲን ሙሉ አይደለም ነው ሀሣባቸው ወይስ ምንድነው እሺ እንደው ሁሉም ይቅርና ይሄ ነገሩኝ የተባለው መልክት ከመምጣቱ በፊት የነበሩ ሰዎች እነ አቡበከር ዑመር ኡስማን ዐሊይ እንዴት ሊሆኑ ነው???
ሸሪዐን ለመተግበርም ሆነ ለፍቅር እነሡ አይቀድሙም? አሁን ካሉትስ ቢሆን ለመደንገግ እነሡ የተሻሉ አልነበሩም???
አልላህ ከመልእክተኛችን ሠለልላሁ ዐለይሂ ወዐላ አሊሂ ወሰለም ጋር በጀነት ይሰብስበን አሚሚሚሚሚሚሚን
29 viewsGlamor, 18:54