2022-07-22 20:08:51
"የተዘጉ በሮች እና ያሳወሩን ብዥታዎች ትናንትና ነበር ።የ22 ወር ልጄ የራሱን ነፃነት ለማወጅ ሲንቀሳቀስ በአይኔ አየሁት ። ከመኪና ወንበሩ መቀመጫ መሀል ከወጣ ቡሀላ እንደ ትልቅ ልጅ በሩን ለመዝጋት ሞከረ ። እኔ የሚሰራውን ሁሉ በቅርበት እከታተለው ነበር ።እኔ በሩን እንዲዘጋ ብተወው ኖሮ ትንሹ ጭንቅላቱ በግጭት አይተርፍም ነበር ። አነሳሁትና በሩን ራሴ ዘጋሁት ።ድርጊቴ አናደደውና አለቀሰ ።እሱ ማድረግ የፈለገውን ነገር ስለከለከልኩት ነበር የተበሳጨው ።
ክስተቱን እያየሁኝ የሆነ ሀሳብ ጭንቅላቴ ውስጥ መጣ ። በተለይ ከአላህ አንፃር የዚህ አይነቱ ነገር በህይወታችን ውስጥ ሁሌም ያጋጥማል ። እኛ አንድን ነገር ስንፈልግ አላህ ግን ሳይፈልግ ሲቀር እንዴት እንደሚከለክለን አስተዋልኩበት ። በተለይ ወጣት ሆነን ሳለ የዚህ አይነቱ ነገር በተደጋጋሚ ያጋጥመናል ። አንዱን ነገር በእጅጉ ፈልገን እኛ በፈለግነው መልኩ ካልተሳካልን ተስፋ እንቆርጣለን ፣እንናደዳለን ፣ክፉኛእንበሳጫለን ። ግና ኃላ ላይ ቆይቶም ቢሆን አለመሳካቱ ለበጎ እንደሆነ ይገለጥልናል ። እኔ ልጄ እንዳይጎዳ ያደረኩት ነገር ቢኖር በሩን እንዳይታገለው እሱን መውሰድ ብቻ ነበር ። እሱ ግን ለእሱ ጥቅም እንደሆነ አልገባውም ። በመነጫነጩ መሐል ሆኖ ከትልቅ አደጋ እንዳዳንኩት አያውቅም ነበር ። ልጄ ምንም ሳያቅ በየዋህነቱ እንዳለቀሰው ሁሉ እኛም እንዲሁ ካለቀስንላቸው ነገሮች አላህ እኛን ያዳነበት ሁኔታ ብዙ ነው ።
የአውሮፕላን የበረራ ሰዓት ሲያመልጠን፣ስራ ስናጣ ፣ካሰብነው ሰው ጋር በትዳር የመጣመር ጉጉታችን ሲከሽፍ ...ሌላም ሌላም ገጠመኝ ሲገጥመን "ይሁን ለበጎ ነው "ብለን ያሰብንበትና ያሳለፍንበት አጋጣሚ ይኖር ይሆን!
አላህ በቁርአኑ እንዲህ ይለናል ፦
كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلْقِتَالُ وَهُوَ كُرْهٌۭ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰٓ أَن تَكْرَهُوا۟ شَيْـًۭٔا وَهُوَ خَيْرٌۭ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰٓ أَن تُحِبُّوا۟ شَيْـًۭٔا وَهُوَ شَرٌّۭ لَّكُمْ ۗ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
መጋደል እርሱ ለእናንተ የተጠላ ሲሆን በእናንተ ላይ ተጻፈ፡፡ አንዳች ነገርን እርሱ ለናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም ነገር እርሱ ለናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም (የሚሻላችሁን) ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም፡፡"
ምንጭ
(ልብህን አስመልስ በYasmin Mujahid )
82 viewsGlamor, edited 17:08