2022-07-31 16:55:11
የሴት ልጅ ክብር ሴትን ልጅ ማብቃት
[ክፍል አንድ]
የአላህ መልክተኛ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)
ባልደረቦች የእስልምናን መልዕክት ለማድረስ ብለው ወደ አንድ ከተማ ሲገቡ ከመልክተኛው የተቀበሉትን መልዕክት ውብ በሆነ መልኩ ነው ሚያስተላልፉት ።እንዲህ ይላል የእርሳቸው መልዕክት ፦"
እኔ የመጣሁት ከባሮች ባርነት የባሮች ጌታ ወደ ሆነው ባርነት ነፃ ላወጣችሁ ነው "።
------------------------------------------------
በዚህ አረፍተነገር ውስጥ አንድ የሆነ ምርጥ መልዕክት አለ። በቃላቱ ውስጥ የተደበቀ ሲሆን ሁሉንም በተለይ ተጎጂ የሆነውን የማህበረሰብ ክፍል ለማብቃት እንዲሁም ወደ ነፃነት ለመድረስ ትክክለኛው ቁልፍ ነው።
ምን መሰለህ ...አንተ ወይም እኔ ከፈጣሪያችን ውጪ አንድ ነገር እንዲገዛን ከፈቀድን ፤ ስኬታችንን ደስታችንን ጥቅማችንን ከዚያ ነገር አያይዘን በዝምታ ነገሮችን የምንቀበል ከሆነ ያጎጂ የሆነ ባርነት ነው። ያ ራሴን የስኬቴ እና የውድቀቴ ሁሉ ፈላጭ ቆራጭ ወሳኝ አድርጎ የሚያቀርበው ነገር እኔን የሚቆጣጠር አለቃዬ ነው የሚሆነው ማለት ነው ።
ሴትን ልጅ ሊገዛ የሚችልና አለቃዋ የሆነ ነገር በየጊዜው የተለያየ መልክ ይዞ ዘመናትን ተሻግሮ ዛሬ እዚህ ላይ ደርሷል። ለረጅም ዘመን ለሴት ልጅ መለኪያ ተደርጎ በስፋት የሚታወቀው ወንድ ነው። ግና ብዙን ጊዜ እኛ የምንረሳው ነገር ቢኖር አላህ ለሴት ልጅ ክብር የሰጠው ከእሱ(ሱብሀነሁ ወተዐላ) አንፃር ባላት ግንኙነት እንጂ ከወንድ ልጅ ጋር ባላት አቀራረብ አይደለም ። ግና ምእራባውያን የሴትነትን ነፃነት አቀንቃኞች አምላክን ከስፍራው በማንሳታቸው እንደ መለኪያ የቀረው ወንድ ልጅ ብቻ ነው ። ስለሆነም ምዕራባውያን የሴትነት ነፃነት አቀንቃኞች ወንድ ልጅን መለኪያቸው ለማድረግ ተገደዱ።ይህን በማድረጋቸውም ምክንያት ለሴት ልጅ የተሳሳተ መለኪያ ለመቀበል ቻሉ። ሴት ልጅ "ሙሉ ሰው " የምትሆነው እንደመለኪያዋ እንደ ወንድ ልጅ ስትሆን ብቻ ነው አሉ።
-----------------------------------------------
ወንድ ልጅ ፀጉሩን አጭር አድርጎ ሲቆረጥ ሴቷም ካልተቆረጥኩ አለች።እነኚህን ነገሮች ያሰበችው ወዳና ከመጀመሪያው አስባበት ሳይሆን "መለኪያ /ውሀ ልክ" ነው ተብሎ የታሰበው ወንድ ልጅ ስለተሳተፈበት ብቻ ነው።
.....
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
° በዳሩል አርቀም °
° የተዘጋጀ °
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ምንጭ(ልብህን አስመልስ ከሚለው መፅሀፍ)
ይ
ቀ
ጥ
ላ
ል
82 viewsGlamor, 13:55