Get Mystery Box with random crypto!

Bilal Media & Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication B
የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication
የሰርጥ አድራሻ: @linkbi7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-10-04 16:20:15 Channel photo updated
13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 19:52:47 #poem_358

(ነሱሀ አወል)

ኢላሂ....!
ሰውማ ታውቃለህ...!
በነፈሰበት ነው
እግሩን ሚያዋድደው፣
በዘነበበት ነው
ሳይጠይቅ ሚነጉደው።

አንተ ግን ጌታየ...!
ነፈሰ
ዘነበ፣
ከሰመም
አበበ፣
ከጎኔ አትርቅም
ከጎኔ አትሸሽም፣
እንዴት? ግን ወደድከኝ
እኔን ያህል ቀሽም።

አቤት እዝነት!

http://t.me/Nesuhaawel_poem
41 viewsGlamor, 16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 21:34:22 ራስህን ስታጣ በሌሎች ትሳባለህ!ራስህን ስትሆን ሰዎችን ትስባለህ! ያኔ ግን ራሳቸውን እንዳያጡ ስበቱ በልኩ እንዲሆን አድርግ!!!
24 viewsGlamor, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 18:02:33 ማን ነው የከፋው?
አንዳንድ ሰዎች መውሊድ በኢስላም የሌለ የፈጠራ መንገድ ነው፡፡ መውሊድ ሸር ነው፡፡ ኸይር ቢሆን ኖሮ አላህ እና መልክተኛው ይደነግጉልን ነበር፡፡ ሰሃባዎች፣ ታቢእዬች፣ አትባኡ ታቢኢን፣ አራቱ አኢማዎች ፉቀሃዎች (አቡ ሀኒፋ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማሙ ሻፊኢይ፣ ኢማሙ አሕመድ)፣ ሙሐዲሶች (ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ነሳኢ፣ አቡ ዳውድ ኢብን ማጃእ…..) ያውቁት ነበር፡፡ እነዚህ ሁሉ ምርጦች አያውቁትም ሲባሉ እሺ አናከብርም ፈጠራ ስለሆነ ከማለት ፋንታ “በሳቸው መወለድ ሰይጣን እና ወሃቢ ብቻ ነው ያለቀሱት” ሲሉ እየተደመጡ፣ ሲፅፉም እየታዩ ነው፡፡
እውነታው በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መወለድ የመካ ሙሽሪኮች አልተቆጡም ነበር፡፡ የመካ አጋሪያን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ከነብይነት በፊት “ሙሐመዱል አሚን (ታማኙ ሙሐመድ)” እያሉ ነበር የሚጠሯቸው፡፡ ነብይ ሆነው “ህዝቦቼ ሆይ! ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ የለም በሉ ትድናላችሁ” ሲሉ የመጀመሪያው ጠላታቸው በሳቸው መወለድ አይደለም ሊቆጣ ተደስቶ የነበረው አቡ ለሃብ “እልም ያድርግህ ለዚህ ነው ወይ የሰበሰብከን” ሲል ግልፅ ጥላቻውን ይፋ አደረገ፡፡ ከዛም አጋሪያን ታማኙ ሙሐመድ እንዳላሉ “ድግምተኛ፣ እብድ፣ አባትና ልጅን የሚለያይ፣ ገጣሚ….” እያሉ ይሰድቧቸውና ስማቸውን ያጠፉ ጀመር፡፡ አለ የሚባል ሁሉ ፈተና ደረሰባቸው፡፡
ጥያቄ አለኝ ሰሃባዎች መውሊድን አላከበሩም ነበር ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ስለሚጠሉ ወይንም በሳቸው መወለድ ስለተናደዱና ስለበሸቁ ነበርን?
በፍፁም፡፡ ሰሃባዎች ማለት በጣም ስነስርኣት ያላቸው ትውልድ ነበሩ፡፡ አደለም መልክተኛው በህይወት እያሉ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከሞቱም በኋላ የሳቸውን ትእዛዝ ታዘው ለሁለት አገር ድል በቅተዋል፡፡ ዛሬ ይህ ኡመት አላህ ካዘነለት ውጭ ሱና እንከተል እየተባለ ወደ ቢድኣ ይሮጣል፡፡ ይህም ኡማዋ ላለበት ውርደት ሰበብ ሆኗል፡፡ አላህ የሳቸውን ሱና አጥብቀው፣ የሱናን ባንዲራ ከፍ አድርጎው ለድል ከሚጎናፀፉት ያድርገን፡፡
ዛሬ ዛሬ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንደገለፁት “የማይሰሩትን የሚናገሩ፣ ያልታዘዙትን የሚሰሩ” ሰዎች ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎችን ከቻልን በእጃችን እንድናስቆም፣ ካልቻልን በምላሳችን እንናገር፣ ካልቻልን በቀልባችን እንድንጠላ ነግረውናል፡፡
አላህ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መወለዳቸውን ሳይሆን መላካቸውን ነው ፀጋ፣ ልገሳ ብሎ የጠራው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
لَقَدْ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ يَتْلُوا۟ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِهِۦ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَإِن كَانُوا۟ مِن قَبْلُ لَفِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ
አላህ በምእምናን ላይ ከጎሳቸው የኾነን፤ በእነርሱ ላይ አንቀጾቹን የሚያነብ፣ የሚጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልእክተኛ በውስጣቸው በላከ ጊዜ፤ በእርግጥ ለገሰላቸው፡፡ እነርሱም ከዚያ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ፡፡
እኛ እዚህ ዲን ላይ ያለን ድርሻ መከተል ብቻ ነው፡፡ መጨመር እና መቀነስ ለእሳት ይዳርጋል፡፡ አላህ ኢድ እና አረፋን እንድናከብር እንደ ደነገገልን መውሊድን እንድናከብር ቢያዘን እንሰራ ነበር፡፡ ነገር ግን የሃይማኖቱ ባለቤት አላህ አላዘዘንም እኛም ስነስርኣት ይዘን ሰይጣን የሚያመጣልንን ወጥመድ አንቀበልም ብለን ይሀው በሱና ላይ ሰሃባዎች በነበሩበት መንገድ ላይ ፀንተናል፡፡ አልሐምዱሊላህ፡፡
ሰይጣን በነብዩ ውዴታ ስም አላህ ያላዘዘውን እንዳያሰራን ወጥመዶቹን ጠንቅቀን እንወቅ፡፡ ነሷራች ኢሳን (አለይሂ ሰላም) ያመለኩት ወደውት እንጂ ጠልተውት አይደለም፡፡ ስለዚህ የአላህ ባሪያ የሆኑትን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስንወድ አላህና መልክተኛው ያዘዙንን ብቻ በመታዘዝ ከከለከሉን በመራቅ ብቻና ብቻ ነው፡፡ አላህ እና መልክተኛው ያላዘዙንን ሰርተን “ለነብዩ ያለኝን ውዴታ ለመግለፅ ነው” ብንል ምክንያት አይሆነንም፡፡
አይደለም መልክተኛውን አላህን መውደዳችን እንኳን የሚረጋገጠው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) በመከተል ነው፡፡ መከተል ሲባል የሰሩትን በመስራት የከለከሉትንና ያልሰሩትን ከመስራት በመራቅ፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በመልክተኛ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ አሚን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
65 viewsGlamor, 15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 22:44:42 ስለዳሩል አርቀም ኢስላማዊ ጀመአ ምን ያውቃሉ ?
ዳሩል አርቀም ጀመአ የተለያዩ ኸይር ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ጀመአ ነው ።ለአብነትም
*ለረመዳን አስቤዛ
*ለአረፋ የቲም ህጻናትን ልብስ ማልበስ
*ኡዱህያ ለተቸገሩ ሰዎች መስጠት/ማድረስ
እኒህን ስራዎች ሲሰራ ቆይቷል ።አሁን ደግሞ የአንድ አቅመ ደካማን ቤት ለማሳደስ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ። እርሶም የዚህ ኸይር ስራ ተካይ ይሆኑ ዘንድ በአሏህ ስም እንጠይቃለን



የሚነዩበትን መንገድ አመቻችተናል ።


"ተማሪ ነኝ ብር የለኝም "
telegram ከምትገቡበት ቀንሳችሁ

"እኔ በግሌ ምረዳው ሰው አለ "

ወንድሜ እህቴ ሰደቃኮ ገንዘብን አታጎልም

የአሏህ ባሮች ሆይ ለምን ያለንን ለመስጠት እንሰስታለን ። አንድ ብርም ትሁን ለአኺራችን ትተቅመናለች።
እርስዎ ለመስጠት ፈቃደኛ ይሁኑ እንጂ እኛ መንገዱን አመቻችተንልዎታል።

*በካርድ 0913219422 ላይ ካርድ በመላክ ያለዎትን ይነይቱ

* በኢትዩጲያ ንግድ ባንክ 1000451773759
41 viewsGlamor, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 19:56:48
ውዶቼ ለአላህ ብላቹ ዱአ አርጉላት የቻላቹ አግዞት ሁላችሁም ፖስት በማረግ ተባበሩን
"ማንም ሰው በዚህ ምድር ለሌላው ሰው አዛኝ አይሆንም፤ የትንሳኤ ቀን አሏህ ﷻ ያዘነለት ቢሆን እንጅ"

~ ዑመር ኢብን አብዱልዓዚዝ رحمه الله
12 viewsibnu rebah, 16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 19:56:48 " #ልጄ_አይኗን_እያየሁ_ልትሞትብኝ_ነው " እናት

ይህች አንጀት የምትበላ ቆንጅዬ የ4ወር ጨቅላ #ሰብሪና_ካሊድ ትባላለች!ለእናትና አባቷ የመጀመሪያ ልጅ ናት!!

ራስደስታ ሆስፒታል ተወልዳ በጥሩ ጤንነት ወደ ቤቷ ብትገባም ከወራት በኋላ ጡት አልጠባም እያለች ስታስቸግር፣ላብና ለቅሶዋ ሲያስጨንቃቸው እናት ወደ
ሆስፒታል ወስዳት"ልጄ ምን ሆናብኝ ነው?ብላ እያለቀሰች ጠየቀች!

ከተለያየ ምርመራ በኋላ ዶክተሮቹ በሚያሳዝን ሁኔታ ትንሿ #ሰብሪና የልብ ቧንቧ መጥበብ ተከስቶባታል በአስቸኳይ ህክምና ካላገኘች ህይወቷ አደጋ ላይ ነው" ብለዋታል!!

አባት ሞተረኛ እናት ደግሞ የቤት እመቤት ሆና ኑሮው ሲከብዳቸው ከወጡበት ቤተሰብ ቤት ተመልሰው እየኖሩና እንደገና ለማገገም እየሞከሩ ሌላ መከራና ስቃይ ደግሞ በልጃቸው ከባድ ህመም መጣባቸው!!

ህክምናው ሀገር ውስጥ በግል በአስቸኳይ ቀዶጥገና እንድትሰራ 500,000 ብር ተጠይቀው ጨንቋቸዋል!

እናንተ ደጋጎች ይህችን ጨቅላ ተባብረን እናድናት
ምንም ማድረግ ባንችል #በዱዐቹ #ሼር በማድረግ እንተባበራት
#አካውንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000263049032-ሀናን ኑሪ
#ስልክ
0927190507-ሀናን(እናት)
0934441194-ካሊድ
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
12 viewsibnu rebah, 16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 11:32:45 #poem_354 (ነሱሀ አወል) ከሳቋ ላይ የሚመረት አለ ሀሴት አለ ደስታ፣ የልብ ምቴን የሚጨምር የሚያስጨንቅ በድውታ። (ያለልኩ የሚያስመታ!) ከጥርሷ ላይ የሚታለብ ልብ አጥጋቢ አለ ፍቅር፣ ፀሊም ልቤን ሚያሽቀረቅር። ፈገግ ስትል..! የሚትሰልብ ከእውን አለም፣ አለ አደይ አለ ተስፋ የሚታለም። ትሳቅ ብቻ...! ልቤን ትውጋው ቀልቤን ትግፈፍ፣ በሳቋ ላይ እንድንጣለል እንድንሳፈፍ ። ትሳቅ…
44 viewsGlamor, 08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 11:32:13 #poem_354

(ነሱሀ አወል)

ከሳቋ ላይ የሚመረት
አለ ሀሴት
አለ ደስታ፣
የልብ ምቴን የሚጨምር
የሚያስጨንቅ በድውታ።
(ያለልኩ የሚያስመታ!)

ከጥርሷ ላይ የሚታለብ
ልብ አጥጋቢ
አለ ፍቅር፣
ፀሊም ልቤን
ሚያሽቀረቅር።

ፈገግ ስትል..!
የሚትሰልብ
ከእውን አለም፣
አለ አደይ
አለ ተስፋ
የሚታለም።

ትሳቅ ብቻ...!
ልቤን ትውጋው
ቀልቤን ትግፈፍ፣
በሳቋ ላይ እንድንጣለል
እንድንሳፈፍ ።

ትሳቅ ብቻ...!
ያምርባታል
እስከማመር እንጥፍጣፊ፣
ፈገግ ትበል ትፈውሰኝ
ከአለም ጥፊ።

እስቲ ሳቂ!

http://t.me/Nesuhaawel_poem
42 viewsGlamor, 08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 08:16:59 መውሊድና እልክ
6 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ