Get Mystery Box with random crypto!

እውን አላህ እጅ የለውም? ~ ህሊና ላለው ሰው “አላህ እጅ የለውም” የሚል እምነት አስቀያሚና እጅ | Bilal Media & Communication

እውን አላህ እጅ የለውም?
~
ህሊና ላለው ሰው “አላህ እጅ የለውም” የሚል እምነት አስቀያሚና እጅጉን የሚያሳፍር ነው። ግና አእምሯቸው በእምነት የለሾች ፍልስፍና በመበከሉ የተነሳ ይህንን አጉል እምነት ተውሒድ ያደረጉ፣ ይባስ ብሎም ያልተጋራቸውን በሙሽ^ሪክነት የሚወነጅሉ አንጃዎች ተፈልፍለዋል። በዘመናችን ይህንን ጥፉ አመለካከት ከሚያራምዱ አንጃዎች ውስጥ “አሕ -ባሽ” ፊታውራሪ ነው። ይህ የአሕ -ባሽ አመለካከት ከሙዕተዚላ የተኮረጀ እምነት ነው። ለዚህም ሁለት አይነት መረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል።
1ኛ፡- የሙዕተዚላዎችን ስራዎች። ለምሳሌ የቃዲ ዐብዱል ጀባር አልሙዕተዚሊን ስራዎች። [ሸርሑ ኡሱሊል ኸምሳ፡ 228] [ሙተሻቢሁል ቁርኣን፡ 231]
2ኛ፡- አሕ -ባሾች እንከተላቸዋለን የሚሏቸው ኢማሞች ምስክርነት። ለምሳሌ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪና አቡ መንሱር አልበግዳዲ ይህ እምነት የሙዕተዚላ ዐቂዳ እንደሆነ መስክረዋል። [መቃላቱል ኢስላሚዪ፞ን፡ 157፣ 167] [ኡሱሉዲን፡ 228]
ስለ ራሱም ይሁን ስለሌሎች ከማንም በላይ አዋቂ የሆነው ጌታ ግን እጅ እንዳለው በግልፅ ቋንቋ ይናገራል። መልእክተኛውም ﷺ እንዲሁ። ጥቂት ማስረጃዎችን እንመልከት፡-
(قَالَ یَـٰۤإِبۡلِیسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسۡجُدَ لِمَا خَلَقۡتُ بِیَدَیَّۖ )
{ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ?} [ሷድ፡ 75]
ከዚች አንቀፅ አባታችን ኣደም በአላህ እጆች የተፈጠሩ ክቡር ፍጡር እንደሆኑ ማንም ይረዳል፡፡ አሕ -ባሽ ሲቀር። እነሱ ግን “እጅ”/ “የድ” የሚለውን “ችሎታ / ፀጋ ማለት ነው” ይላሉ።
- ለችሎታማ ሁሉም የተፈጠረው በአላህ ችሎታ ነው። እዚህ ላይ በልዩ ሁኔታ አክብሮ እንደፈጠራቸው ሲናገር ነው “በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት” ማለቱ። የ“እጅ” ትርጓሜው “ችሎታ” ቢሆን ኖሮ ኣደም ከኢብሊስ ልዩነት ባልነበራቸው ነበር። ኢብሊስም በአላህ ችሎታ የተፈጠረ ነውና።
- እጅ ማለት ችሎታ ቢሆን ኖሮ {በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት} ሲለው ኢብሊስ “እኔስ በችሎታህ አይደል የተፈጠርኩት?” ይል ነበር። ግን አላለም። ከኢብሊስ ከፍ ብለህ አስብ እንጂ!!
አዎ የጥፋት ቁንጮው ኢብሊስ በአላህ እጆች አልካደም። “የለም! በእጆችህ አልፈጠርከውም። ሲጀመር እጅ የት አለህና?!” አላለም!! “ከኛ ወዲያ ተውሒድ አዋቂ ላሳር” የሚሉ አሕ -ባሾች ግን “እጅ የለውም” ሲሉ ኢብሊስ እንኳን ያልደፈረውን ጥፋት እየፈፀሙ ነው።

ሌላ ማስረጃ፡-
(وَقَالَتِ ٱلۡیَهُودُ یَدُ ٱللَّهِ مَغۡلُولَةٌۚ غُلَّتۡ أَیۡدِیهِمۡ وَلُعِنُوا۟ بِمَا قَالُوا۟ۘ بَلۡ یَدَاهُ مَبۡسُوطَتَانِ یُنفِقُ كَیۡفَ یَشَاۤءُۚ)
{አይሁዶችም “የአላህ እጅ የተጠፈረች ናት” አሉ። እጆቻቸው ይጠፈሩ!! ይልቅ ሁለቱም እጆቹ የተዘረጉ ናቸው። እንደሚሻ ይለግሳል፡፡} [ማኢዳህ፡ 64]
አስተውሉ! አይሁዶቹ የተረ-ገሙት “የአላህ እጅ የተጠፈረች ናት” በማለታቸው እንጂ ከነ ጭራሹ “አላህ እጅ የለውም” ብለው አይደለም። አሕ -ባሾችስ? አይሁዳውያን ያልተዳፈሩትን እንኳን በመሻገር ጭራሽ ለአላህ እጅ መኖሩን አስተባብለዋል።
በሐዲሥም ከነብዩ ﷺ የተላለፉ ብዙ ማስረጃዎች አሉ። ለምሳሌ፡-
يُجْمَعُ المُؤْمِنُونَ يَوْمَ القِيَامَةِ فَيَقُولُونَ: لَوِ اسْتَشْفَعْنَا إِلَى رَبِّنَا فَيُرِيحُنَا مِنْ مَكَانِنَا هَذَا، فَيَأْتُونَ آدَمَ فَيَقُولُونَ لَهُ: أَنْتَ آدَمُ أَبُو البَشَرِ، خَلَقَكَ اللَّهُ بِيَدِهِ، وَأَسْجَدَ لَكَ المَلاَئِكَةَ، وَعَلَّمَكَ أَسْمَاءَ كُلِّ شَيْءٍ فَاشْفَعْ لَنَا إِلَى رَبِّنَا حَتَّى يُرِيحَنَا
{በቂያማ ቀን አማኞች ይሰበሰቡና ‘ወደ ጌታችን አማላጅ ብንልክና ከዚህ ቦታችን ቢያሳርፈን’ ይላሉ። ከዚያም ኣደም ዘንድ ይመጡና ‘አንተ የሰው ዘር ሁሉ አባት የሆንከው ኣደም ነህ። አላህ #በእጁ ፈጥሮሃል። መላእክትን አሰግዶልሃል። የሁሉን ነገር ስሞችም አስተምሮሃል። ያሳርፈን ዘንድ ጌታችን ዘንድ አማልደን’ ይላሉ። … } [ቡኻሪ፡ 7516]
يَأْخُذُ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ سَمَاوَاتِهِ وَأَرَضِيهِ بِيَدَيْهِ، فَيَقُولُ: أَنَا اللهُ - وَيَقْبِضُ أَصَابِعَهُ وَيَبْسُطُهَا - أَنَا الْمَلِكُ " …
{አላህ - ዐዘ ወጀል - ሰማያቱንና ምድሮቹን #በሁለት_እጆቹ ይይዝና ‘እኔ ነኝ አላህ! - ጣቶቻቸውን እየጨበጡና እየዘረጉ- እኔ ነኝ ንጉሱ’ ይላል።} … [ሙስሊም፡ 2788]
አያዎችንና ሐዲሦችን በዚህ ላይ ልግታ። ለማሳጠር ስል የሰለፎችን ንግግርም አላካትትም። እውነታው እንደ ፀሐይ ፍንትው ብሎ ሳለ የሚጨናበሱ ሰዎች መኖራቸው የቢድዐ ዳፍንት ምን ያክል ከባድ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። “አሕ -ባሾችስ ለአቋማቸው ማጠናከሪያ ምን ይጠቅሳሉ?” ካላችሁ “እጅ የለውም” የሚል ቀጥተኛ ማስረጃ መቼም አያመጡም። የሚጠቅሱት ሁለት ማምታቻ ነው።

[ማምታቻ አንድ]፡-

“የሚመስለው የለም” የሚለውንና መሰል አንቀፆችን በመጥቀስ ከሶሐቦች ያልተገኘ የራሳቸውን ትርጉም መስጠት። “ምን አገናኘው?” ካላችሁ እነሱ ዘንድ “እጅ አለው” ማለት ማመሳሰል ነው። በቃ! “እንዲያ ከሆነ ቁርኣኑ የማመሳሰልና የሺርክ ሰነድ ነው ማለት ነው” ብትሏቸው ምንም ሳያፍሩ “አዎ ዟሂሩ ኩ^ፍ^ር ነው” ይላሉ። እንዲያ ከሆነ የመጀመሪያ አመሳሳዮች አላህና መልእክተኛው ናቸው ማለት ነው!! አዑዙ ቢላህ! ሐቂቃው ግን አላህን እራሱን በገለፀበት፣ ነብዩም ﷺ አላህን በገለፁበት መግለፅ ፈፅሞ ማመሳሰል አለመሆኑ ነው። የቡኻሪ ሸይኽ የሆኑት ኢማም ኑዐይም ብኑ ሐማድ ረሒመሁላህ የተናገሩትን ተመልከቱ፡-
مَنْ شَبَّهَ اللَّهَ بِشَيْءٍ مِنْ خَلْقِهِ فَقَدْ كَفَ-رَ وَمَنْ أَنْكَرَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ فَقَدْ كَفَ-رَ فَلَيْسَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ وَرَسُولُهُ تَشْبِيهٌ
“አላህን ከፍጡሩ በየትኛውም ያመሳሰለ በርግጥም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበትን የካደም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበት እና መልእክተኛው (እሱን የገለፁበት) ማመሳሰል አይደለም።” [ላለካኢ፡ ቁ. 936]
ይሄ የኑዐይም ንግግር በአላህ መገለጫዎች ዙሪያ ቁልፍ የሆነ ቀመር ነው። ከውስጡ ሶስት ወሳኝ ህጎችን እናገኝበታለን። እነሱም፡-
1ኛ፡- አላህን በፍጡር ማመሳሰል ክህ -ደት ስለሆነ መጠንቀቅ እንደሚገባ።
2ኛ፡- አላህ እራሱን የገለፀበትን ማስተባበል ክህ -ደት እንደሆነ።
3ኛ፡- በቁርኣንና በሐዲሥ ውስጥ ፈፅሞ ማመሳሰል እንደሌለ። (አሕ -ባሽ ግን ቁርኣንና ሐዲሥ በማመሳሰል የታጨቀ ነው ብለው ነው የሚያምኑት።)

[ማምታቻ ሁለት]፡-