Get Mystery Box with random crypto!

ሌላኛው የሚጠቅሱት “ማስረጃ” በታዋቂ ዑለማዎች ማስፈራራት ነው። ቁርኣንና ሐዲሥ ስትጠቅሱላቸው እነ | Bilal Media & Communication

ሌላኛው የሚጠቅሱት “ማስረጃ” በታዋቂ ዑለማዎች ማስፈራራት ነው። ቁርኣንና ሐዲሥ ስትጠቅሱላቸው እነሱ “ነወዊይ፣ ኢብኑ ሐጀር፣…” ይላሉ። ከቁርኣንና ሐዲሥ በተቃራኒ ፍፁም ያልሆኑ ሰዎችን ማጣቀስ ነውር ነው። “እናንተ ቁርኣኑንና ሐዲሡን ከነሱ በላይ ልታውቁት ነወይ?” ይላሉ። መልካም! እነሱስ ቁርኣኑንና ሐዲሡን ከሰለፎች በላይ ሊያውቁት ነወይ? እስኪ የሰለፎቹን ተፍሲር መርምሩና አደብ ይኑራችሁ።
የአሕ -ባሽ አቋም ሌላው ቀርቶ “እንከተላቸዋለን” ከሚሏቸው የአቡል ሐሰን አልአሽዐሪ አቋም ጋር እንኳን አይገጥምም፡፡ አቡል ሐሰን የአህሉ ሱና፞ን ዐቂዳ ሲዘረዝሩ እንዲህ ብለዋል፡-
وأن الله سبحانه على عرشه كما قال: الرحمن على العرش استوى وأن له يدين بلا كيف كما قال: خلقت بيدي وكما قال: بل يداه مبسوطتان.
“የጠራው አላህ ‘አረ፞ሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ’ እንዳለው በዐርሹ ላይ ነው። ሁለት እጆች እንዳሉትም እንዲሁ ያለ አኳኋን (ያፀድቃሉ)። ‘በሁለት እጆቼ ፈጠርኩ’ እንዳለው፤ ‘ይልቁንም ሁለት እጆቹ የተዘረጉ ናቸው’ እንዳለውም (እንዲሁ ያፀድቃሉ)።” [መቃላቱል ኢስላሚዪ፞ን፡ 290]
ከዚያም የአህሉ ሱና፞ን አቋም በሰፊው ከዘረዘሩ በኋላ “እነዚህ ባጠቃላይ (የሱና፞ ሰዎች) የሚያዝዙባቸው፣ የሚተገብሯቸውና የሚያምኑባቸው ናቸው። በዘረዘረነው አቋማቸው ሁሉ እናምናለን። እንጓዝበታለንም” ብለው ቋጭተዋል። [መቃላት፡ 297]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር፡ 12/2012)