Get Mystery Box with random crypto!

Bilal Media & Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication B
የቴሌግራም ቻናል አርማ linkbi7 — Bilal Media & Communication
የሰርጥ አድራሻ: @linkbi7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-02-24 17:30:39 (ነሱሀ አወል)

⎡ሰው አይደለች ይደክማታል⎤

ከውጪውም ከውስጥም ያለ ሰላሟን እስክታጣ ትጎሳቆላለች..ግን እንዲሁ አትቀርም እንባዋን ጠርጋ ዳግም ታንሰራራለች... አምላኳ ተስፋዋ እንደሆነ አትዘነጋውም!
የኔ ሴት እንዲህ ናት ነኩታ ምታንሰራራ ፣ ፈርሳ ራሷን ምትሰራ ፣ ተሰብራ የምትጠገን..አቅሟ አምላኳ የሆነ ጀግና ሴት!

አምላኬ ሆይ ልቧን ጠግን
20 viewsGlamor, 14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 17:17:42 የዘር ፖለቲካ እምነታችንን እንዳይነጥቀን
~
ከ150 አመታት በፊት የኩሽ ህዝብ እምነት ዋቄፈና ነበር የሚል ፅሁፍ አየሁኝ። ይሄ ሙሉ ለሙሉ ስህተት ነው። በኩሽ የቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች ውስጥ ሶማሊና አፋር ይጠቀሳሉ። የሁለቱም ህዝቦች እስልምና የ150 አመት ታሪክ አይደለም።
ምናልባት ፀሀፊው ኩሽ ሲል የሚፈልገው ኦሮሞ ማለቱ ይመስላል። ፍላጎቱ እንደዚያ ከሆነም፡
1- ኩሽ በሚል ሌሎች ህዝቦችን በሚጠቀልል ሰፊ ቃል መግለፁ ተገቢ አይደለም።
2- የኦሮሞ ህዝብም ቢሆን የእስልምና ታሪኩ የመቶ አምሳ አመት ታሪክ አይደለም፤ በተለይም የምስራቁ ክፍል።

ለፖለቲካዊ ግብ ሲባል የኦሮሞን ህዝብ ከኢስላም የማራቅ ጥረቶች በተደጋጋሚ ይታያሉ። "እስልምናም ክርስትናም መጤ ናቸው፤ ነባሩ እምነታችን ዋቄፈና ነው"፣ "ሃይማኖት ህዝባችንን ለያይቷል" ፣ ... በሚሉ ሴራዎች ሙስሊሙ ለሃይማኖቱ ጀርባ እንዲሰጥ ለማድረግ የሚሞክሩት ቀላል አይደሉም። ቁጥሩን መገመት ባይቻልም በነዚህ አካላት ወጥመድ ውስጥ የወደቁ ሙስሊሞች በተጨባጭ አሉ። "ኦሮሞነት ከሃይማኖትም በላይ ነው" የሚሉ ሰዎችን ማየት በጣም የሚዘገንን ነገር ነው።
ወገኔ ዘር፣ ጎሳ፣ ብሄር፣ ... እንደ ኢስላም ተራ ነገሮች ናቸው። ኢስላም ከዘር፣ ከሃገር ቀርቶ ከህይወትም በላይ ነው። ከሃገርም ከዘርም በላይ ስለሆነም ነው ሶሐቦች አገራቸውን ጥለው ሐበሻ ድረስ የተሰደዱት። ስለሆነም ነው ነብያችን ሶላለሁ ዐለይሂ ወሰለም መካን ያክል አገር ጥለው የተሰደዱት። ኢስላም ከዘር በላይ ስለሆነም ነው ሶሐቦች በበድርና በኡሑድ ዘመቻ ቁረይሾች ጋር በሰይፍ የተሞሻለቁት። ከኢስላም የሚበልጥ ቀርቶ የሚወዳደር እንኳ ምንም ነገር የለም። ስለ እምነቴ አንገቴን እሰጣለሁ። ስለ ብሄሬ ግን ጠብታ ደም አልገብርም። ለብሄሬ ስል የማንንም ነፍስ ቀርቶ ጠብታ ደም አላፈስም። ብሄርን ብቻ ነጥሎ መሰረት ላደረገ ትግል የስሙኒ አስተዋፅኦ እንዲኖረኝ አልፈልግም።
ወላጆቼ፣ ቤተሰቦቼ ከዘር ማንነት ከቋንቋ በላይ ናቸው። ኢስላሜ ደግሞ ከነሱም በላይ ነው። በዘርም በጉርብትናም የማልቀርበው የጉራጌ ሙስሊም (ምሳሌ ነው) በዘር ከሚገናኘኝ ሙስሊም ያልሆነ ጎረቤቴ በላይ ለልቤ የቀረበ ነው። ኧረ ፈፅሞ ለንፅፅርም አይቀርቡም።
መጠቆም የፈለግኩት የዘር አጀንዳ ከልክ አልፎ እምነታችንን በሚነጥቅ ደረጃ ስለ ደረሰ ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል። ዱዓቶችና መሻይኾች ሳይቀሩ የችግሩ ሰለባ እየሆኑ ስለሆነ ከፍተኛ የማንቃት ስራ ያስፈልጋል። በዘር ሰበብ ባሳዛኝ ሁኔታ የሙስሊም ደም በያካባቢው እየፈሰሰ፣ ሚሊዮኖች እየተፈናቀሉ በርካታ መሻይኾችና ታዋቂ ሰዎች "አላህን እንፍራ" የሚል ማስታወሻ ለማስተላለፍ እንኳ ወኔ አጥተዋል። ያሳዝናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
14 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 20:08:48 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑭☞ ጆን ዊሊያም ድራፐር  አሜሪካዊው ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ፣ እና የታሪክ አጥኚ


☞ “ስብከቱ ሳይሆን የሃይማኖቱ ዘላቂነት ነው አድናቆታችንን እንድንገልፅ ያደረገን፡፡ በመካና መዲና የተጠነሰሰው ተመሳሳይ የጠራ ፍፁም የሆነ የእምነት አሻራ ከአስራ ሁለት ክፍለ ዘመን በኃላም በቁርዓን የተቀየሩ ህንዶች አፍሪካውያን ቱርኮች ተጠበቀ፡፡የሙሐመድ ተከታዮች የሚያምኑበትና የሚሰዉለትን ነገር በሰው የስሜት ህዋሳቶችና ሃሳቦች ደረጃ ዝቅ የሚያደርገውን የሰይጣንን ፈተና ተቋቋሙ፡፡


ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም
)፦



☞⑮☞ Annie Beasant /አኒ ቤሳንት (እውቅ የብሪታኒያ ሶሻሊስት፣ የመለኮታዊ ጥበብ ፍልስፍና እና የሴቶች መብት አቀንቃኝ፣ ጸሐፊ፣ የመድረክ ተናጋሪ እና የአየርላንድ እና ሕንድ የነጻነት ትግል እውቅ ደጋፊ)


☞‹‹የዚያን የዓረቢያን ታላቅ ነቢይ ታሪክ እና ሥነ-ምግባር ላጠና፣ እንዴት ባለ ጥበብ እንዳስተማረ እና እንዴት እንደኖረ ለሚያውቅ
ሰው እርሱን ከማክበር ውጭ ምርጫ አይኖረውም፡፡ ከአምላክ ታላላቅ መልእክተኞች አንዱ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ከምናገረው
ብዙውን የምታውቁት ቢሆንም እኔ ራሴ ስለእርሱ ደግሜ ባነበብኩ ቁጥር ለዚያ ብርቱ የዓረቢያ መምህር አዲስ ክብር እና ግርምት
ያጭርብኛል፡፡››
The Life and Teachings of Muhammad, Madras 1932, p. 4
18 viewsGlamor, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 18:01:15 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑬☞ Major Arthur Glyn Leonard /ሜጀር አርተር ግሊን ሊዮናርድ/ (የብሪታኒያ ሚሊታሪ ኤክስፐርት)☞‹‹በዚህች ምድር ላይ አምላክን ያገኘ ሰው ካለ፣ በንጹህ እና ቅዱስ ፍላጎት ገፊነት ሕይወቱን ለፈጣሪ አገልግሎት የሰጠ ሰው ካለ ያለጥርጥር ፣ ይልቁንም በእርግጥ፣ ያ ሰው የዓረቢያው ቅዱስ ነቢይ ሙሃመድ ነው! … ዓረቦችን ከፍ ያደረጋቸው የሙሐመድ ድንቅ ችሎታ እና ያሰረፀባቸው የእስልምና ሃይማኖት እስትንፋስ ነበር፡፡ ከግድየለሽነት እና ከጎሠኝነት አዘቅት አውጥቶ ወደ ድንቅ ብሔራዊ አንድነት እና ታላቅ ግዛት አሸጋገራቸው፡፡ የሙሐመድ ምክንያታዊነት ከፍታ እና ያሰረፀው ቀላልነት፣ ቁጥብነት እና ንጹህነት፣ እንዲሁም የመሥራቹ ለራሱ መርሆች ያለው ተገዢነት ነበር የእውነተኛ ጉጉትን ስበት ፈጥሮ የማኅበረሰቡን ሞራላዊ እና እውቀታዊ ድሩን የገመደው፡፡ …
(ሙሐመድ) የውልደት አጋጣሚ ሆኖ ዓረባዊ ነበር፡፡ አምላክን እና ተፈጥሮን ከሁሉም አስቀድሟል፡፡ ከምንም በላይ ሰውኛ ያደረገው፣ ከዘመኑ የቀደመ እንዲሆን ያስቻለውም ይኸው ነበር፡፡ በእርግጥም
ሙሐመድ ከዘመኑ በምእተ ዓመታት የቀደመ ሰው ለመሆኑ ቅንጣት አያጠራጥርም፡፡››
☞Islam, Her Moral and Spiritual Values
16 viewsGlamor, 15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 06:26:39 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦

☞⑫☞ ↠ “ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ይዞት የመጣው እምነት ከአእምሮና ከጥበብ ጋር ልዩ ቁርኝት ስላለው አለምን ሁሉ እንደሚያዳርስ አምናለሁ::”
ታዋቂው የሩሲያ ፀሐፊ ሊዮ ቶልስቶይ
34 viewsGlamor, 03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 18:24:27
ተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ አሕመድ ኣደም ከሚታወቅባቸው በርካታ ጥዑም ደርሶቹና ዳዕዋዎቹ ባሻገር «ቁርኣን የህይዎት ብርሃን» በተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ብቅ ብሏል።


መጽሐፉ ስለ ቁርኣን ትሩፋት፣ የንባብ ህግጋት፣ የሒፍዝና የሓፊዞች ስርዓትን በተመለከተ የሚያትት ነው።


በአላህ ፈቃድ በቅርብ ቀን ገበያ ላይ ይውላል።

ገዝተን ለማንበብ፣ ለቤተሰባችንና ለወዳጅ ዘመዳችን በስጦታ መልክ ለማቅረብ ከወዲሁ እንዘጋጅ።

ኡስታዙንም አላህ ይጨምርለት፣ ምንዳውንም ይክፈለው፣ ኢኽላሱንም ይወፍቀው። እኛንም አንብበን የምንጠቀምበት ያድርገን።
17 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 17:53:28 ለምን ይዋሻል?
~
ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሙስሊሞች ባለውለታ ናት እያሉ ሲፅፉ ነበር። ይሄ ፍፁም ሐሰት ነው። እንዲያውም እውነታው በተቃራኒው ነው ያለው። በታሪክ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ለዘመናት የደረሰው ግፍ በቤተ ክርስቲያን ቡራኬ ነው ሲፈፀም የኖረው።

* በስጦታ ተደልለው ሶሐቦችን ለመውሰድ አልመው ለመጡት የቁረይሽ መልእክተኞች ንጉስ ነጃሺ አሳልፎ እንዲሰጥ የጠየቁት ካህናት እኮ ናቸው።
* በነ አፄ አምደ ጽዮን፣ በነ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ፣ ሙስሊሞች ላይ የደረሰው እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በቤተ ክርስቲያን ይሁንታ አልነበረም ወይ ሲፈፀም የነበረው?
* የጎንደር ሙስሊሞች ከማህበረሰቡ ተነጥለው ወደ "እስላምጌ" (አዲስ ዓለም) እንዲገለሉ የተደረጉት በካህናት ጉትጎታ አልነበረም ወይ?
* በአፄ ዮሐንስ ሙስሊሞች ላይ በተፈፀመው ሰፊ ጭፍጨፋ ላይ የነበረው የቤተ ክርስቲያን ሚናስ ተዘንግቶ ነው ወይ?
* በሃረር ወደ ቤተ ክርስቲያንነት የተቀየሩት መስጂዶች ዛሬም ህያው ምስክር አይደሉም ወይ?
* ልጅ እያሱ ላይ ለተፈፀመው ደባ ቀዳሚው ክስ ምን ነበር? "ሰልሟል" የሚል አልነበር? ሴራቸው የተሳካው በጳጳሱ ድጋፍ፣ በቤተ ክርስቲያን ይሁንታ አልነበረም?
* "መስጂዱ ካልፈረሰ ታቦቱ አልንቀሳቀስ አለ" የሚለው አስቂኝና አሰልቺ ድራማቸው ተረስቶ ነው?

ወይ ታሪክ አንብቡ ወይም አርፋችሁ ተቀመጡ። ከሺ ዓመታት በላይ ለዘለቀው ግፍ ይቅርታ መጠየቁ ቢቀር ጭራሽ ባለውለታ አድርገን እንድናስብ ይፈልጋሉ። እነሱስ ያው ስራቸው ነው። የሚደንቀው አንዳንድ ከነፋሱ ጋር የሚወዛወዙ ሸምበቆ አቋም ያላቸው አሸርጋጆች ሁኔታ ነው። ሸምበቆን "አቋምህ እንዴት ነው?" ቢሉት ፤ "እኔ ምን አውቄ! ነፋሱን ጠይቁት አለ" ይባላል። ነገም ነፍሱን እያዩ እንደሚከሰቱ ይጠበቃል። በሙስሊሞች ግፍና በደል ላይ ግን ትንፋሻቸው አይሰማም። እነዚህ ግን የውሸት ታሪክ ጭምር እየፈጠሩ ያራግባሉ። የመቻቻልን እሴት በዚህ መልኩ የሚረዳ አካል ለአስተሳሰብ ልምሻ የተጋለጠ አሳዛኝ ፍጡር ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
39 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 21:45:05 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑪☞Jenison Hopkins Denoson /ጄኒሰን ሆፕኪንስ ዴኒሰን/ (አሜሪካዊ የሥነ ልቦና ጠቢብ፣ በግላዊ እድገት ዙሪያ ደራሲ)


‹‹በአምስተኛው እና ስድሰተኛው ምዕተ ዓመታት ሥልጣኔ በታላቅ አደጋ ውስጥ ነበር፡፡ ሰዎች በመሪዎቻቸው ሥር እንዲሰባሰቡ እና
እንዲታዘዟቸው በማድረግ ሥልጣኔውን ተሸክመው የቆዩት አሮጌ ስሜትን መሠረት ያደረጉ ልማዶች (ባሕሎች) በመፈረካከስ ላይ ነበሩ፡፡ የሚተካቸው ሌላ ምሰሦም አልነበረም፡፡… በአራት ሺ ዓመታት ሂደት ሲገነባ የቆየው ሥልጣኔ ሊፈረካከስ ነበር፡፡ የሰው ልጅ አንዱ ጎሣ ለሌላው ጠላት ወደሆነበት እና ሕግ እና ሥርዓት ወዳልነበረበት አናርኪስት ባርቤሪዝማዊ ሥርዓት ለመመለስ ጫፍ ደርሶ ነበር፡፡ …. ሥልጣኔ ምስጥ በልቶት ሊወድቅ እየተንገዳገደ እንዳለ ዛፍ ሆኖ ነበር፡፡… የሰውን ልጅ ዳግም ወደአንድነት የሚሰበስብ፣ ስሜትን መሠረት ወዳደረገ ልማድ ዳግም በመመለስ ሥልጣኔውን የሚያተርፍ ሌላ ሰው ነበርን?…. የሰውን ልጅ ሁሉ ከምሥራቅ እስከምዕራብ ዳግም ወደአንድነት ያመጣው ብቸኛ ሰው ከዓረቦች የተወለደው (ሙሐመድ) ነበር፡፡››
J. H. Denison, Emotions as the Basis of Civilisation, pp. 265 9
17 viewsGlamor, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 19:37:11 ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦



☞⑩☞William James Durant /ዊሊያም ጄምስ ዱራንት (ክህሎተኛ አሜሪካዊ ጸሐፊ፣ የታሪክ ተመራማሪ እና ፈላስፋ)
መጨረሻ የሌለው ፀሎቱ ከፈጣሪ ጋር የተለዋወጠው ልዩ ሚስጥራዊ መንፈሳዊ ንግግር ሞቱ ከሞተ በኃላ የተጎናፀፈው ድል እነዚህ ሁሉ የሚያረጋግጡልን አስመሳይ ያለ መሆኑንና የጠበቀና ቀና እምነቱ የሰጠው ሃይል ነበር፡፡ የሚያምንበት ቀኖና(የሃይማኖት ህግጋት) ሁለት መልክ ነበረው፡፡
አንደኛው የአምላክ አንድነትና ሌላው አምላክ ቁስ አካል ያለመሆኑን የሚያስረዳ ሲሆን የመጀመርያው አምላክ ምን እንደሆነ ሲገልፅ የኃለኛው አምላክ ያልሆነውን ይነግረናል፡፡ ማለትም የመጀመርያው የውሸት ጣዖቶችን በሰይፍ ማውረድን የኃለኛው
ደግሞ በቃላት አዲስ ሃሳብ መጀመርን ይነግረናል፡፡
(speaking on The
Character Of Muhammed (pbuh))
23 viewsGlamor, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 19:52:38
❝ሳዳት❞
-------------------------------------------
እውነትን ከመስበክ ስለማትሳነፍ፡
ሐቅን ከማስተማር ስለማትዛነፍ፡
ሁሌም በወሬኞች ስለማትጠለፍ፡
እኔ እወድሀለሁ ያለ ድንበር ማለፍ፡
---------------------------------------------
መረጃህ ኢስላም ነው ንግግርህ መልካም፡
እውነትን ለመስበክ ሁሌ አታውቅም ድካም፡
በተውሒድህ ፅና ወዳጅ ሁሉ ይይህ፡
በሰለፍያ ላይ አፅንቶ ያቆይህ፡
በደዕዋ ስራህ ላይ እናከብርሀለን፡
መረጃህ አርኪ ነው እኛ እንወድሀለን፡
-----------------------------------------------
ስለማትሯሯጥ ሰወችን ለመጉዳት፡
ስለማትችልበት በስሜት መነዳት፡
ባህሪህ ስለሆነ በፀባይ ማስረዳት፡
አሏህ ይጠብቅህ ጀግናችን ነህ ሳዳት፡
------------------------------------------------
ሳዳት ወላሒ እወድሀለሁ<=>ኑረዲን
-------------------------------------------------
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
29 viewsرَاحِمَا بِنْتْ حَيْرَدِنْ☞, 16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ