Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦ ☞⑪☞Jenison Hopki | Bilal Media & Communication

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑪☞Jenison Hopkins Denoson /ጄኒሰን ሆፕኪንስ ዴኒሰን/ (አሜሪካዊ የሥነ ልቦና ጠቢብ፣ በግላዊ እድገት ዙሪያ ደራሲ)


‹‹በአምስተኛው እና ስድሰተኛው ምዕተ ዓመታት ሥልጣኔ በታላቅ አደጋ ውስጥ ነበር፡፡ ሰዎች በመሪዎቻቸው ሥር እንዲሰባሰቡ እና
እንዲታዘዟቸው በማድረግ ሥልጣኔውን ተሸክመው የቆዩት አሮጌ ስሜትን መሠረት ያደረጉ ልማዶች (ባሕሎች) በመፈረካከስ ላይ ነበሩ፡፡ የሚተካቸው ሌላ ምሰሦም አልነበረም፡፡… በአራት ሺ ዓመታት ሂደት ሲገነባ የቆየው ሥልጣኔ ሊፈረካከስ ነበር፡፡ የሰው ልጅ አንዱ ጎሣ ለሌላው ጠላት ወደሆነበት እና ሕግ እና ሥርዓት ወዳልነበረበት አናርኪስት ባርቤሪዝማዊ ሥርዓት ለመመለስ ጫፍ ደርሶ ነበር፡፡ …. ሥልጣኔ ምስጥ በልቶት ሊወድቅ እየተንገዳገደ እንዳለ ዛፍ ሆኖ ነበር፡፡… የሰውን ልጅ ዳግም ወደአንድነት የሚሰበስብ፣ ስሜትን መሠረት ወዳደረገ ልማድ ዳግም በመመለስ ሥልጣኔውን የሚያተርፍ ሌላ ሰው ነበርን?…. የሰውን ልጅ ሁሉ ከምሥራቅ እስከምዕራብ ዳግም ወደአንድነት ያመጣው ብቸኛ ሰው ከዓረቦች የተወለደው (ሙሐመድ) ነበር፡፡››
J. H. Denison, Emotions as the Basis of Civilisation, pp. 265 9