Get Mystery Box with random crypto!

ለምን ይዋሻል? ~ ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሙስሊሞች ባለውለታ ናት እያ | Bilal Media & Communication

ለምን ይዋሻል?
~
ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሙስሊሞች ባለውለታ ናት እያሉ ሲፅፉ ነበር። ይሄ ፍፁም ሐሰት ነው። እንዲያውም እውነታው በተቃራኒው ነው ያለው። በታሪክ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ለዘመናት የደረሰው ግፍ በቤተ ክርስቲያን ቡራኬ ነው ሲፈፀም የኖረው።

* በስጦታ ተደልለው ሶሐቦችን ለመውሰድ አልመው ለመጡት የቁረይሽ መልእክተኞች ንጉስ ነጃሺ አሳልፎ እንዲሰጥ የጠየቁት ካህናት እኮ ናቸው።
* በነ አፄ አምደ ጽዮን፣ በነ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ፣ ሙስሊሞች ላይ የደረሰው እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በቤተ ክርስቲያን ይሁንታ አልነበረም ወይ ሲፈፀም የነበረው?
* የጎንደር ሙስሊሞች ከማህበረሰቡ ተነጥለው ወደ "እስላምጌ" (አዲስ ዓለም) እንዲገለሉ የተደረጉት በካህናት ጉትጎታ አልነበረም ወይ?
* በአፄ ዮሐንስ ሙስሊሞች ላይ በተፈፀመው ሰፊ ጭፍጨፋ ላይ የነበረው የቤተ ክርስቲያን ሚናስ ተዘንግቶ ነው ወይ?
* በሃረር ወደ ቤተ ክርስቲያንነት የተቀየሩት መስጂዶች ዛሬም ህያው ምስክር አይደሉም ወይ?
* ልጅ እያሱ ላይ ለተፈፀመው ደባ ቀዳሚው ክስ ምን ነበር? "ሰልሟል" የሚል አልነበር? ሴራቸው የተሳካው በጳጳሱ ድጋፍ፣ በቤተ ክርስቲያን ይሁንታ አልነበረም?
* "መስጂዱ ካልፈረሰ ታቦቱ አልንቀሳቀስ አለ" የሚለው አስቂኝና አሰልቺ ድራማቸው ተረስቶ ነው?

ወይ ታሪክ አንብቡ ወይም አርፋችሁ ተቀመጡ። ከሺ ዓመታት በላይ ለዘለቀው ግፍ ይቅርታ መጠየቁ ቢቀር ጭራሽ ባለውለታ አድርገን እንድናስብ ይፈልጋሉ። እነሱስ ያው ስራቸው ነው። የሚደንቀው አንዳንድ ከነፋሱ ጋር የሚወዛወዙ ሸምበቆ አቋም ያላቸው አሸርጋጆች ሁኔታ ነው። ሸምበቆን "አቋምህ እንዴት ነው?" ቢሉት ፤ "እኔ ምን አውቄ! ነፋሱን ጠይቁት አለ" ይባላል። ነገም ነፍሱን እያዩ እንደሚከሰቱ ይጠበቃል። በሙስሊሞች ግፍና በደል ላይ ግን ትንፋሻቸው አይሰማም። እነዚህ ግን የውሸት ታሪክ ጭምር እየፈጠሩ ያራግባሉ። የመቻቻልን እሴት በዚህ መልኩ የሚረዳ አካል ለአስተሳሰብ ልምሻ የተጋለጠ አሳዛኝ ፍጡር ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor