Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦ ☞⑭☞ ጆን ዊሊያም ድራፐር | Bilal Media & Communication

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑭☞ ጆን ዊሊያም ድራፐር  አሜሪካዊው ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ፣ እና የታሪክ አጥኚ


☞ “ስብከቱ ሳይሆን የሃይማኖቱ ዘላቂነት ነው አድናቆታችንን እንድንገልፅ ያደረገን፡፡ በመካና መዲና የተጠነሰሰው ተመሳሳይ የጠራ ፍፁም የሆነ የእምነት አሻራ ከአስራ ሁለት ክፍለ ዘመን በኃላም በቁርዓን የተቀየሩ ህንዶች አፍሪካውያን ቱርኮች ተጠበቀ፡፡የሙሐመድ ተከታዮች የሚያምኑበትና የሚሰዉለትን ነገር በሰው የስሜት ህዋሳቶችና ሃሳቦች ደረጃ ዝቅ የሚያደርገውን የሰይጣንን ፈተና ተቋቋሙ፡፡


ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም
)፦



☞⑮☞ Annie Beasant /አኒ ቤሳንት (እውቅ የብሪታኒያ ሶሻሊስት፣ የመለኮታዊ ጥበብ ፍልስፍና እና የሴቶች መብት አቀንቃኝ፣ ጸሐፊ፣ የመድረክ ተናጋሪ እና የአየርላንድ እና ሕንድ የነጻነት ትግል እውቅ ደጋፊ)


☞‹‹የዚያን የዓረቢያን ታላቅ ነቢይ ታሪክ እና ሥነ-ምግባር ላጠና፣ እንዴት ባለ ጥበብ እንዳስተማረ እና እንዴት እንደኖረ ለሚያውቅ
ሰው እርሱን ከማክበር ውጭ ምርጫ አይኖረውም፡፡ ከአምላክ ታላላቅ መልእክተኞች አንዱ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ከምናገረው
ብዙውን የምታውቁት ቢሆንም እኔ ራሴ ስለእርሱ ደግሜ ባነበብኩ ቁጥር ለዚያ ብርቱ የዓረቢያ መምህር አዲስ ክብር እና ግርምት
ያጭርብኛል፡፡››
The Life and Teachings of Muhammad, Madras 1932, p. 4