Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦ ☞⑬☞ Major Arthur | Bilal Media & Communication

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑬☞ Major Arthur Glyn Leonard /ሜጀር አርተር ግሊን ሊዮናርድ/ (የብሪታኒያ ሚሊታሪ ኤክስፐርት)☞‹‹በዚህች ምድር ላይ አምላክን ያገኘ ሰው ካለ፣ በንጹህ እና ቅዱስ ፍላጎት ገፊነት ሕይወቱን ለፈጣሪ አገልግሎት የሰጠ ሰው ካለ ያለጥርጥር ፣ ይልቁንም በእርግጥ፣ ያ ሰው የዓረቢያው ቅዱስ ነቢይ ሙሃመድ ነው! … ዓረቦችን ከፍ ያደረጋቸው የሙሐመድ ድንቅ ችሎታ እና ያሰረፀባቸው የእስልምና ሃይማኖት እስትንፋስ ነበር፡፡ ከግድየለሽነት እና ከጎሠኝነት አዘቅት አውጥቶ ወደ ድንቅ ብሔራዊ አንድነት እና ታላቅ ግዛት አሸጋገራቸው፡፡ የሙሐመድ ምክንያታዊነት ከፍታ እና ያሰረፀው ቀላልነት፣ ቁጥብነት እና ንጹህነት፣ እንዲሁም የመሥራቹ ለራሱ መርሆች ያለው ተገዢነት ነበር የእውነተኛ ጉጉትን ስበት ፈጥሮ የማኅበረሰቡን ሞራላዊ እና እውቀታዊ ድሩን የገመደው፡፡ …
(ሙሐመድ) የውልደት አጋጣሚ ሆኖ ዓረባዊ ነበር፡፡ አምላክን እና ተፈጥሮን ከሁሉም አስቀድሟል፡፡ ከምንም በላይ ሰውኛ ያደረገው፣ ከዘመኑ የቀደመ እንዲሆን ያስቻለውም ይኸው ነበር፡፡ በእርግጥም
ሙሐመድ ከዘመኑ በምእተ ዓመታት የቀደመ ሰው ለመሆኑ ቅንጣት አያጠራጥርም፡፡››
☞Islam, Her Moral and Spiritual Values