Get Mystery Box with random crypto!

የወረዳ 10 አዲስ ተመራጮችን በተመለከተ ታህሳስ መጀመሪያዎቹ ላይ በእለተ ሀሙስ ቀን የየካ | Bilal Media & Communication

የወረዳ 10 አዲስ ተመራጮችን በተመለከተ

ታህሳስ መጀመሪያዎቹ ላይ በእለተ ሀሙስ ቀን የየካ ክ/ከተማ አመራሮች ደብዳቤ በመላክ ኢማሞች፣ሙአዚኖች እና የአስተዳደር ሰራተኞች በአጠቃላይ ስለ መስጅዶቻችን ይመለከተናል የሚል ሁሉ በእለተ እሁድ በአሊ ሚራ መስጅድ እንዲገኝ የሚል መልእክት ያለው ደብዳቤ ተላለፈ። ገና ይህ ጥሪ ሲተላለፍ ጀምሮ በቃ ልንባረር ነው በማለት ምንም ባልተወራበትና ንግግር ባልተደረገበት መንጫጫትና አላስፈላጊ ንግግሮችን መስማት ጀመርን

እኔ ይህ ከሆነ (በነሡ የምመራ ከሆነ) በተለይም አንድ ተራን ሠው በመጥቀስ እሱ ካልተነሣ እከፍራለው እስከመባል ደረጃ ደረሠ ልብ በሉ ይህንን የተናገረው
እብድ ወይም ስካር ላይ ሆኖ አይደለም ጤነኛ ነው
ተራ ሰው ወይም ሌላ ችግርም ያለበት እንዳይመስለን!!! ራሡን "የጃቢር መስጅድ አስተዳዳሪና ወቅፍ አድርጊ" ብሎ የሚጠራው (ብሎ የሚጠራው ነው ያልኩት) ግለሠብ ነው። በርግጥ ለዚህ ንግግር በወቅቱ ከነበረ አንድ አባት መልስ ተሠቶታል
ይህንን ንግግር (...... እከፍራለው) ያለውን ማለቴ ነው፤የቀድሞዎቹ መጅሊሶች እንኳ አልተናገሩትም
እንግዲህ የሚያወራውም እያወራ ያልተባለን በሹክሹክታ እየዘባረቀ እኛም ሹክሹክታቸውን በስፒከር እየሠማን
በዚህ ውዝግብ ውስጥ ተሁኖ የጥሪው ቀን ደርሶ እሁድ በወረዳው የሚገኙ 4 መስጅዶች ላይ ካሉ ጀመዐዎች ወደ ስብሰባው አቀናን
ከኦካሻ 5 ሰው
ከሁነይን 7 ሰው
ከአቡበከርም ተቀራራቢ የሆነ ሠው ሲመጣ
ከጃቢር ሁለት ሰው መጣ ኢማምና ቅድም እከሌ ካልተነሣ እከፍራለው ባዩ ተውፊቅ። ሌሎቹ ስለማያገባቸው ቀርቶ ሳይሆን ስላልነገራቸው ነው ም/ቱም ብዙዎቹን ለምን እንደቀሩ ስጠይቅ የሠሙት ነገር እንደሌለ እና ደብዳቤው የደረሠው አካል እንዳላስተላለፈ ነው የተረዳሁት በተጨማሪም በጁምዐ እና ቅዳሜ እለት እዛው ጃቢር መስጅድ ስገዱና የሚተላለፍ መልእክት ካለ ታሣውቁኛላቹህ ያልኳቸው ወጣቶች ምንም እንዳልነበረ አሣወቁኝ እዚህ ጋር አንድ ነጥብ ያዙና እንቀጥል...

አሊ ሚራ መስጅድ ስንደርስ ፕርግራሙ ተጀምሮ የወሌ ሙሀመድ መስጅድ ኢማም ስለ አማና ከባድነት ዳእዋ እያደረጉ ነበር እጅግ ልብን የሚያርሱና የበደልን መጥፎነት ግልፅ አድርገው የሚያሣዩ እንዲሁም ሹመትን መመኘት ከአልላህ እገዛን እንደማያስገኝና ሣይፈልግ የተጫነበት ግን አልላህ እንደሚረዳው በመረጃ እያጣቀሱ ታላላቅ አሊሞች በተገኙበት ድንቅ ምክር አስተላለፉልን አልላህ የተግባር ሠዎች ያድርገን
መድረክ መሪዎቹም ስለ ተቋም ምንነት አላማውና ተግባሩ በግልፅ ቋንቋ አስቀመጡ ለምሣሌ
ተረኛ እነሡ ናቸው የሚባል ነገር መኖር እንደሌለበት
በአንድነት ለጋራ አላማ መጓዝ እንዳለብን
ሀገራዊና ልማታዊ ጉዳዮች ላይ መሣተፍ እንዳለብን
መስጅዶችን በአስተዳደርም ይሁን በጀመዐ ማስተካከል ማጠንከርና ከመጠፋፋት መተቃቀፍ ከመጣላት መፋቀርን በአጠቃላይ በአንድነት በመጓዝ ላይ አደራ አደራ አደራ ብለው አሳሰቡን በቀጣይም

ከታዳሚው ሀሣብ እንዲነሣ መድረኩ ተከፈተ በርግጥም ጠቃሚ የሆኑ ሀሣቦች ተነስተዋል ከተነሡት አስተያየቶች መካከል፦
በወረዳ 10 ላይ የጃቢር መስጅድ አስተዳደር ነኝ የሚለው አንድ ሠው (ከላይ የተጠቀሰው) የሚከተሉትን ሀሣቦች አነሣ
መስጅዱን ወቅፍ ያደረኩት እኔ ነኝ
አስተዳዳሪውም ራሴ ነኝ
ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ ንግግራቸው እንዴት ይጣፍጣል ለነሡ ለማስረከብ ዝግጁ ነን ከጎናቹህ ነን...
የሠፈር አንዳንድ ኡማውን የሚከፋፍሉ ሠዎች አሉ ለህፃናት ጥላቻን የሚሰብኩ
አሽአሪያና ማቱሪዲያ የጀሀነም ናቸው የሚሉ አሉ መረጃ እንዲያመጡ 4 ወር ሙሉ ጠብቀናቸው በዛው የጠፉ አሉ ሠዎችን እንዳይበክሉ ብዬ ህዝቡ ግራ እንዳይጋባ ሀላፊነት ስላለብኝ አስትቻለው...
በአጠቃላይ ይሄ ለውጥ ደስ የሚልና የሚበረታታ ነው ከጎናቹህ ነን....

እነዚህን ወሬዎቹን አስታውሳለው የሚገርመው ደብዳቤውን እንኳን በአግባቡ ያላስተላለፈ አካል ነው እንግዲህ የኡማ ሀላፊነት አለብኝ እያለ ዓሊሞች ፊት የሚያወራው???

ወደ መጨረሻ ላይ ትውውቅ ይደረግ ተብሎ የየወረዳው አመራሮች መድረክ ላይ ወታቹህ ራሣችሁን አስተዋውቁ ተባልንና አስተዋውቀን ስንመለስ ወረዳ 10 ተቃውሞ አለ ማለት ጀመረ። ከመድረክ መሪዎቹ ሌላ ግዜ በሰፊው እንደምንገናኝና እንደሚያወሩበት ቢነገረውም ተደጋጋሚ የእድል ይሰጠኝ ምልክት አሣየ። ዙሁር ደርሷል ኢማሞች ደሞ ወደየ መስጅዶቻቸው መሔድ አለባቸው ቢባልም ፕሮግራሙ በዱዓ ከተዘጋ በኋላ ወደ መድረክ በመሄድ መስጅድ ውስጥ በከፍተኛ ጩኸት መናገር ጀመረ።ቅድም ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ ንግግራቸው እንዴት ይጣፍጣል እንዳላለ በደቂቃ ውስጥ ተቀይሮ አይሆንም አላስረክብም ጲሪሪም ጳራራም ማለት ጀመረ ከወንድሞችም መካከል ይህ ሠው ማን እንደሆነና በ2004/5 ግዜ ምን እንደሠራ የሚያውቁ ወንድሞች ፊትለፊት አፋጠጡት የአልላህ ቤት ላይ መጮህ የለመደ ማንም ይኑር ማን ግድ የለውምና ጃቢር እንደለመደው በመጮህ የሚያሣምን መስሎታል ሣይሳካለትም ቀርቶ ፊቱ ቀልቶ እያጉረመረመ መኪናውን አስነስቶ ያመጣቸውን ሠዎች እንኳ ሙሉ ሳይዝ ተመለሠ

ስንት ነገሮችን ይሁን ይለፍ ብለን ዝም አልን
ISIS ናቹህ ቦክዋራ፣አልሸባብ ተባልን አላዋጣ ሲል
17 ኮሚቴ ትሳደባላቹህ ተባለ አላዋጣ ሲል
ሙፍቲን ተሣድባችኋል ተባለ ለዚህም መረጃ ሲጠየቅ ተቀየረችና ሳዳቶች ናቸው ብሎ እርፍ አሁንም በየግዜው ይቀያየራል ትችቱ የአሁኑ ደሞ ሌላ ናት

4 ወር ሙሉ ጠብቀን መረጃ አልመጣልንም ስላለበት ስለ መፀሀፏ ደሞ ሌላ ሠፊ ታሪክ ነው ራሡን ችሎ እመጣበታለው ኢን ሻ አ አልላህ