Get Mystery Box with random crypto!

የአብሬት ጉዞ አብሬት በጉራጌ ዞን በቸሀ ወረዳ የሚገኝ ቀበሌ ሲሆን በአካባቢው በሱፍያው አለም የ | Bilal Media & Communication

የአብሬት ጉዞ

አብሬት በጉራጌ ዞን በቸሀ ወረዳ የሚገኝ ቀበሌ ሲሆን በአካባቢው በሱፍያው አለም የነበሩ ሸይኾች የነበሩበት ቦታ ነው።

በቦታው በዋናነት የሚታወቀው የአብሬት ሼይኽ (ሰይድ ቡደላ) በመባል በሚታወቁ የሱፍያው ሸይኽ የነበሩበትና ዳዕዋቸውን ሲያካሂዱ የቆዩበት ቦታ ስለሆነ ከሌሎቹ በበለጠ ቦታው ወይም አካባቢው ገኖ ይታወቃል።


የአብሬት ሸይኽ መውሊድ ማክበር
/////////////////////////////////////

በየአመቱ ረጀብ 15 ቀን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ህዝቦች ወደ አብሬት ይጎርፋሉ።

ብዙዎቹ ዘንድ የድሆች ሀጅ በመባልም ይሰየማል ።አብሬት መሄድ እንደ መካ ሲሆን የቁባ ሸይኽ ቀብር ሄዶ መዘየር ደግሞ መዲና ሄዶ የነብዩ صلى الله عليه وسلم መስጂድና ቀብር እንደመዘየር ይቆጠራል በማለት የተጋነነ ምልከታቸውን ሲያንፀባርቁ ይስተዋላል።

እንዲህ አያሉም ሲያዜሙ ይደመጣሉ:_" አብሬት ያናሽ ተብራሸ ወሬ ምር ባይተ የኦድሸ" አብሬትን ያላየ ተበላሽቷል: ወሬ የምን ብሎስ ያወራል"

በጥቅሉ ይህ ቦታ መሄድ ከፍታኛ ረደኤት እና በረከት እንደሚያስገኝ ይታሰባል።ብዙ የተቸገሩ ፣ልጅ ያጡ፣ትዳር አልሳካ ያላቸው፣ስራ አልመቻች ያለው፣በህመም የተቸገሩ ሰዎች እና ሌሎችም ተመሳሳይ ችግር ላይ የወደቁ ሰዎች ወደ ቦታው በማምራት የተለያዩ ነገራቶ ለቁባ ሸይኽ ቀብርና ለአብሬት ሽይኽ ልጆች ስለት ተስለው እንደሚመለሱና በቀጣዩ ጊዜ ደግሞ የተሳሉትን ነገር በመያዝ ወደ ቦታው በማምራት ስለታቸውን ከአሏህ ውጪ ላለ አካል ተፈፃሚ ሲያደርጉ ብዙ አመታቶችን ያስቆጠሩበት የዘውትር ተግባራቸው መሆኑ ይታወቃል።

ቦታው ላይ በረካ አለው ተብሎ ስለሚታሰብ አንዳንዶቹ ወደዚህኛው ቦታ ለብሰው የሄዱትን ልብስ ታጥቦ እጣቢው መሬት ላይ መደፋት የለበትም በሚል እሳቤ ይህ ልብሳቸው የታጠበበት ቆሻሻ ውሃ የሚጠጡ በርካቶች ናቸው።

ብዙ በሽርክ የታጨቁ መንዙማዎችና ተግባረቶች የበዓሉ ዋና ማድመቂያዎች ናቸው።

ቦታው ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ይህ ፀያፍ የሆነው ዚና በተለያዩ ወንበዴ ወንዶችና ሴቶች አማካኝነት ይፈፀማል።እንደውም ይህ ፀያፍ ተግባር በማሰብ ወደ ቦታው የሚያቀኑ ብዙ ከእስልምና እምነት ውጪ ያሉ ብዙዎች መሆናቸው እንደ ቀን ፀሀይ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው።

አንዳንድ አባቶች ከቤታቸው ወደ አጠገባቸው የሚገኝ መስጂድ ገብቶ መስገድ አልችልም እያለ ወደ አብሬት ከአራት _ አምስት ሰአታት ጓዛቸውን ተሸክሞ ሲጓዝ ይስተዋላል።

ይህ ከላይ የጠቀስኳቸው ቦታ ላይ የሚፈፀሙ ተግባራቶች ለግንዛቤ ያክል ጠቀስኳቸው እንጂ እንደ ኢስላም እይታ ይህ በዓል ማክበር ብይኑ ምንድነው የሚለውን መመልከት ብቻውን ተግባሩ የተወገዘ መሆኑ ያስረዳናል።

1/ ከኢስላም ትርጉም ውስጥ " ለአሏህ ፍፁም ታዛዥ መሆንና ላወረደው ህግም (ሸሪዓ) ፍፁም ታዛዥ መሆን ይገኝበታል።

እንዲህ ከሆነ ይህ የአብሬ መውሊድ የሚባለው ነገር አሏህ አዞበታል? ነብያችን صلى الله عليه وسلم መልእክታቸው በሚገባ አድርሰው ሲያበቃ ይህ ተግባር መልእክታቸው ውስጥ አካተውታልን?


እንደሚታወቀው ኢስላም ትንሹም ትልቁ የእለተእለት ተግባራችን በዝርዝር ያብራራ ሲሆን የሽንት ቤት አጠቃቀማችን ሳይቀር በሃዲስ ተብራርቷል።

ይህ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች ተሰብስቦ እና በከፍተኛ ድግስ የሚከበረው ይህ በዓል ኢስላም እንዴት በዝምታ ያልፈዋል?

ነብያችን صلى الله عليه وسلم የጃሂሊያዎች በዓላት ሁሉ ቀርተው ሁለቱ በዓላት እንደ ቀየረልን ሲናገሩ የአብሬት ሸይኽ መውሊድ እውነት መከበር ካለበት ለምን በዝምታ አለፋት።

አላህ سبحانه وتعالى


الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا

ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡

ሲል =_የአብሬት መውሊድ እውነት የእስልምና አካል ከሆነ ለምን መውሊዱ ሳይካተት እምነታቹህ ሞላሁላቹ አለ?

ልብ በል
____
አሏህ እምነታቹህ ሞላሁላቹ ካለ በኃላ አዳዲስ መጤ ተግባራቶች እየጨመሩ ዲን ነው ብለው የሚያከናውኑ ሰዎች አሏህን እያስዋሹ እንደሆነ ሊዘነጉት አይገባም።

አሏህ ሞላሁት እያለ አንተ አአይ ይህ ይቀርሀል እያልክ መባዘን ምን የሚሉት አላዋቂነት ነው?

أَأَنتُمْ أَعْلَمُ أَمِ اللَّهُ

«እናንተ ታውቃላችሁን? ወይንስ አላህ?»

ዲን ላይ የሌለ አዲስ መጤ ነገር ስታመጣ ትልቅ ቅጥፈት እየቀጠፍክ መሆኑ ከግንዛቤ አስገባው።



أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُم مِّنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَن بِهِ اللَّهُ

ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አልሏቸውን?


ወደ አሏህ መዳረስ የምንችለው የአሏህ መልእክተኛን በመከተል እንጂ በተለያዩ ግለሰቦች ፍልስፍና እንዳልሆነ ነብያችን
صلى الله عليه وسلم ከእለታት አንድ ቀን ቀጥተኛ መስመር አሰመሩና ከዳርና ዳሩ ደግሞ የተለያዩ መስመሮች አሰመሩ ከዚያም እንዲህ የሚለው የቁርአን አንቀፅ አነበቡ

وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
↓↓↓→
إن شاء الله


አቡ ሙሀመድ አብዱልናስር መኑር አል_ ጃቢሪይ
↓↓↓↓↓↓→
https://t.me/twhidsunabegegnea