Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦ ☞⑨↠ Dr. Gustav W | Bilal Media & Communication

ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን ስለ ነብዩ መሀመድ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም)፦


☞⑨↠ Dr. Gustav Weil /ዶ/ር ጉስታቭ ዌይል/ (ጀርመናዊ የምስራቅ ታሪክ አጥኚ /ኦሪየንታሊስት/፣ ደራሲ እና ተርጓሚ)
‹‹ሙሐመድ ለሕዝቦቹ አንጸባራቂ ተምሣሌት ነበር፡፡ ምግባሩ ንጹህ እና ጉድፍ አልባ ነበር፡፡ ቤቱ፣ ምግቡ ሁሉ አስገራሚ ቅለት
የሚታይባቸው ነበሩ፡፡ እጅግ ከመተናነሱ የተነሳ ባልደረቦቹ የተለየ መጠሪያ እንዲያበጁለት እንኳ አይፈቅድም ነበር፡፡ ራሱ መሥራት የሚችለውን ነገር ነገር በአገልጋዮች አያሠራም ነበር፡፡ ለሁሉም ሰው በሁሉም ወቅት መገኘት የሚችል ነበር፡፡ የታመመን ጠያቂ፣ ለሕዝቦቹ የሚያዝን ነበር፡፡ ቸርነቱ እና ለጋስነቱ ዳርቻ አልባ የሆነውን ያክል ለሕዝቡ ደኅንነትም እጅግ ተጨናቂ ነበር፡፡››
History of the Islamic Peoples