Get Mystery Box with random crypto!

የስብዕና ልህቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የሰርጥ አድራሻ: @human_intelligence
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 89.04K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።
#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-31 22:17:26 የአቶሚክ ልማድ አስደናቂ ሀይል

ውጤቶችህ የልማዶችህ ቀሪ መለኪያዎች ናቸው፡፡ ያለህ ገንዘብ የፋይናንስ አጠቃቀምህ ውጤት ነው፤ እውቀትህም የመማር ልማድህ ቀሪ መለኪያ ነው።
በሕይወትህ ውስጥ ያሉት ምስቅልቅሎችም ነገሮችን የማጽዳት ልማዶችህ  ድምር ውጤቶች ነው።የምታገኘው የምትደጋግመውን ነው፡፡


የሕይወትህን መዳረሻ ለመገመት ከፈለግህ ማድረግ ያለብህ ነገር ቢኖር የምታገኛቸውንና የምታጣቸውን ጥቃቅን ለውጦች ተከትለህ ማየትና ይህ የለውጥ መስመር በሃያ - በሰላሳ ዓመታት የት እንደሚያደርስህ መረዳት ነው፡፡ የወር ወጪህ ከገቢህ ያነሰ ነው? በየሳምንቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ትሰራለህ? በየቀኑ አዳዲስ ነገሮችን ታውቃለህ? መጽሐፍ
በጥቂቱም ቢሆን ታነባለህ? የወደፊት ሕይወትህን ሙሉ የሚወስኑት እንደነዚህ ያሉ ጥቃቅን የጦር ግንባሮች ናቸው፡፡

በሙሉ ጊዜ በውድቀትና በስኬት መካከል ያለውን ልዩነት ያሰላል፡፡ ጊዜ የሚያደርገው ነገር ቢኖር የምትሰጠውን ነገር ማባዛት ነው፡፡ ጥሩ ልማዶች ጊዜን አጋርህ ሲያደርጉት፣ መጥፎ ልማዶች ግን ጠላትህ ያደርጉታል፡፡

ልማዶች በሁለቱም በኩል የተሳሉ ሰይፎች ናቸው፡፡ መልካም ልማዶች ሊስሉህና ሊያሳድጉህ የሚችሉትን ያህል መጥፎ ልማዶች ደግሞ ቆራርጠው ሊጥሉህ የሚችሉበት እድል በዚያው መጠን ነው፡፡
ለዚህም ነው ዝርዝሩን መረዳት ጠቃሚ የሚሆነው፡፡ ልማዶች እንዴት እንደሚሰሩና እንዴት ወደ ውጤት እንዲወስዱህ ማድረግ እንደምትችል መማር አለብህ፡፡ በዚህ መንገድ የሰይፉን ቆራጭ ስለት የማስወገድ እድል ታገኛለህ፡፡

ብዙውን ጊዜ ሁኔታ ቀያሪ ቅጽበቶች ቀደም ብለው የተሰሩ የብዙ ተግባራት ድምር ውጤቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ተደራራቢ ቅድመ ተግባራት ዋናውን ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈልገውን አቅም ይገነባሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በሁሉም ቦታዎች የሚታይ ነገር ነው፡፡ ካንሰር የሕይወት ዘመኑን 80 በመቶ የሚያሳልፈው የማይታይ ሆኖ ነው፡፡ ከዚያ የሰውነትን አካል የሚቆጣጠረው ግን በወራት ውስጥ ነው፡፡ ሸምበቆም መሬት ለመሬት ስሮቹን በሚዘረጋባቸው አምስት ዓመታት ውስጥ ብዙም አይታይም፡፡ ከዚያ ነው በስድስት ሳምንታት ውስጥ በአየር ላይ እስከ 90 ጫማ ድረስ ማደግ የሚችለው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ልማዶችም የሆነ ወሳኝ ምዕራፍን አልፈን አዲስ ሁኔታ ውስጥ ገብተን እስክንገኝ ድረስ ምንም ለውጥ የሚፈጥሩ አይመስሉንም፡፡ በየትኛውም ሁኔታ መጀመሪያ እና መካከለኛ ዘመን ውስጥ ብዙውን ጊዜ የመከፋት ሸለቆ ይኖራል፡፡ ለውጥ ለማምጣት ስትነሳ የእድገት ደረጃዎችህን በማይቆራረጥ እና ወጥ በሆነ መልኩ ማየት እንደምትችል
ታስባለህ፡፡ ግን አታይም፡፡ በመጀመሪያዎቹ ቀናት፣ ሳምንታትና ምናልባትም ወራት አካባቢ ለውጥ የማይመጣ መስሎ መታየቱ በጣም የሚያበሳጭ ነው፡፡ የትም የምትሄድ መስሎ አይሰማህም፡፡ ይህ የየትኛውም የድርርቦሽ ድል መገለጫ ባህሪ ነው - ሁልጊዜም ትላልቅ ውጤቶች የሚመጡት ዘግይተው ነው፡፡

ዘላቂነት ያላቸውን ልማዶች መገንባትን ከባድ ከሚያደርጉት መሰረታዊ ምክንያቶች መካከል አንደኛው ይህ ነው፡፡ ሰዎች ትናንሽ ለውጦችን ለማምጣት ይሞክሩና ውጤቱ ግን አልታይ ይላቸዋል፡፡ ከዚያም ለማቆም ይወስናሉ። “ለአንድ ወር ያህል በየቀኑ እሮጥኩ፤ እና ለምንድነው ሰውነቴ ላይ ለውጥ ያላየሁት?” ብለህ ልታስብ ትችላለህ፡፡ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ አንድ ጊዜ ከተቆጣጠረህ ጥሩ ልማዶችን እየተውክ ለመሄድ ትመቻቻለህ። ትርጉም ያለው ለውጥ ለማሳየት ግን ልማዶችን ለረዥም ጊዜ ማቆየትና ጉብታውን ለማለፍ የሚያስችላቸው አቅም ማጠራቀም አለባቸው፡፡ እኔም የተዳፈነ ችሎታ ጉብታ (The plateau of atent potential) የምለው ይሄንን ነው፡፡

ጥሩ ልማድ ለመገንባት ወይም መጥፎ ልማድ ለመተው ስትታገል ራስህን ብታገኘው የመሻሻል አቅም አጥተህ እንዳይመስልህ፡፡ ይልቁንም እንደዚህ የሚሆነው ገና የተዳፈነው ችሎታህን ጉብታ ስላለፍክ ብቻ ነው፡፡ “ጠንክሬ ብሰራም ውጤት አላመጣሁም አይነት አቤቱታ “በረዶው ለምን በ26፣ በ27 ወይ በ28 ዲግሪ አልቀለጠም?” ብሎ ቅሬታ እንደማቅረብ ያለ ነው፡፡ ድካምህ አልባከነም፣ እየተጠራቀመ ነው እንጂ፡፡ ሁሉም ድካሞችህ ተደማምረው 32 ዲግሪ ላይ ውጤት ማሳየት ይጀምራሉና፡፡

በስተመጨረሻ የእምቅ ችሎታ ጉብታህን ስታልፍ ሰዎች ስኬትህን የአንድ ቀን ስኬት ብለው ይጠሩታል፡፡ የውጪው ዓለም ሁሉንም የለውጥ ደረጃዎችህን አያይም፡፡ ሰዎች ማየት የሚችሉት ድራማዊ የሆነውን የለውጡን ፍሬ መገለጫ ብቻ ነው፡፡ አንተ ግን ለዚህ ያበቁህ ምንም ለውጥ እያሳየህ በማይመስል ሰዓት ሁሉ የሰራሀቸው ጠንካራ ስራዎች መሆናቸውን ታውቃለህ፡፡

ሁሉም ትላልቅ ነገሮች የሚነሱት ከትናንሽ ጅማሮዎች ነው፡፡ የእያንዳንዷ ልማድ ዘር አንዲት ትንሽ ውሳኔ ነች፡፡ ይህች ውሳኔ ስትደጋገም ግን ልማድ እያደገና እየጠነከረ ይሄዳል፡ ስሮቿ እየተስፋፉ ይሄዱና ቅርንጫፍ ማውጣትም ትጀምራለች፡፡
የእምቅ ችሎታ ጉብታን አልፎ ለመሄድና በሌላው ጎን ለመገኘት የሚያስችለንን የጥንካሬ ትግል ቆይታ የሚወስነው ምንድን ነው? አንዳንድ ሰዎች የመልካም ልማድን ድርርቦሽ ትርፍ ሲያጣጥሙ አንዳንዶች ግን የመጥፎ ልማዶቻቸው ምርኮኛ ሆነው የሚቀሩትስ ለምንድን ነው?

ይቀጥላል

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
9.0K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 21:59:33 ትናንሽ ልማዶች ትልቅ ልዩነት ይፈጥራሉ።
Atomic Habit
ደራሲ- ጄምስ ክሊር
ትርጉም-ድረስ ጋሻነህ

የአንድን ወሳኝ ቅጽበት ሚና ከፍ አድርጎ ማየትና በየቀኑ የሚደረጉ የጥቃቅን መሻሻሎችን ሚና ዝቅ አድርጎ ማየት ይቀለናል ፡፡ ብዙውን ጊዜ ትልቅ ስኬት ትልቅ አድርገን ራሳችንን ተግባርን እንደሚፈልግ እናሳምነዋለን፡፡ ክብደት መቀነስም ይሁን ትልቅ ቢዝነስን መገንባት፣ መጽሐፍ መፃፍም ይሁን ውድድርን ማሸነፍ ወይም የትኛውንም ሌላ ግብ ለማሳካት ሁሉም ሰው የሚያወራለት አይነት መሬት የሚያንቀጠቅጥ ትልቅ ነገርን መስራት እንዳለብን በማመን ራሳችንን እናጨናንቃለን፡፡


ጥቃቅን ነገሮችን በአንድ በመቶ ማሻሻል ግን የማንመኘው ለእይታም የማይገባ ነገር ነው፡፡ ይሄኛው አይነት የመሻሻል መንገድ ግን ከፍተኛ ውጤት የማምጣት አቅም አለው - በተለይ በረዥም ጊዜ፡፡ ትንሽ ለውጥ በጊዜ ሂደት የምታመጣው ልዩነት አስደናቂ ነው፡፡ ሂሳባዊ ስሌቱ ይሄን ይመስላል፡፡ ለአንድ ዓመት ሙሉ በቀን 1 በመቶ እያሻሻልን ብንሄድ በአመቱ መጨረሻ መጀመሪያ ከነበርንበት በ37 በመቶ እንሻሻላለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በቀን በአንድ በመቶ ወደታች እየሄድን ለአንድ ዓመት ከቆየን ወደ ዜሮ አካባቢ እንደርሳለን፡፡ በጥቂት ጅማሮ የተጀመረች ቀጣይነት ያላት ትንሽ መሻሻል ተጠራቅማ ታሪክ ትሰራለች፡፡

ልማዶች ራስን የማሻሻል ድርብርብ ድርብርብ ወለዶች (compound interests) ናቸው፡፡ በድርብርብ ወለድ ራሱን በሚያበዛበት ልክ ገንዘብ መጠን የልማዶች ውጤትም በደጋገምናቸው መጠን ይባዛል። በየቀኑ ተነጥለው ሲታዩ የሚፈጥሩት ለውጥ በጣም ጥቂት መስሎ ቢታይም በወራት ወይም በዓመታት ቆይታ የሚያመጡት ለውጥ ግን አስደናቂ ነው፡፡ የመልካም ልማዶች ጠቀሜታዎች እና የመጥፎ ልማዶች ጉዳቶች ግልጽ ብለው የሚታዩት ከአምስት ወይም ከአስር ዓመታት በኋላ ወደኋላ ዞር ብለን ስንመለከታቸው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

ይህንን ነገር በየቀኑ ሕይወታችን አንጥረን ለማየት ከባድ ነገር ሊሆን ይችላል። በዚህም የተነሳ እነዚህን አይነት ለውጦች መተውና መናቅ ይቀናናል፡፡ ዛሬ ላይ ጥቂት ገንዘብ መቆጠብ ብትችል አሁኑኑም ሚሊየነር አትሆንም፡፡ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጂም ብትሰራ በአካል ቅርፅህ ላይ ምንም ለውጥ አታይም፡፡ ዛሬ ምሽት ፈረንሳይኛ ቋንቋን ለሶስት ሰዓታት ብታጠና የቋንቋው ተናጋሪ አትሆንም፡፡ ጥቃቅን ለውጦችን ለማምጣት እንሞክራለን፡፡ የለውጡን ውጤት ቶሎ ማየት ስለማንችል ግን ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለሳለን፡፡

መጥፎው ነገር ደግሞ ይህ የለውጡ ውጤት የሚታይበት ፍጥነት እጅግ ዘገምተኛ መሆን ለመጥፎ ልማዶች እንድንመቻች የሚያደርገን መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ ምሽት ቤተሰቦችህን ተወት አድርገህ ስራ ላይ ብታሳልፍ ይረዱሃል፡፡ ሥራህን የምትጨርስበት ሰዓት ለነገ ብለህ ብታሳድረው ለዚህ የሚሆን ጊዜ “ነገ ላይ አይጠፋም፡፡ በዚህ መንገድ አንዲትን ውሳኔ መተው ብዙም ከባድ ነገር አይደለም፡፡

መጥፎ ውሳኔዎችን በየቀኑ ችግሮቻችንን በ1% እያባባስን፣ እየደጋገምን፣ ትንንሽ ስህተቶችን እየሰራን እና ጥቃቅን ምክንያቶችን እያበጀን ከሄድን ግን ድምር ውጤታቸው እጅግ የገዘፈ እና የከፋ ይሆናል፡፡ ችግር የሚዳርጉንም እዚህም  እዚያም የምንስራቸው ችግሮቻችንን በ1% የማባባስ ስራዎቻችን ድምር ውጤቶች ናቸው

በልማዶቻችን ላይ በምናመጣቸው ጥቃቅን ለውጦች የምናመጣው ጠቅላላ . ውጤት የአውሮፕላንን የበረራ መስመር በጣም በትንሽ ዲግሪ በመቀየር እንደሚመጣው ለውጥ ያለ ለውጥ ነው፡፡ ለምሳሌ ከሎስ አንጀለስ ወደ ኒው ዮርክ እየበረርክ ነው እንበል፡፡ ከላክስ አየር ማረፊያ የተነሳውን
አውሮፕላን ፓይለቱ በ 3.5 ዲግሪ ወደ ደቡብ ቢቀይረው መዳረሻህ የሚሆነው ኒው ዮርክ ሳይሆን ዋሽንግተን ዲሲ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ትንሽ ለውጥ ስትነሳ አካባቢ አይታወቅህም፡፡ የአውሮፕላኑ አፍንጫም አቅጣጫውን የሚቀይረው በጣም በትንሽ ጫማዎች ናቸው፡፡ ጉዞው መላው አሜሪካን ሲያካልል ግን መዳረሻህ መጀመሪያ ካሰብከው ቦታ በመቶዎች በሚቆጠሩ ማይሎች ርቀት ላይ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በየቀኑ በልማዳችን ላይ የምናሳያቸው ጥቃቅን ለውጦች ሕይወታችንን ፍፁም የተለየ መዳረሻ ይስጡታል። በ1% የተሻለ ወይም በ1% የወረደ ውሳኔን መስጠት ትርጉም ሊኖረው የሚችል ለውጥ አይመስለንም፡፡ በጊዜ ሂደት ግን አሁን አንተ በሆንከው እና አንተ ትሆን በነበረው ማንነት መካከል ያለውን ልዩነት የሚፈጥሩት እነዚህ ጥቃቅን ልዩነቶች ናቸው፡፡ ስኬት የ በየቀኑ ልማዶች ድምር ውጤት ነው፡፡ ወሳኙ ነገር ልማዶችህ ወደ ስኬት የሚወስዱህ ናቸው ወይስ አይደሉም? የሚለው ነው፡፡

ስለሆነም አብዝተህ መጨነቅ ያለብህ ዛሬ ላይ ስላመጣኸው ውጤት ሳይሆን የዛሬው ጉዞህ አቅጣጫ ላይ ነው፡፡ የወጪ አወጣጥ ልማድህ ካልተቀየረ ጥሩ ነገር አትጠብቅ፡፡ በተቃራኒው ዛሬ ላይ ደሃ ብትሆንም ሽርፍራፊ ሳንቲሞችን የምትቆጥብ ከሆነ ግን ወደ የፋይናንስ ነፃነት የሚወስደው መንገድ ላይ ነህ - ከምታስበው በላይ በዝግታ ብትጓዝም፡፡

ይቀጥላል

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
7.2K viewsedited  18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 21:01:42 ይቀመጣል እንደ አደራ
ሰው ክፉም ሰራ
ደግም ሰራ

ሁሉም የእጁን ያገኘዋል፤
ቢቆይ እንጂ መች ይቀራል!!

ወንድሙ ጅራ

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence
7.2K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 08:23:31 መደመር

ጊዜው ተቀይሮ

ዘመን ተቀይሮ

ይቀንሳል ያልነው የመከራው ኑሮ

ተደራርቦ መጣ ሁሉም ተደምሮ::

Ⓒgetem
8.0K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 20:53:21 ድንቅ አባባሎች

‹ልምድ ንድፈሃሳብ ከሌለው እውር ነው፡፡ ነገር ግን ንድፈሃሣብ ራሱ ልምድ ከጎደለው እንደው ዝምብሎ የምሁር ጨዋታ ነው የሚሆነው፡፡››
ኢማኑኤል ካንት

‹‹ደስታ ከምክንያታዊነት ጋር የሚስማማ ሳይሆን ከምናብ ጋር የሚዋሃድ ነው፡፡››
  ኢማኑኤል ካንት

‹‹ሌላ ሠው ማፍቀር የፈጣሪን ሌላኛውን ፊቱን ማየት ነው፡፡››
  ቪክቶር ሂጎ

"አእምሮ አስደናቂ አገልጋይ ነው ፣ ግን አስፈሪ ጌታ ነው።"
  ሮቢን ሻርማ

"አንድን ነገር መቼም ላላውቀው አልችልም በሚል ስሜት ተማረው፤ስታውቅ ደግሞ መቼም ላጣው እችላለሁ በሚል ስሜት አጥብቀህ ያዘው!!"
  ኮንፊሽየስ

"ሁለት የሞኝነት መንገድ አለ ። አንደኛው እውነት ያልሆነውን ማመን ሲሆን ሌላኛው እውነት የሆነውን አለማመን ነው ።"
      ሶረን ኪድጋርድ

‹በህግ አንድ ሠው የሌላን ሠው መብት ከተጋፋ ወንጀለኛ ነው፡፡ በስነምግባር ግን አንድ ሠው ሌላ ሠው ላይ ክፉ ማሠቡ ብቻ ወንጀለኛ ያደርገዋል፡፡››
  ኢማኑኤል ካንት

"ትንሽ ኪሳራ ፈርተን ትልቅ ጥቅም የሚገኝበትን ነገር አለመሞከር ሞኝነት ነው።"

"ቅናት ከፍቅር ጋር አብሮት ይኖራል ነገር ግን አብሮት አይሞትም።"
ያልታወቀ

"ስለራስዎ ጥሩ ስሜት እስኪሰማዎት ድረስ አንድ ሰው ስለራሱ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ማድረግ አይችሉም ፡፡"
  ሮቢን ሻርማ

  ‹‹ሠዎች ጥንካሬ አላጠራቸውም፡፡ ያጠራቸው ፈቃድ ወይም ፍላጎት ብቻ ነው፡፡››
  ቪክቶር ሁጎ

‹‹ዝናህን ለመገንባት ሃያ ዓመት ይወስድብሃል፡፡ ዝናህን ለማበላሸት ግን ሃያ ደቂቃ በቂህ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ካሰብክ ነገሮችን በተለያየ መንገድ ታከናውናቸዋለህ፡፡››
  ዋረን በፌት

"ከኑሮህ ለመማር የምትከፍለው ትልቁ ዋጋ ትዕግስት ነው።"
ካቴና

"የበለጠ ለመስራት እና የበለጠ ለመሞከር ጥረት ያድርጉ። ህልሞችዎን ለመጀመር ሀይልዎን ይጠቀሙ ፡፡ ህልሞችዎን ያስፋፉ። በአእምሮዎ ምሽግ ውስጥ ማለቂያ የሌለው አቅም ሲኖርዎት የመለስተኛነት ሕይወት አይቀበሉ ፡፡ ታላቅነትዎን ለመጠቀም ደፉሩ"

ሮቢን ሻርማ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
4.4K viewsedited  17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 20:39:16 ተረኛው ጨባጭ!

“አንድ ሰው ሕጻን ሆኖ ሲወለድ እጁን (መዳፉን) ጨብጦ ነው፤ አንድ ሰው ሸምግሎ ሲሞት ደግሞ እጁን (መዳፉን) ዘርግቶ ነው” ይላል ካልታወቀ ምንጭ የተቀዳ እውነተኛ አባባል፡፡

ለአንድ ሕጻን አንድን ነገር በእጁ አስይዛችሁት ካወቃችሁ ልጁ የያዘውን ነገር በቀላሉ እንደማይለቅ ትደርሱበታላችሁ፡፡ አንድ ሕጻን ልጅ እጁን ጨብጦ መወለዱ ሁሉን ለመያዝ፣ ሁሉን በእጁ ለማስገባትና ሁሉን ነገር በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ የመሞከሩ ምልክት ነው፡፡

አንድ ሰው ሸምግሎ ሲሞት እጁን ዘርግቶ መሞቱ ደግሞ ሁሉን አይቶት፣ ሞክሮት፣ ጨብጦና “የእኔ ነው” ብሎ በመጨረሻ ምንም ነገር የእርሱ እንዳልሆነና አንድ ቀን ሁሉም ነገር ከእርሱ ቁጥጥር ውጪ እንደሚሆን የመገንዘቡ ምልክት ነው፡፡  

እውነታው ይህ ነው፡- ተወልደን በልጅነት ባሳለፍንበት ወቅትና ሸምግለን ከዚህ አለም ወደመሰናበት በምንደርስበት ወቅት መካከል ባሉን እንደ ጥላ በሚያልፉት አመታቶቻችን መያዝና መቆጣጠር በምንችለውና በማንችለው መካከል መለየት አስፈላጊ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ነገ ሁሉንም ነገር ትተነው እንደምናልፍ በመገንዘብ ዘመናችንን እንዳናባክነው እናስተውል፡፡

እጅህ በገባው ነገር ደስተኛ ሁን፣ ለመልካም ነገር ተጠቀምበት፡፡ እጅህ ለማስገባት ያልቻልከውን ነገር ለማስገባት ሞክር፣ ነገር ግን ሁሉን ካልያዝኩ በማለት ዘመንህን አታስበላ፡፡

ለጊዜው ነው እንጂ ምንም ነገር በቋሚነት የአንተ አይደለም፡፡ የእኔ ነው ብለህ የምታስበው ሁሉ ለጊዜው በአደራ የተሰጠህ ነው፡፡ ዛሬ አንተ የምትኖርበትን ቤትና ትናንት መሬት የእኔ ነው ብሎ የሚኖርበት ሰው ነበር፡፡ ዛሬ ግን የአንተ ነው፡፡ ነገ ደግሞ ይህንን ስፍራ ሌላው ተረኛው ጨባጭ ይረከበዋል፡፡

ቁም ነገሩ ዛሬ በእጅህ ያለውን መልካም ነገር  የመልቀቂያህ ጊዜ እስከሚመጣ ድረስ ለመልካም ዓላማ የመጠቀምህ ጉዳይ መሆኑን ላስታውስህ፡፡

ዶክተር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
8.8K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 20:37:03 በባንክ አካውንታችሁ ውስጥ 86,400 ብር ተቀማጭ አላችሁ እንበልና እና የሆነ ሰው ከአካውንታችሁ ላይ 10 ብር ሰረቃችሁ እንበል። አስር ብሩን ለማስመለስና የወሰደባችሁን ሰው ለመያዝ ብላችሁ 86,390 ብሩን ታባክናላችሁ ወይስ ዝም ብላችሁ ትታችሁ መኖራችሁን ትቀጥላላችሁ? አዎ በእርግጠኝነት ትታችሁ መኖርን ትቀጥላላችሁ።

እንግዲህ በቀን ውስጥም 86,400 ሰከንድ ጊዜ አለን። ስለሆነም የአንድ አሉታዊ ሰው 10 ሰከንድ ንግግር 86,390 ሰከንዳችንን እንዲረብሸን መፍቀድ የለብንም። ሕይወት ከዚያ በላይ ትልቅ ናትና ለትናንሽ ነገር ጊዜዎን አያጥፉ።

@Human_Intelligence
7.1K viewsedited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 21:27:21 በቃ ልመዱት !!!

•  ሰዎች “አደርገዋለሁ” ብለው የገቡላችሁን ቃል ኪዳን ላይፈጽሙ ይችላሉ - ልመዱት!

•  ዛሬ የሚወዷችሁና የሚያከብሯችሁ ሰዎች ነገ ሊጠሏችሁና ሊንቋችሁ ይችላሉ - ልመዱት!

•  ዛሬ ምስኪን መስለው ለሕልውናቸው በእናንተ እርዳታ ላይ የተደገፉ ሰዎች ነገ ውለታ-ቢስ ሆነው ልታገኟቸው ትችላላችሁ - ልመዱት!

•  ሰዎች የሆናችሁትን ማንነት ሳይሆን ያላችሁን ቁሳቁስ አይተው እንደቀረቧችሁ ልትደርሱበት ትችላላችሀ - ልመዱት!

•  አንዳንድ ሰዎች በሰላሙ ጊዜ የሰሙትን ምስጢራችሁን ግንኙነታችሁ ሻከር ሲል ለወሬና እናንተንው ለማጥቃት ሊጠቀሙበት ይችላሉ - ልመዱት!

እነዚህንና እነዚህን መሰል በማንኛውም ሕብረተሰብ መካከል የሚንጸባረቁ የሰዎች ባህሪያትን መልመድ ማለት፣ ሁል ጊዜ ከሰዎች የምንጠብቀውን ነገር እንደማናገኝ መገንዘብና ራስን ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡

ከሰዎች የምንጠብቀውን መልካም ነገር ስናገኝ ደስ የመሰኘታችንንና ሰዎቹንም የማመስገናችን ልምምድ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለማንኛውም አይነት ወጣ ያለ የሰዎች ሁኔታ ራስን ማዘጋጀትና ከሁኔታው ባሻገር አልፎ ለመሄድ የውስጥ ውሳኔን መወሰን እጅግ ጠቃሚ ልምምድ ነው፡፡ 

እንደሰው የመለዋወጥ ሁኔታ የሚለዋወጥ ሰባራ ማንነት እንደሌላችሁ ለራሳችሁ የምታስመሰክሩበት ቀን ይሁንላችሁ!

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
8.9K viewsedited  18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 21:47:18
የአብነት አጎናፍር አልበም ተለቋል
Listen to Aleke on #Sewasew Music
https://play-sewasewmusic.tunedglobal.com/albums/204027285?country=ET
11.4K viewsedited  18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 08:19:47 የራስ-በራስ ምልከታ ወሳኝነት

ማንም ሰው ስለ እኛ ካለው አመለካከት ይልቅ እኛው በራሳችን ላይ ያለን አመለካከት የላቀ ተጽእኖ አለው፡፡

ከሚከተሉት ሁለት እጅግ ጎጂ ከሆኑ የራስ-በራስ ምልከታዎች ጠንቀቅ!

1.  ሁሉም ሰው (አብዛኛው ሰው) እንደሚወደንና እንደሚያደንቀን ማሰብ፡፡

ይህ አመለካከት ከእውነታ የራቀ የቅዠት አለም ውስጥ እንድንኖር አጋልጦ ይሰጠናል፡፡ ምንም አይነት ውብ፣ ድንቅና ጎበዝ ሰዎች ብንሆን የሚወዱንና የሚቀበሉን ሰዎች የመኖራቸውን ያህል የማይወዱንና የማይቀበሉንም ሰዎች ሞልተዋል፡፡ ከዚህ እውነታ ሊያመልጥ የሚችል ማንም ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡ ሁሉም ሰው እንደሚወደንና እንደሚቀበለን ማሰብ ላልተፈለገ የስሜት ቁስል አሳልፎ ይሰጠናል፡፡ ይህ ቀውስ የሚመጣው እውነታውን ቀስ በቀስ እያየነው ስንመጣ ነው፡፡  

2.  ሁሉም ሰው (አብዛኛው ሰው) እንደማይወደንና እንደማይቀበለን ማሰብ፡፡

ይህ አመለካከት ተቀባይነት ለማግኘት ያልሆነውን ሆነን፣ የሌለንን ደግሞ እንዳለን አስመስለን እንድንኖር ይገፋፋናል፡፡ እዚህ ጋርም ማስታወስ ያለብን ነገር፣ ምንም አይነት ሰዎች ብንሆንና በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን የማይወዱንና የማይቀበሉን ሰዎች የመኖራችውን ያህል የሚወዱንና የሚቀበሉን ሰዎች እንዳሉ ነው፡፡ ይህ እውነት የገባቸው ሰዎች አስገራሚ የሆነ በሚወዷቸውና በሚቀበሏቸው ሰዎች ላይ የማተኮርና በዚያ ላይ የመገንባት ብቃት አላቸው፡፡

በሉ እንግዲህ፣ የማይቀበሏችሁ ሰዎች ካሉ፣ ይህንን አመለካከታቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ መሞከሩ አይከፋም፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን ስለ እነሱ እያሰቡ መዋልና ማደር ተውና በሚቀበሏች ሰዎች ላይ ትኩራትችሁን አድርጉ፡፡

በሌላ ጎኑ ደግሞ፣ የሚቀበሏችሁን ሰዎች በማሰብ መደሰትና በሁኔታው ላይ በመገንባት አንድን መልካም ነገር ለማከናወን መጠቀም ተመራጭ መንገድ ነው፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
2.6K views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ