Get Mystery Box with random crypto!

የራስ-በራስ ምልከታ ወሳኝነት ማንም ሰው ስለ እኛ ካለው አመለካከት ይልቅ እኛው በራሳችን ላይ | የስብዕና ልህቀት

የራስ-በራስ ምልከታ ወሳኝነት

ማንም ሰው ስለ እኛ ካለው አመለካከት ይልቅ እኛው በራሳችን ላይ ያለን አመለካከት የላቀ ተጽእኖ አለው፡፡

ከሚከተሉት ሁለት እጅግ ጎጂ ከሆኑ የራስ-በራስ ምልከታዎች ጠንቀቅ!

1.  ሁሉም ሰው (አብዛኛው ሰው) እንደሚወደንና እንደሚያደንቀን ማሰብ፡፡

ይህ አመለካከት ከእውነታ የራቀ የቅዠት አለም ውስጥ እንድንኖር አጋልጦ ይሰጠናል፡፡ ምንም አይነት ውብ፣ ድንቅና ጎበዝ ሰዎች ብንሆን የሚወዱንና የሚቀበሉን ሰዎች የመኖራቸውን ያህል የማይወዱንና የማይቀበሉንም ሰዎች ሞልተዋል፡፡ ከዚህ እውነታ ሊያመልጥ የሚችል ማንም ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡ ሁሉም ሰው እንደሚወደንና እንደሚቀበለን ማሰብ ላልተፈለገ የስሜት ቁስል አሳልፎ ይሰጠናል፡፡ ይህ ቀውስ የሚመጣው እውነታውን ቀስ በቀስ እያየነው ስንመጣ ነው፡፡  

2.  ሁሉም ሰው (አብዛኛው ሰው) እንደማይወደንና እንደማይቀበለን ማሰብ፡፡

ይህ አመለካከት ተቀባይነት ለማግኘት ያልሆነውን ሆነን፣ የሌለንን ደግሞ እንዳለን አስመስለን እንድንኖር ይገፋፋናል፡፡ እዚህ ጋርም ማስታወስ ያለብን ነገር፣ ምንም አይነት ሰዎች ብንሆንና በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን የማይወዱንና የማይቀበሉን ሰዎች የመኖራችውን ያህል የሚወዱንና የሚቀበሉን ሰዎች እንዳሉ ነው፡፡ ይህ እውነት የገባቸው ሰዎች አስገራሚ የሆነ በሚወዷቸውና በሚቀበሏቸው ሰዎች ላይ የማተኮርና በዚያ ላይ የመገንባት ብቃት አላቸው፡፡

በሉ እንግዲህ፣ የማይቀበሏችሁ ሰዎች ካሉ፣ ይህንን አመለካከታቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ መሞከሩ አይከፋም፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን ስለ እነሱ እያሰቡ መዋልና ማደር ተውና በሚቀበሏች ሰዎች ላይ ትኩራትችሁን አድርጉ፡፡

በሌላ ጎኑ ደግሞ፣ የሚቀበሏችሁን ሰዎች በማሰብ መደሰትና በሁኔታው ላይ በመገንባት አንድን መልካም ነገር ለማከናወን መጠቀም ተመራጭ መንገድ ነው፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence